Get Mystery Box with random crypto!

(2ኛ ኮርስ - ነገረ ሃይማኖት) #በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን | ማኅበረ ቅዱሳን (Mahibere Kidusan)

(2ኛ ኮርስ - ነገረ ሃይማኖት)

#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን

የቀጠለ.......
__
#በገነት_ውስጥ_ስለ_በቀሉት_ዕፅዋት
እግዚአብሔር አምላካ
ን በገነት ውስጥ (ለአዳም) ሦስት ዓይነት ዕፅዋትን ፈጥሮለታል፡፡
አንዱ - የሚመገበው
ሁለተኛው - የሚጠብቀው - ዕፀ በለስ
ሦስተኛው ደግሞ የሚታደስበት - ዕፀ ሕይወት ነው
እስኪ በጥቂቱም ቢኾን ስለ እነዚህ ዕፅዋት እና ስለ አዳም እንመልከት፡-


#እንዲመገባቸው_የተሰጡት_ዕፅዋት
ሰው ወዳጁ እግዚአብሔር በገነት ውስጥ ታላላቅና ታናናሽ ዕፅዋትን ያበቀለ ሲኾን ታናናሹ ብቻ ቅጠላቸው ዐሥራ ኹለት ዐሥራ ኹለት ክንድ ያክላል፡፡ እንደ ኮከብም ያበራል፡፡ ፍሬአቸውም ክብ ነው፡፡ ዛሬ እነዚህን ዕፅዋት የሚመገቡት በብሔር ብጹዓን ያሉ ጻድቃን ቅዱሳንና በገነት ያሉ አዕዋፍ ናቸው፡፡ የሚያመጣላቸውም ነፋስ ነው፤ ነፋሱ እንደ ዝናብ ያዘንብላቸዋል፡፡ ያን ተመግበውም ፈጣሪያቸውን ሲያመሰግኑ ይኖራሉ /ገድለ ዞሲማስ/፡፡



#ዕፀ_ሕይወት
አበው እንደሚነግሩን ዕፀ ሕይወት ጫፏ ከሰማይ ይደርሳል፡፡ ፍሬዋ እንደ ሮማን ፍሬ ተነባብሮ ከእግር እስከ ራሷ ምሉ ነው፡፡

ከዕፀ ሕይወት ፍሬ አንዲቱን ቆርጦ በአፉ ጎርሶ አላምጦ ሳይውጣት እንደ ቀድሞው ፍሬ ተክታ ትገኛለች። /ሕዝ.47፡12-13፣ ራእ.22፡2-3/፡፡

ከዕፀ ሕይወት አንዲቱን ፍሬ በበሏት ጊዜ ጣዕሙ ከአፍ፣ መዓዛው ከአፍንጫ ሳይለይ እስከ ሰባት ቀን ይቀመጣል (ኄኖ 7፥6-16)
ከዚህች ዕፅ የቀመሱ ሰዎች “እንዲህ ያለውስ ምግብ ያለ እግዚአብሔር ቸርነት ለፍጡር አይገባውም ነበር” እያሉ ያደንቃሉ፡፡ ቅጠሏ፣ አበባዋ፣ ፍሬዋ ያለ ደዌ ያለ ሕማም ነፍስን ከሥጋ ይለያል፡፡

እግዚአብሔር አምላካችን ዕፀ ሕይወትን ብላም አትብላም አላለውም፡፡ ይህ ለምን እንደ ኾነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሲመልስልን እንዲህ ይለናል፡-
“አዳም ቢፈልግ ኖሮ ይህን ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚሰጠውን ዛፍ ከሌሎች ዛፎች ጋር አብሮ መብላት ይችል ነበር፤ በመኾኑም ስለ ዕፀ ሕይወት ብላም አትብላም አላለውም፡፡”
ከዚህ መረዳት እንደምንችለው የሰው ልጅ (አዳም) የራሱ የኾነ ነጻ ፈቃድ አለው፡፡ ይህ ነጻ ፈቃዱ እንኳንስ ዲያብሎስ እግዚአብሔርም ቢኾን ጣልቃ የሚገባበት አይደለም፤ ሰው ራሱ እንደ ውዴታው የሚያዘው እንጂ፡፡ በመኾኑም በዚህ ነጻ ፈቃዱ ከፈለገ ይህን ዕፀ ሕይወት በልቶ ለዘለዓለም መኖር ይችል ነበር፡፡ ውሳኔው ለራሱ ለአዳም የተተወውም ስለዚሁ ነው፡፡

መረዳት ያለብን ግን ዕፀ ሕይወት ሲባል ዕፁ በራሱ ሕይወትን የሚሰጥ ነው ለማለት አይደለም፡፡ ዕፁ የመታዘዝ ምልክት ነው፤ እግዚአብሔርን ቢታዘዝና እንደ ሕጉ ቢኖር ይህቺን ዕፅ በልቶ ይታደስ ነበር፡፡

ይታደስ ነበር ሲባል የሰው ልጅ በመዋቲነትና በኢመዋቲነት መካከል ኾኖ ተፈጥሮ ስለ ነበር ወደ ኢመዋቲነት ይሸጋገር ነበር ማለት ነው፡፡ በበደለ ጊዜ ይህቺን ዕፀ ሕይወት እንዳይበላ መከልከሉም ስለዚሁ ነው፡፡ ምክንያቱም ከበደሉ ሳይነጻ ይህቺን ዕፅ ቢበላ ኖሮ ለዘለዓለም እየበደለ ነበር የሚኖረው፡፡ በበደሉ ምክንያት የመጣበት ጉስቁልና ለዘለዓለም አብሮት ነበር የሚኖረው፡፡ እንደ ዲያቢሎስ አመፀኛና እርጉም ሁኖ ይቀር ነበር።

ሰው ወዳጁ እግዚአብሔር ግን መጀመሪያ ሞቱንና ጉስቁልናዉን አስወግዶ ወደ ቀድሞ ቦታው ወደ ገነት ወደ ቀድሞ ክብሩ ወደ ልጅነት ይመልሰው ዘንድ ከገነት እንዲወጣና ከዚህች ዕፅ እንዳይበላ አደረገው፡፡

ዛሬ ይህ ዕፀ ሕይወት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ኾኖ ተሰጥቶናል /የሐሙስ ውዳሴ ማርያም/፡፡
~~~~

ቀጣይ ትምህርታችን
ስለ ዕፀ በለስ
#ወስብሐት ለእግዚአብሔር _ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!

@mahiberekidusan
@mahiberekidusan
@mahiberekidusan
❸➒