Get Mystery Box with random crypto!

#የወጣቶች_ሕይወት (ሕይወተ ወራዙት) (በቀሲስ ሕብረት የሺጥላ) #ክፍል_2 #ሕልመ_ለሊት_መፍት | መዓዛ ሠናይ

#የወጣቶች_ሕይወት (ሕይወተ ወራዙት)

(በቀሲስ ሕብረት የሺጥላ)
#ክፍል_2

#ሕልመ_ለሊት_መፍትሄ_አለው ?

ብዙ ሰዎች ተግቶ ለመፀለይ ፣ ለማስቀደስና ለመቁረብ በወሰኑ ጊዜ ሕልመ ለሊት እንቅፋት እየሆነ ይፈተኑበታል። በእርግጥ መብላትና መጠጣት ሳያቆሙ ሙሉ ለሙሉ ከሕልመ ለሊት መለየት አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ የሚቻል ነገር አይደለም ። ስለዚህ መፍትሄዎችን እናያለን

#ሀ በመፅሐፈ መነኮሳት ላይ"በሌሊት በሕልም ከሴት ጋር የተገናኘህ መስሎህ ዘር ቢወርድህ በመዓልት አታስባት " ይላል ። ሕልምህን ደስ እያለህ ብታስባት ግን በተግባር ዝሙትን ወደ መፈፀም ያደርስሃል። ስለዚህ ከሕልመ ለሊት ፈተና ለመዳን አንዱ መፍትሔ ሕልምን በውን ደስ እየተሰኙ መላልሶ አለማሰብ ነው

#ለ ሕልመ ለሊት በምታይበት ጊዜ ከነቃህ ቸል ብለህ ተመልሰህ አትተኛ ። ፈጥነህ ተነሳና ተጣጥበህ ጸሎት አድርስ ። ከተቻለህ ስገድ ባይቻልህ ግን የባሕሪህን ድካም ፈጣሪ ያውቀዋልና ይቅር በለኝ ፣ አድነኝ ፣ እያልህ ወደ እግዚአብሔር ለምን

#ሐ ሌላው ከሕልመ ለሊት ለመዳን ዋነኛው መፍትሔ ውኀ በብዛት አለመጠጣት ነው ። መፅሐፈ መነኮሳትም ይሄን ሲመሰክር " እንደ ውኀ ጥም አካልን የሚያደርቅ ፣ከሕልመ ሌሊትና ከዘር መፍሰስ ፣ በቀን ሐጢአት ማሰብን የሚያጠፋ የለም " ይላል ። አንድ ሰው ምንም በጾም አመጋገቡን ቢቀንስ አብዝቶ ውኃ የሚጠጣ ከሆነ አይጠቀምም። ለምን ቢባል ሰውነቱ ስለሚለመልምና ሰይጣን እርሱን ለማሳት መንገድ ስለሚያገኝ ነው ። ስለዚህ ከሕልመ ሌሊት እፎይ ለማለት ከፈለክ "ውኃን ከልክለህ ሰውነትህን አስጨንቀው " ተብለሀል። ወንጌልም ይህን ሲያጠነክር እንዲህ ይለናል ፦ "ርኩስ መንፈስ ግን ከሰው በወጣ ጊዜ ዕረፍት እየፈለገ ውሃ በሌለበት ቦታ ያልፋል ፤ አያገኝምም ። በዚያን ጊዜ ወደ ወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ ይላል ፣ ቢመጣም ባዶ ሆኖ ተጠርጎ አጊጦ ያገኘዋል " (ማቴ 12-43) ይህ ጥቅስ ብዙ ትርጉሞች ቢኖሩትም ከያዝነው ሃሳብ ጋር የሚዛመደውን ብቻ እንይ ፡" ርኩስ መንፈስ ግን ከሰው በወጣ ጊዜ ዕረፍት እየፈለገ ውሃ በሌለበት ቦታ ያልፋል ። ማለት ሰይጣን መግቢያ ካገኘው ብሎ ሰውነቱን በረሃብና በጥም ወደሚያስጨንቅ ሰው ይሄዳል ማለት ነው ። ይልቁንም "ውሃ በሌለበት" ማለቱን መዘንጋት የለብንም ።"አያገኝምም "የሚለው ቃል ደሞ ሰይጣን ሰውነቱን በውሃ ጥም (በፆም) በሚያስጨንቅ ሰው ላይ ለማደር አለመቻሉን ያሳያል ።

#መ በሕልመ ለሊት በተደጋጋሚ እንዳትጠቃ ወደ ዝሙት ከሚያመራ ማናቸውም ነገር ሽሽ። በመሸ ጊዜ የምታያቸውን ፊልሞች ፣ ንባቦች ፣ ሌሎችንም ነገሮች በጥንቃቄ መርምረህ ለፍትወት የሚያጋልጡትን ሽሽ።ከዚያ ይልቅ ደጋግ መንፈሳዊ መፅሐፍትን ለማንበብ ትጋ ።

#ሠ ሌላው መፍትሄ ደግሞ ከመንፈሳዊ መምህራንና ከአበው ካህናት ጋር እየተመካከሩ በሚያቀርቡት የመፍትሄ ሀሳብ መጓዝ ነው ። እዚህ ላይ ልንጠነቀቅ የሚገባን የምናማክረው ሰው ምስጢራችንን ለመጠበቅ የታመነና በምንነግረውም ነገር ራሱ ወደ ፈተና ሊገባ የማይችል በሕይወቱ ብዙ ተሞክሮ ያለው መሆን አለበት ። እንዲሁም ጥሩ መፍትሄ አለን ፡ ልፋፈ ፅድቅ እንደግማለን እያሉ ከሚያጭበረብሩ ተኩላ ባህታውያንም መጠንቀቅ
አለብን

https://t.me/meazasenay