2022-02-02 21:48:41
#ለመረጃ_ይሆን_ዘንድ
ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ: ጥር 21/2014 ዓ.ም: ቅዳሜ: 8:00 ሰዓት: ንባብና አንባቢ እንዲበዛ ጥረት ለሚያደርጉ ለሰባት አካላት ለመተዋወቂያ ይሆነው ዘንድ (ለእያንዳንዳቸው ከሁለት መቶ በላይ የሆኑ) መጻሕፍትን በስጦታ አስረክቧል።
በአጠቃላይ የመጽሐፍ ባንኩ በዕለቱ ከሁለት ሺህ መጻሕፍት በላይ በዚሁ ዕለት አበርክቷል።
ስጦታውን የተረከቡት አካላት ከአዲስ አበባ: ከአለም ገና: ከሞጆ: ከጋሞ: ከእንጨቆረር: ከደብረታቦር: ከሲዳማ የተወከሉ አንባብያን ናቸው።
በዕለቱ ከተለያዩ አካባቢዎች ተወክለው የመጢ አንባብያን ስለንባብ ማዕከላቸው አጫጭር መግለጫዎች የሰጡ ሲሆን የዛጎል የመጻሕፍት ባንክ ሥራ አስኪያጅ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደን (ዶክተር) ጨምሮ ጋዜጠኛና ደራሲ ዘነበ ወላ እና ዶክተር ፈቀደ አግዋር ('የልብ ጠጋኙ ማስታወሻ' ደራሲ) እና ሌሎችም ተጋባዥ እንግዶች የንባብ ተሞክሯቸውንና ጥበባዊ ትረካዎቻቸውን አካፍለዋል።
በባንኩ በኩል መጻሕፍት በመለገስና አርአያነት ያለው ተግባር በመፈጸም ሲተባበሩ ለቆዩ ግለሰቦችም የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል ።
ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ : ከዚህ ቀደም ከወዳጆቹና ከዓላማው ደጋፊዎች የተለገሱትን: ከሃያ አምስት ሺህ በላይ የሆኑና ልዩ ልዩ ይዘት ያላቸውን መጻሕፍት ለተለያዩ አካባቢዎች (በገጠር ከተማው) መለገሱ ይታወቃል ።
አድራሻችን:- አራት ኪሎ ከቱሪስት ሆቴል ጀርባ: ኢክላስ ሕንጻ: አብርሆት መጻሕፍት ቤት አጠገብ።
ለተጨማሪ መረጃ:- 0900651010/ 0941960940::
https://t.me/zagolbookbank
894 views18:48