Get Mystery Box with random crypto!

በዚህ ማለዳ ባረኳችሁ፤ ከየትኛዉም እስራት እግዚአብሔር ዛሬና አሁን ይፍታችሁ በኢየሱስ ስም። | የእግዚአብሔር ምኩራብ ቤተክርስቲያን/ SYNAGOGUE OF GOD CHURCH/ ⭐ ሲኤምሲ አጥቢያ ⭐

በዚህ ማለዳ ባረኳችሁ፤ ከየትኛዉም እስራት እግዚአብሔር ዛሬና አሁን ይፍታችሁ በኢየሱስ ስም።
ሀይልን ይጨምርላችሁ፣ የሚያቆማችሁ አይኑር፣ ራሳችሁን እንድትዘጉ የሚያደርግ የሚጥር አይኑር፣ መንገዶቻችሁን ለማዘጋት፤ ለማስቀረት፤ ለማብረድ፤ ለማቀዝቀዝ፤ ለማዘግየት፤ ለማስቀረት ማንም እናንተን አይቻል በጌታ በኢየሱስ ስም። እግዚአብሔር ያሻግራችሁ፣ እግዚአብሔር ከጤንነትን ፈተና ያሻግራችሁ፣ ከኑሮ ተግዳሮት ያሻግራችሁ፣ ከተቃዋሚዎች ሁኔታ ያሻግራችሁ እግዚአብሔር በአምላኬ ቅጥሩን ያዘልላችሁ፣ ወደ ሰፊ ሜዳ ያውጣችሁ፣ እግዚአብሔር ሀይል ይስጣችሁ በጌታ በኢየሱስ ስም። በተከፈተላችሁ በር መውጣትና መግባት ይሁንላችሁ፣ የተባረኩ ቀኖችን ይጨምርላችሁ፣ የእግዚአብሔር ደስታ አሁንም በእናንተ በኩል ይፈጸም። ሽንፈትን፤ ድካምን፤ ዝለትን፤ ስንፍናን፤ ተግዳሮትን እግዚአብሔር ከፊታችሁ ይጣልላችሁ፤ እነዚህን ተሻግራችሁ ሂዱ፣ የተባረከ ቀንና ዘመን ይሁንላችሁ። መልካም ቀን/ለሊት ተባረኩ።