Get Mystery Box with random crypto!

#ህይወት_ያለበት_ድንቅ_መዝሙር_ነዉ_ስሙት። እንዲከተላችሁ አስቀድሙ! በእግዚአብሔር መንግስ | የእግዚአብሔር ምኩራብ ቤተክርስቲያን/ SYNAGOGUE OF GOD CHURCH/ ⭐ ሲኤምሲ አጥቢያ ⭐

#ህይወት_ያለበት_ድንቅ_መዝሙር_ነዉ_ስሙት።
እንዲከተላችሁ አስቀድሙ!

በእግዚአብሔር መንግስት የሚያስፈልጋችሁ ነገር ይከተላችኋል እንጂ አትከተሉትም። ክርስትና መከተል ሳይሆን ማስቀደም ነው። የእግዚአብሔርን መንግስት እስካስቀደማችሁ ድረስ ሊከተላችሁ የተገባ ነገር በሙሉ ይከተላችኋል። ምድራዊ ነገር ሲከተላችሁ በረከት ነው። ስትከተሉት እርግማን ነው። ቤተክርስቲያን ዉስጥ ሆኖ ላለመረገም የህይወታችሁ ዋና ለሚሆነዉ ፅድቅና መንግስቱ ቅድሚያ ስጡ።

“ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።ማቴዎስ 6፥33

መልካም ቀን። ሐምሌ 19/11/2014ዓ.ም፤ “የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።”
— 2ኛ ቆሮ 13፥14

#የእግዚአብሔር_አገልጋይ_ማስረሻ_በላይ
መልዕክቱን ለሌሎች አድርሱልኝ።