Get Mystery Box with random crypto!

ማራኪ ስነ-ፅሁፍ

የቴሌግራም ቻናል አርማ maraki_lyrics — ማራኪ ስነ-ፅሁፍ
የቴሌግራም ቻናል አርማ maraki_lyrics — ማራኪ ስነ-ፅሁፍ
የሰርጥ አድራሻ: @maraki_lyrics
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 682
የሰርጥ መግለጫ

በያላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ!!! ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ፡ በቻናላችን ማራኪ ፣ አዝናኝና ቁም ነገር የሚያስጨብጡ ስነ -ፅሁፎችን ፡ ከተለያዩ የስነ-ፅሁፍ ባለሙያዎች ወደ እናንተ ይዘን እንቀርባለን።
https://t.me/ n3xAcsHqjJNlNDg0
ሀሳብና አስተያየት በ @Muke_ye ያድርሱን

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-05 22:55:04 ጠቃሚ_መልእክት
አንድ ንጉስ አስር ተናካሽ ውሾች (Wild dogs) ነበሩት ፤ እነዚህን ውሾችም አገልጋዮቹን ‹አሽከሮቹን› ሲያጠፉ ለማሰቃዬትና ለማስበላት ይጠቀምባቸዋል፡፡

ከእለታት አንድ ቀን አንደኛው አሽከሩ ትክክል ያልሆነ ሃሳብ ንጉሱን ተናገረው ፤ በዚህም ምክንያት ንጉሱ እጅግ ተቆጣበት ፤ ወዲውኑም ወደ ውሾቹ እንዲወረወር ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡ አሽከሩም በሀዘን "አስር አመታት አገለገልኩህ ፤ ተገዛውልህ ያልከኝን ሁሉ አደረኩልህ ፤ አሁን ግን ይህንን አደረክብኝ ፤ እባክህ ወደ ውሾች ውስጥ ከመወርወሬ በፊት አስር ቀን ስጠኝ" ብሎ ተማጸነው፡፡ ንጉስም ተስማማ ‹ፈቀደለት›።

ይወረወር ዘንድ የተፈረደበት አሽከር ውሾቹን ወደሚንከባከበው ሌላኛው አሽከር ሔደና ‹እባክህ እነኝህን ውሾች ለአስር ቀን ልንከባከባቸው › ብሎ ጠየቀው፡፡ የውሾቹ ጠባቂም ግራ በመጋባት ሁኔታ ፈቀደለት ፡፡ የተፈቀደለት አሽከርም ውሾቹን መንከባከብ ጀመረ። ቆሻሻቸውን ማጸዳዳት ፤ ምግባቸውን በሰአቱ ማቅረብ ፤ ማጠብና አስፈላጊውን እንክብካቤ ሁሉ አደረገላቸው ፤ አስር ቀኑም አለቀ፡፡ ከዚያም በኋላ ከንጉስ ጋር በተነጋገሩት መሰረት …አሽከሩ ተጠርቶ ወደ ተናካሽ ውሾቹ ዘንድ ይወረወር ዘንድ አዘዘ ፤ ወረወሩትም ፡፡

ወርዋሪዎቹም ይህ አሽከር እንዴት በውሾቹ ሊበላ እንደሚችል እየዘገነናቸው መመልከት እንደጀመሩ ያላሰቡትን ሁኔታ በአይናቸው አዬ ፤ ንጉሱም በሚመለከተው ሁኔታ ግራ ተጋባና «በእነዚህ ተናካሽ ውሾቼ ላይ ምን ደረሰ ? ምንስ ገጠማቸው?» ማለት እንደጀመረ… የተወረወረው አገልጋይ በውሾቹ መሃል እየተሻሼ በኩራት እየተራመደ እንዲህ አለ "እነዚህን ውሾች ለአስር ቀናቶች ብቻ መገብኳቸው ተንከባከብኳቸው እነርሱም ያደረኩላቸውን በፍጹም አልዘነጉም ፤ አንተን ግን አስር አመት ሙሉ ተገዛሁልህ አገለገልኩህ ነገር ግን በአንዲት ጥፋት ምክንያት ሁሉንም ረሳህና ለሞት አሳልፈህ ሰጠኸኝ" አለው ፡፡ ንጉሱም ሁኔታውን ሁሉ በማስተዋልና ፤ ከውሾች እንዳነሰም በመገንዘብ አገልጋዬ ነጻ እንዲሆን አዘዘ ፤ ነጻም ሆነ፡፡

ይህ መልእክት ሰው በጣም ብዙ ውለታ ውሎላቸው ነገር ግን በአንድ ጥፋት ምክንያት የተደረገላቸውን ሁሉ እየረሱ በክፋት ለሚነሳሱ ሁሉ ይሁን፡፡ በመልካም ነገር የተሞላ ታሪክን ፤ በአንድ ስህተት ምክንያት ከንቱ አናድርግ፡፡

@maraki_lyrics
59 viewsedited  19:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 18:15:47 አሰላሙ አለይኩም የቻናሌ ቤተሰቦች
እንዴት ናችሁልኝ።እኔ እናንተን ለማስደሰት ብዬ እንቅልፍ ከማጣት ውጭ በጣጣጣጣም ደና ነኝ።እና ዛሬም እናንተን የሚያስተምርና የሚያዝናና ኢስላማዊ አደቡን የጠበቀ ምርጥ ቻናል ይዤላችሁ መጥቻለው።እና ምን ታስባላችሁ ተቀላቅላችሁ የደስታው ተካፋይ አትሆኑም
ከናንተ ሚጠበቀው Join ምትለዋን መጫን ብቻ ነው
72 views15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 11:02:06 ወዳጄ ሆይ...!
( ሙከረሙ)

...ምንም እንኳ ቢሆን
ውስጤ አልተዘናጋም ፣ ከመውደድ ወዳጁን

ግንስ እፈራለሁ ፣
የቅርቤ እንዳይርቀኝ
ጥቂቷ ኩርፊያ አድጋ
የኔ ካልኩት ሰው ጋር እንዳታቆራርጠኝ።

ወዳጄ ሆይ!
እንተወው ይቅርና ፣ እንሁን እንደ ፊቱ
ጭራሽ ለኛ አይበጅም ፣ ፍቅርን ማላላቱ
@maraki_layrics
71 viewsedited  08:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 14:44:30 ‍ የፋሱ ሌባ

ባለ ታሪኩ እንዲህ ይተርከዋል…
እንደ ወትሮው በንጋት ተነስቼ ወደ ስራዬ ለማምራት ፋሴን ወደ አስቀመጥኩበት ቦታ ሄድኩኝ። ፋሴ ግን ከቦታው ላይ አልነበረም። ገብቼ ወጣሁኝ, ፈላለኩኝ, ላገኘው አልቻልኩም።

እንግዲያውስ ሰው አንስቶታል ብዬ ከድምዳሜ ደረስኩኝ። ግን ፋሴን የሰረቀኝ ማን ነው

ሳስብ ከሚቀርበኝ ጎረቤቴ በስተቀር ወደ ቤቴ የገባ ሰው አልነበረም። ስለዚህ የፋሴ ሌባ ጎረቤቴ ነው ብዬ ጎረቤቴን ጠረጠርኩት።
ሌባው ጎረቤቴ መሆኑን ባምንም ግን እንዴት ብዬ ልጠይቀው የሆነ አጋጣሚ ላይ ጨዋታ ተመቻችቶልኝ ላፋጥጠው መጠባበቅ ጀመርኩኝ።

ከዝያ ቀን ጀምሮ
ሲያወራኝ እንደ ሌባ ነው ሚያወራኝ፤
አካሄዱ የሌባ ዐይነት አካሄድ ነው፤
ሁሉም እንቅስቃሴው የሌባ ዐይነት መስሎ እየታየኝ ነው።

ለመጠየቅ አጋጣሚው በመጠባበቅ ላይ ሳለሁ አንድ ነገር ትዝ አለኝ።
[የዝያ ምሽት ፋሱ ተጠቅሜበት ሌላ ቀን ከማስቀምጥበት ቦታ ሳይሆን ሌላ ቦታ አስምጬው ነበር።] ወደ ቦታው ሄጄ ሳረጋግጥ የተከበረው ፋሴ ካስቀመጥኩበት ቦታ ላይ አገኘሁት።

ችግራችን ታያችሁ ኣ
የሰዎች ማንነታቸው ሳናውቅ ወይም ሳንረዳ በፊት የራሳችን ግምት (ጥርጣሬ) እንሰጣቸዋለን። ከዝያ በኋላ…
የሚናገሩት፣
የሚሰሩት፣
የሚሄዱበት፣
አጠቃላይ እንቅስቃሴያቸው ቀድመን ከሰጠናቸው ጥርጣሬ ጋ እንዲገጥም እናስገድደዋለን [ባይሆንም የሆነ ይመስለናል]። በዚህም ምክንያት ብዙ ወንድሞቻችን ብዙ ወዳጆቻችን ለማጣት እንገደዳለን።

“ይመስለኛል፣ እጠረጥረዋለሁ፣ ፣ ፣” ከሚሉ የሩቅ ውርወራዎች ውጣና ቀርበህ ተመካከር። ልብህ ሁሌም ለወንድሞችህ ክፍት አድርግላቸው። ያስቀየሙህ ቢመስልህ እንኳ ከ“ይመስለኛል” ተላቀቅና ቀርበህ ጠይቃቸው

ሐምዱ ቋንጤ

@maraki_layrics
85 views11:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 21:52:04 ረመዳን ከሪም
#የዚህ ቻናል ዋነኛ አላማ
:- ኢስላማዊ ትምህርቶችን, ምክሮችን እና ታሪኮችን
አነቃቂ ፅሁፍ እና አነቃቂ ንግግሮችን
መፅሐፍትን
ጥቅስ እና አባባሎችን
ፍልስፍና , ሳይንስ እና ጠቅላላ ዕዉቀትን በማቅረብ መልካም ስብዕናን ዕዉቀትን እና በጎ አሰተሣሠብን መገንባት ነዉ!

ለ አስተያየት @Theonenu
ለ Cross @Theonenu
https://t.me/Islamkonolege
73 views18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 17:09:31 የሁለት ደቂቃ ንባብ

አትተርጉሙ!
አንድ አባት ከልጆቹ ጋር ወደ አንድ ካፌ ይገባል።ካፌው ውስጥ እንደገቡ ብዙም ሳይቀመጡ ልጆቹ መሯሯጥና እየተጯጯሁ መጫወት ይጀምራሉ።ይሄ ሁሉ ሲሆን አባት አንገቱን ደፍቶ በሀሳብ ጭልጥ ብሏል።ይሄን ሁሉ የሚመለከት አንድ ሰው በልጆቹ እንቅስቃሴ ተረብሾ ልጆቹን ስርአት የማያስይዝ ምን አይነት ቸልተኛ ሰው ነው እያለ በአባታቸውን ይናደዳል።በዚህ ብስጭት ውስጥ ሆኖ የሚሯሯጡት ልጆች ድንገት የእሱን ጠረጴዛ ነክተውት ኖሮ ያዘዘው ሻይ ልብሱ ላይ ተደፋ።ይሄን ጊዜ ንዴቱን መቋቋም አቅቶት ውደ አባትየው ሄደ።ለግጭት እየተጋበዘ ሊያንቀውም እየዳዳው”ምን አይነት የማትረባ ሰው ነህ?ልጆችህን ስርአት አታስይዝም?”ብሎ አምባረቀበት።አባትየው በረጅሙ ተንፍሶ በተረጋጋ አንደበት”ወዳጄ የልጅነት ሚስቴ የልጆቼ እናት ታማ ከምትረዳበት ሆስፒታል አሁን ከመግባታችን ተደውሎ መሞቷን ነገሩኝ።ምን ማድረግ እንዳለብኝና ለልጆቼ ምን እንደምል ግራ ገብቶኛል”አለው።ይሄን የሰማው ሰው በትልቅ ድንጋይ እንደተመታ ሰው ራሱን አመመው።

በህይወታችን ከምንሰራቸው ስህተቶች ውስጥ አንዱ ስለ ሁኔታዎች በቂ ግንዛቤ ሳይኖረን በራሳችን መተርጎምና መፈረጅ ነው።ሰዎች የሆነ ነገር ሲያደርጉ ስለማይወደኝ ነው፣ ስለማያከብረኝ ነው፣ ስልክ ሳያነሱ ወይ የሆነ ነገር ሲያደርጉ ሲቀሩ ደግሞ ሆም ብለው ነው ብለን በራሳችን እንተረጉማለን።የትርጉም ዋናው መዘዝ ከእውነታው አለም ያወጣንና የራሳችንን አለም እንደንፈጥር ያደርገናል።በህይወት ያሉትን ሰዎች እንገላቸውና ክፉ ናቸው አያከብሩኝም የምንላቸውን የራሳችንን ሰዎች በአዕምሯችን እንፈጥራለን።ሀሳባችንን ፊት ለፊት የመናገር ልምድ ስለሌለን በራሳችን ትርጉም በውስጣችንን እንበሰለሰላለን እንጎዳለን።መፍትሄው ምንድን ነው?

1.ምቾት ያልሰጡን ነገሮች ሲኖሩ በራሳችን ከመተርጎም ይልቅ ፊት ለፊት መጠየቅን እንለማመድ።

2.ያሰብኩትና የተሰማኝ ሁሉ ትክክል ነው ማለትን እናቁም።

3.ሰዎች በብዙ ችግርና ውስብስብ የህይወት መንገድ ያልፋሉና ለመረዳት እንሞክር።በዚህ መልኩ ጤናማ ግንኙነታችንን ማዳበር እንችላለን።

ማሕበራዊ ድረ-ገፅ

@maraki_layrics
82 viewsedited  14:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 15:35:50 ደራሲ ከበደ ሚካኤል [ የቀጠለ ]

ደራሲ ከበደ ሚካኤል በአምስት አመታቱ የጣሊያን የአገዛዝ ዘመን ግን ከበደ ልዑል መኮንንን ለማስተማር ከመጡት መምህራን አንደኛው ሚስተር ሊሞይን የተባለ አቋቁመውት በነበረው ቤተ መፃህፍት ውስጥ እየተቀመጡ ብዙ የማንበብ ዕድል ስላጋጠማቸው ያ ዘመን በተደጋጋሚ አነበቧችው ተበለው ከተጠቀሱት መፅሃፍት አንደኛው ናፖሊዮን የተባለው መፅሃፍ ነው፡፡

ከንባቡ ጐን ለጐንም የጣለያንኛ ቋንቋን በሚገባ ተማሩ፡፡ ቋንቋን በተመለከተ ከበደ ሚካኤል ልሣነ ብዙ፡ ከሚባሉ ደራሲዎች አንዱ ናቸው፡፡ ከአገራቸው አማርኛና ግዕዝ ቋንቋዎችን ከውጭ ደግሞ ፈረንሣይኛን፣ ጣሊያንኛንና አንግሊዘኛ ቋንቋዎችን ጠንቅቀው ያውቁ እንደነበር የተረጋገጠ ነው፡፡

በሁሉም ቋንቋዎች የሚያገኙትን መፅሃፍት ታዲያ ለማንበብ አይቦዝኑም፡፡ ለከበደ ሚካኤል እንደ እጅ ማሟሻና እንደመጀመሪያ የሚቆጠረው ድርሰታቸው ብርሃነ ህሊና የተባለው ሲሆን የተጻፈው በጣሊያን ዘመን ነው፡፡ በኋላ የቅኔ ውበት በተባለው መፅሐፋቸው ከተካተቱት ስብስቦች አንደኛው በመሆን በተደጋጋሚ ታትሟል፡፡ ከበደ ሚካኤል ጠላት ከተባረረም በኋላ የድርሰት ሙያን እላቋረጡም፡፡

ከ1933 እስከ 1966 ዓም፡ በጋዜጠኝነት፣ በትምህርት ሚኒስቴር ውስጥ በኢንስፔክተርነትና በምክትል ጻይሬክተርነት፡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት በተርጓሚነትና በፀሐፊነት፣ በብሂራዊ ቤተመፅሃፍት ወመዘክር በዳሬክተርነት፡ እንደገና በትምህርት ሚኒስቴር በዳሬክተርነት፣ በንጉሠ፡ነገሥቱ ካቢኒ ከምክትል ሚኒስትርነት ማዕረግ የዜና ማደራጃ ኃላፊ እና በኋላም ሚኒስትር ሆነው ባገለገሉባቸው እጋጣሚዎች ሁሉ የድርሰት ሙያን አላቋረጠም።

በነዚህ የሥራ ዘመናት በርከት ያሉ መጽሃፍትን አሳትመዋል። ብዙዎቹ መፅሃፍቶቻቸወ፡ አራት ጊዜና ከዚያም በላይ እየተደጋገሙ ለመታተም በቅተዋል፡፡ በድርሰት ሥራዎቻቸው ትርጉሞች እና ወጥ ድርሰቶች ተውኔቶችና ግጥሞች የተካተቱ ሲሆን አሁን ድረስ ተወዳጆች ናቸው፡፡

ከበደ ሚካኤል ለመጀመሪያ ጊዜ እንግሊዛዊውን የተውኔት ደራሲ ሼክስፒርን ለኢትዮጵያ ተደራሲ ያስተዋወቁ በመሆናቸው የተለየ ሥፍራ አላቸው፡፡

ከበደ ሚካኤል በተደጋጋሚ ከአሳተሟቸውና በአንባቢውም ዘንድ ተወዳጅ ከነበሩ ድርስቶቻቸው መካከል የሚከተሉት በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ፡፡
 
የዶ/ር ደራሲ ከበደ ሚካኤል ሥራዎች

1.  የእውቀት ብልጭታ(ትምህርት)
2.  የመዠመሪያ እርምጃ(ትምህርት)
3.  ታሪክና ምሳሌ ፪ኛው(ትምህርት)
4.  ታላላቅ ሰዎች(ትምህርት)
5.  የዓለም ታሪክ ፩ኛ ክፍል(ትምህርት)
6.  ብርሃነ ሕሊና(ግጥምና ቅኔ)
7.  የቅኔ አዝመራ(ግጥምና ቅኔ)
8.  የቅኔ ውበት(ግጥምና ቅኔ)
9.  ጃፓን እንዴት ሰለጠነች(ትምህርት)
10.  የትንቢት ቀጠሮ(ተውኔት)
11.  አኒባል(ተውኔት)
12.  በላይነህ/ የቅጣት ማዕበል(ተውኔት)
13.  ካሌብ(ተውኔት)
14.  አክዐብ(ተውኔት)
15.  ቅዱስ ገብርኤል በምድረ ገነት(ተውኔት)
16.ትልቁ እስክንድር
17. ከይቅርታ በላይ
18. የሥልጣኔ አየር
19. የልዑል መኮንን ታሪክና መታሰቢያ በሥዕል
20. የድርሰት ትንሣኤ
21. ግርማዊነታቸው በአሜሪካን አገር
22. ኢትዮጵያና ምዕራባዊ ሥልጣኔ
23. ሥልጣኔ ማለት ምንድነች? ይገኙባቸዋል፡፡

ከላይ ከተጠቀሱት አንዳንዶቹ በስብስብ መልከ በድጋሚ የተጻፉ አሉ፡፡ ለምሣሌ የቅኔ ውበት የሚለው መፅሃፍ የስብስቦች መጠሪያ እንጂ በራሱ የተለየ ድርሰት አይደለም።

ከበደ ለዚህ ሁሉ ሥራቸው የተለያዩ ሽልማቶችን እግኝተዋል፡፡ በ1957 ዓ ም በአማርኛ ስነ ፅሁፍ የመጀመሪያው የቀዳማዊ ኃይለስላሴ ሽልማት ድርጅት ተሽላሚ ለመሆን በቅተዋል፡፡ በ1990 ዓ.ል ደግሞ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ከአዲስ አበባ ዩኒሽርስቲ ተቀብለዋል፡፡

በ1991 ዓ.ል በተወለዱ በ84 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ:

ከበደ ሚካኤል ከ1966 ዓ.ል ለውጥ በኋላ ብዙ ችግሮች ደርሰዉባቸዋል። የሰሩት ቤት በመወረሱ አብዛኛዉን ኑሯቸውን የገፉት አውራሪስ እና ቱሪስት በተባሉ ሆቴሎች ውስጥ ነዉ: “አምሮቸዉ ንክ ሆኗል” እያሉ በሚያስወሩባቸው ወገኖች አማካኝነትም የመገለል ችግር አጋጥሟቸው እንደ ነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ።

የወታደራዊ ደርግ ባለስልጣናት በደራሲነት ለአገራቸው ያበረከቱትን የስነ ጽሁፍ ስራ ከመመልከት ይልቅ የወደቀዉን ስርዐት ግብረበላ ነበሩ ከሚል ድምዳሜ ላይ በመድረሳቸው ቤታቸዉን በቀበሌ ታጣቂዎች ካለአግባብ መነጠቃቸውን እና በችግር ላይ መሆናቸውን እያወቁ አንዳችም መፍትሄ ሳይሰጧቸው አንደቀሩ በቁጭት የሚያስረዱ ወገኖች አሉ። አንዳንድ የደራሲ ከበደ ሚካኤል መጽሃፎች አሁንም ታትመው በገበያ ላይ ይገኛሉ ።

ተፈፀመ @maraki_layrics
101 views12:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 15:32:14 ደራሲ ከበደ ሚካኤል ማናቸው ታዋቂ ስራቸውስ?

የደራሲ ከበደ ሚካኤልን የትውልድ ዘመን በተመለከተ ሁለት ዓይነት ዘገባዎች አሉ፡፡  በደራሲ ከበደ ሚካኤል የህይወት ታሪክ እና ስራዎቻቸው ላይ በመመሥረት በ1976 ዓ.ም የመመረቂያ ፅሑፉን የጻፈው ደራሲ አስፋው አፅምአት የትውልድ ዘመናቸው በህዳር ወር 1907 ዓ.ል መሆኑን አስፍሯል፡፡

ከዚህ በፊት በመስከረም ወር 1973 ዓ.ም ታትሞ ከወጣዉ "የካቲት” መፅሄት ላይ በተዘዋዋሪ እንደተገለጸው የደራሲ ከበደ ሚካኤል የትውልድ ዘመን 1908 ዓ.ም ነው፡፡

ደራሲ ከበደ ሚካኤል ከ1907 እስከ 1908 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ከአባታቸው ከአቶ አይታገድ እና ከእናታቸው አወ/ሮ አፀደ ሚካኤል ሰሜን ሸዋ በጥንታዊቷ መናገሻ አንኮበር ከተማ ተወለዱ።

በተወለዱበት ዘመን አባታቸው አካባቢውን ለቀው በመሄዳቸውና ሳይመለሱም በመቅረታቸው ከበደ በእናታቸው አባት ስም መጠራት ቀጠሉ፡፡

ብላክ ላየንስ (ጥቋቁር እናብስትን) በሚለው የሞልሺየር መፅሃፍ እንደተገለፀው ከበደ ሚካኤል የአራት ዓመት ልጅ እንደሆኑ ወ/ሮ ወለተ ገብርኤል ከተባሉት የሴት አያታቸው ጋር ተቀምጠው ገርብ ገብርኤል በተስኘው ቤተ ክርስቲያን ትምህርታቸውን ጀመሩ፡፡

ከበደ ሚካኤል አንድ ብለው ትምህርት የጀመሩበትን ቤተ ክርስቲያን ያሰሩት ከአያት ቅድመ አያታቸው አንዱ የነበሩት ደጃዝማች መኩሪያ መሆናቸው በታሪካቸው ውስጥ ተፅፏል፡፡

በ1917 ዓ.ል አካባቢ የከበደ ሚካኤል እናትና አያታቸው ወደ አርሲ ለኑሮ ሲሄዱ እላቸው አዲስ አበባ በሚገኘው የካቶሊክ ካቴድራል ትምህርት ቤት በአዳሪነት ገቡ፡፡

በ1922  እናታቸው ከአርሲ ወደ አዲስ አበባ ለመምጣት በመቻላቸው የ14 ዓመቱ አበደ ከእናታቸው ጋር እየኖሩ ትምህርታቸውን ቀጠሉ፡፡

በመሃሉ በአሊያንስ ፍራንሲስ ትምህርት ቤት የነበሩ መምህራን መማታት ያበዙ ስለነበር በዚህ ተማርረው ወደ ላዘሪስት ሚሲዮን ትምህርት ቤት ተዛወሩ፡፡

ቆይቶ ግን ሁኔታዎች በመሻሻላቸው፡ ወደ ቀድሞ ትምህርት ቤታቸው ተመለሱ፡፡ ወደ አሊያንስ ፍራንሲስ ትምህርት ቤት እንደገና ተመልሰው ሶስት ዓመታትን ያህል እንደቆዩ የስነ ጽሑፍ ሙያን በትምህርት ቤቱ ዳይሬክትር አማካኝነት የመማር እድል አጋጠማቸው፡፡

የሊባኖስ ዜግነት ያላቸው ማልሃቢ የተባሉት የትምህርት ቤቱ ርዕሠ መምህር፡ እራሳቸው የልቦለድ ድርሰት ፀሐፊ ስለነበሩ ይህንኑ ሙያ ለመረጧቸው ስድስት ተማሪዎቻቸው ለማሳወቅ በግል መኖሪያቸው ማስተማር በጀመሩ ጊዜ ከበደ ሚካኤል አንደኛው የዕድሉ ተጠቃሚ ሆኑ።

ትምህርቱ ይሰጥ የነበረው በፈረንሣይኛ ቋንቋ ሲሆን ከበደ እጅግ ሲበዛ ጎበዝና ታታሪ ሆነው ተገኙ፡፡ በዚህም የተነሳ የትምህርት ቤቱ ኃላፊዎች ከበደ ወደ ፈረንሳይ አገር ሄደው  የከፍተኛ ትምህርታቸውን አንዲቀጥሉ ይደረግ ዘንድ ለቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ጥያቄ አቀረቡ፡፡

ያን ጊዜ የተወሰኑ ተማሪዎች ከኢትዮጵያ እየወጡ ትምህርታችውን በውጭ አገር የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መማር የጀመሩበት ጊዜ ስለነበር ንጉሠ-ነገሥቱ ከበደ ሚካኤልን በተመለከተ የቀረበላቸውን ጥያቄ ያለማቅማማት ተቀበሉት፡፡

ከእሳቸው ጋር የተመረጡት ተማሪዎች ወደ ውጭ እንዲሄዱ በተዘጋጀበት ጊዜ ግን እንደ አጋጣሚ ሆነና ከበደ በጠና ታመው ቀሩ፡፡ ጤናቸው መሻሻል አንጻሳየ ሁለት መምህራን ወጣቱን ልዑል መኮንን ኃይለሥላሴን ለማስተማር ከፈረንሣይ አገር መጡ፡፡

በቤተ መንግሥት ኃላፊዎች መካከል ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ የሆነ ሶስተኛ መምህር መጨመር እንዳለበት ስምምነት ላይ በመደረሱ ከህመማቸው እያገገሙ የመጡት ከበደ ሚካኤል ለዚህ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ ተመረጡ፡፡

ከበደ የልዑል መኮንን ሶስተኛ መምህር ሆነው የተመረጡት ወደ ውጭ አገር ለትምህርት እስኪሄዱ ጊዜ ነበር፡፡ ብዙም ሳይቆይ ግን 1928 ዓም ደረስና የማይጨው ዘመቻ ታወጀ፡፡ ሁሉም ነገር የጣሊያንን ወረራ በመመከት ላይ በማተኮሩ የከበደ ሚካኤል ወደውጭ አገር ሄዶ የመማር ዕድል በዚያው ተሰናክሎ ቀረ፡፡

ይቀጥላል....@maraki_layrics
81 viewsedited  12:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 20:53:26 .....እኛ ሰዎች ድንቅ ሆነን የተፈጠርነው፣ ድንቅ ሆነን በመገኘት፣ ድንቅ ሕይወት ለመኖር ነው።
ታድያ ለምንድን ነው ብዙ ሰው ድንቅ ማንነቱን ትቶ፣ ተራ ሆኖ በመገኘት ተራ ሕይወት የሚኖረው?.....
ምክንያቱም ተራ መሆን በጣም ቀላል ስለሆነ ነው።
ድንቅ መሆን ቀላል ነገር አይደለም፤
በነጻም አይገኝም፤
ዋጋ ያስከፍላል፤
መሥዋትነትም ይጠይቃል።
ተራ ሰው ልክ እንደ ድንቅ ሰው ሁሉ ድንቅ ሕይወት መኖር ይፈልጋል። ነገር ግን ለድንቅነት የሚከፈለውን ዋጋ መክፈል አይፈልግም።
ተራ ሰው ድንቅ መሆን ይጀምራል፤ ከዚያም ትንሽ ከበድ ሲለው ተስፋ ይቆርጣል፤ ወደ ተራ ሕይወቱም ይመለሳል።
/ከትልቅ ህልም አለኝ ገፆች/
ድንቅ እንሁን ድንቅ እናድርግ
እርሱ ነውና የሰውነታችን ልክ።
የድንቅነት ምሽት ተመኘሁ!!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ !!!
96 views17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 14:27:04 ከዕለታት በአንደኛው ቀን ሰራተኞች ቢሮ ሲገቡ ከመግቢያ በሩ ላይ የተጻፈ ማሳሰቢያ ቢጤ ይመለከታሉ።
"በካምፓኒው ውስጥ እድገታችሁን ሲያደናቅፍ የነበረው ግለሰብ በትናንትናው ዕለት ስላረፈ በስርዓተ-ቀብሩ ላይ እንድትቀላቀሉን እንጋብዛችኋለን" ይላል። የመስሪያ ቤት የስራ ባልደረባቸው ስላረፈ ብዙሃኑ ሰራተኞች አዘኑ። ዳሩ ግን ቢከፉም ሁሉም ተደነቁ። "ምንም እንኳን ቢሞትም እድገቴን ሲያደናቅፍ የነበረው ሰውዬ ግን ማን ነበር?" ሲሉ አሰቡ። ለማየትም ጓግተው አንድ በአንድ ከሬሳ ሳጥኑ እየቀረቡ ቢመለከቱ ድንገት የሚናገሩት ቃል ጠፋቸው። አልጠበቁም። ሌላ ሰው ጥልቅ ስሜታቸውን የነካ ይመስል ከሬሳ ሳጥኑ አጠገብ ቆመው ፈዘው ዝም አሉ። የሬሳ ሳጥኑ ከውስጡ መስታውት ቢሆን እንጂ አንዳችም ነገር አልነበረውም።
ሁሉም ወደ ውስጥ ቢመለከቱ፣ ያዩት የራሳቸውን ምስል ብቻ ነው። ከመስታውቱ አጠገብ አንድ ጥቆማ ሰፍሯል።

"ስኬትህን የመገደብ ብቃት ያለው አንድ ግለሰብ አለ። እሱም እራስህ ነህ።" ይላል!

@maraki_layrics
101 views11:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ