2022-06-27 14:53:22
በአንድ ወቅት የተከሰተ እውነተኛ ገጠመኝ
የተከፈለ ውለታ
አሜሪካን ካንሳስ ሲቲ ነዋሪ የሆነችው ሳራ ዳርሊንግ ከስራ ወጥታ ወደ መኖሪያዋ በማቅናት ላይ ሳለች አንድ በዕድሜ ጠና ያሉ አዛውንት ከመንገድ ዳር ቁጭ ብሎ ሲለምን ትመለከታለች።
ሳራ ወደ አዛውንቱ በመጠጋት ቦርሳዋን ከፍታ የተወሰኑ ዶላሮችን በማውጣት ሰውየው ከጎኑ ባስቀመጠው የፕላስቲክ ኩባያ ውስጥ አኑራ ጉዞዋን ትቀጥላለች።
ሳራ ከምንግዜውም በላይ በህይወቷ ደስተኛ ነበረች ከምትወደውና ከምታፈቅረው ጓደኛዋ ጋር በትዳር ለመጣመር የቀናት ዕድሜ ቀርቷቸዋል።
ለእሷ ከፍተኛ ክብርና ፍቅር ያለው ፍቅረኛዋ እጅግ ውድ የሆነ ዳይመንድ የቃል ኪዳን ቀለበት ገዝቶ በጉልበቱ ተንበርክኮ የታገቢኛለሽ ጥያቄ ካቀረበላት እና በደስታ እሺ ካለችው ጊዜ አንስቶ ህይወቷ በሀሴት ተሞልቷል።
ምሽት ላይ እንደተለመደው በስስት የምታየውን የዳይመንድ ቀለበት ስማ ለመተኛት ቦርሳዋን ከፈተችው በድንጋጤ ደርቃ ቀረች ቀለበቱ በቦታው አልነበረም።
ቦርሳዋን የከፈተችው መንገድ ዳር ቁጭ ብሎ ለሚለምነው አዛውንት ገንዘብ ለመስጠት ብቻ እንደነበር አስታውሳ የሰውየው ገንዘብ መሰብሰቢያ ኩባያ ውስጥ ቀለበቱን አብራ ማኖሯን አስታወሰች።
ለእጮኛዋ ስልክ በመደወል ሁኔታውን አጫወተችው እጮኛዋም ሲከንፍ መጣ
ተያይዘው በልመና ወደ ሚተዳደረው ሽማግሌ ቦታ ሄዱ። ሰውየው በቦታው አልነበረም "በእርግጥ ውድ የሆነ ቀለበት አግኝቶ እንዴት ተመልሶ በቦታው ሊቀመጥ ይችላል" የእጮኛዋ ግምት ነበር።
በቀጣዩ ቀንም በተመሳሳይ ከእጮኛዋ ጋር ሽማግሌው ተቀምጦ ወደ ሚለምንበት ቦታ ሄዱ አሁንም ሰውየው አልነበረም። በቃ ጦስሽን ይውሰድ ከእንግዲህ እርምሽን አውጪ ነበር የእጮኛዋ መልስ። በሦስተኛው ቀንም ሳራ ለእጮኛዋ ደውላ ወደ ሽማግሌው ቦታ እንዲሄዱ ጠየቀችው እጮኛዋ በመገረም "6 ሺህ ዶላር የሚያወጣ ቀለበት ችግረኛ እና በረንዳ የሚያድር ሰው እጅ ገብቶ አገኘዋለሁ ብለሽ እንዴት ታስቢያለሽ?" ነበር ያላት... ሳራም በቃ የዛሬን ብቻ እንየው ሰውየው ከሌለ እርሜን አወጣለሁ አለችው።
እጮኛዋም የሳራን ፍላጎት ለመሙላት ተስማምቶ ጉዞዋቸውን አቀኑ ሽማግሌው በቦታው ተቀምጦ ሲለምን አገኙት
ሳራ በደስታ ተዋጠች አላውቅሽም ብሎ እንዳይሸመጥጠኝ የሚል ስጋት እንደዋጣት ወደ ሽማግሌው ተጠጋች።
አባት ያስታውሱኛል? በማለት ጠየቀች። ሽማግሌው ቢል ሬይ ሀሪስ ይባላል ቀና ብሎ ተመልክቷት አላወቅኩሽም ልጄ ሲል መለሰላት።
ሳራም ከ3 ቀን በፊት ከቦርሳዬ ገንዘብ አውጥቼ ሳስቀምጥ ሌላ ዕቃ አብሬ አኑሬ ነበር?!
የጣት ቀለበት ነው?
አዎን አባት…
ቢል ቀለበቱን ጠቅልሎ ካስቀመጠበት ኪሱ በማውጣት አንድ ቀን እንደምትመለሺ አውቅ ነበር በማለት ከሰጣት ብኋላ... ቀለበቱን ያገኘሁት ዕለት ትክክለኛ ወይም አርቴፊሻል ቀለበት መሆኑን ለማወቅ ወደ ጌጣጌጥ ሱቅ ወስጄው ነበር እነሱም ትክክለኛ መሆኑን ነግረው $4,000 ዶላር ሊገዙኝ ጠይቀውኝ ነበር።
በእርግጥ ኑሮውን በበረንዳ ለሚያሳልፍና በልመና ለሚተዳደር 4ሺህ ዶላር ከፍተኛ ገንዘብ ነው። ነገር ግን እኔን ለመርዳት ብላ በስህተት ቀለበት የጣለችን ሴት ንብረት መንካት አልፈለግኩም። በመሆኑም በጥንቃቄ አኑሬው የአንቺን መምጣት ስጠባበቅ ነበር ሲል መለሰላት።
ሳራ ዳርሊንግ እና እጮኛዋ የመልካሙን ቢል ሬይ ሀሪስ ታሪክ ቀለበቷን ሲሰጣት ከሚታይ ምስል ጋር በማያያዝ ለሶሻል ሚዲያ (Facebook) አበቁት። ከታሪኩም ጎን ለጎን የእርዳታ ማሰባሰቢያ ጎፈንድሚ አካውንት ከፈቱ በቢል ሬይ ቀናነት እጅጉን የተደሰቱ አያሌ ግለሶቦች የዕርዳታ እጃቸውን ይዘረጉ ጀመር በአጭር ጊዜ ውስጥ 260,000$ ዶላር ተሰበሰበለት።
በአሁን ሰዓት ቢል ከበረንዳ አዳሪነት ወጥቶ የቤት ባለቤት ሆነ ተጨማሪ የመጦሪያ ገንዘብም አገኘ።
መልካምነት መልሶ ይከፍላል።
@maraki_layrics
97 views11:53