Get Mystery Box with random crypto!

(2ኛ ኮርስ - ነገረ ሃይማኖት) #በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን | ማኅበረ ቅዱሳን (Mahibere Kidusan)

(2ኛ ኮርስ - ነገረ ሃይማኖት)

#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን

የቀጠለ......
__
, ዓለማተ ማይ/ውሃ፦ ዓለማተ ውሀ በአራት የተከፈሉ
ሲሆኑ በዝርዝር እንያቸው
1ኛ, ሐኖስ፦ ሐኖስ ከኤረር በታች የሚገኝ ውሃ ነው በዚህ አለም ላይ ምንም ፍጥረት አይገኝም ውሃው እንዳይፈስ ባቢል የሚባል ንፋስ ተሸክሞታል። የሐኖስ ስፋቱ በምድር ልክ ነው። ሐኖስ ከምድር ዳርቻ ካለው ውሃ ጋር በጠፈር ይገናኛል።

2ኛ, ጠፈር፦ ጠፈር ከሐኖስ በታች ከውቅያኖስ በላይ ያለ የውሐ ዓለም ነው። ውሃውም የረጋ ነው። ይህንን የውሃ ዓለም የብርሃናት መመላለሻ የዓይን ማረፊያ አድርጎ ፈጥሮታል። በጠፈርም ምንም ሕይወት ያለው ፍጥረት የለም።


3ኛ,በምድር ዙሪያ ያለው ውቅያኖስ ነው። ውቅያኖስ በምድር ዙሪያ ሙሉ ነው ከውቅያኖስ በኋላ ደረቅ ምድር የለም ዝናብም የሚዘንበው ከውቅያኖስ ተቀድቶ ነው በዚህም አስደናቂ ፍጡራን ይኖራሉ እግዚአብሔር በሁለቱ ፍጥረታት ምድርን አጥሯል እነሱም ብሔሞትና ሌዋታን የሚባሉ የዘንዶ ዘሮች ላም መሰል ናቸው።

ብሔሞት እና ሌዋታን ዓለምን እንደ ቀለበት የጠመጠሙ ናቸው መንቀሳቀስ አይችሉም ከውሃ ውስጥ የተፈጠሩ ግን በየብስ ሚኖሩ የሐሙስ ፍጥረት ናቸው።

ብሔሞት፦ ግሩማን አራዊት/ የአራዊት ራስ/ የፍጥረት ቀንድ የሌዋታን ወንድም ነው።
ከአፉ ፋና፤ ከአፍንጫው ጢስ ይወጣል እጢስታው ብልጭታ ያመጣል።

ብሔሞት ዮርዳኖስን ጠጥቶ የማይጠግብ በቀን 1,000 ዝሆን መመገብ የሚችል ነው።
ግን በእግዚአብሔር ፍቃድ ማርና ወተት እየተመገቡ ይኖራሉ።

ሌዋታን፦ አንእስት የብሔሞት ጣምራ አብራው የተፈጠረች ናት
ብሔሞት በስተቀኝ ሌዋታን በስተግራ ተቀምጠዋል።

መገኛቸው በገነት በምስራቅ በኩል ባለ ዴንዳይን በሚባል ምድረ በዳ ነው። (ሄኖ 16፥14)
እነዚህን የተለዩ ፍጥረታት በቅድስና 10ኛው ደረጃ የደረሰ ሰው ማየት ይችላል።
አቡነ ዘርዓብሩክም ጥርሳቸውን ቆጥረው መምጣት ችለዋል።

እነዚህ እንሰሳት የእግዚአብሔር ፍጥረት አውራ ናቸው እግዚአብሔር አይቶም ይደሰትባቸዋል።


ከዚህ በተጨማሪም ካልህ የተባለ ፍጥረት ይገኛል።

ካልህ ከወገቡ በላይ የሰው መልክ ያለው ከወገቡ በታች ደግሞ የአራዊት መልክ ያለው ፍጡር ነው ወይም ደግሞ ከወገቡ በላይ የአራዊት ከወገቡ በታች የሰው መልክ ያለው ሊሆን ይችላል።


4ኛ, ከምድር በታች ምድርን የተሸከመው ውሃ ነው። ይህ ውሃ በእሳትና በመሬት ዓለማት መካከል ይገኛል። ከምድር በታች ባለው ውሃ ፍጥረታት አይኖሩም እስከ ምፅዓት ድረስ ምድርን ተሸክሞ ይኖራል።

, ዓለማተ ነፋስ/የነፋስ ዓለም፦ ዓለማተ ነፋስ በሁለት ይከፈላሉ።
1ኛ, ባቢል፦ ባቢል
ከጠፈር በላይ ያለውን የውሃ ዓለም ሐኖስን ተሸክሞ እስከ ምፅዓት ይኖራል። ባቢል አይንቀሳቀስም። ምክንያቱም ሐኖስ የተባለውን የውሃ ዓለም እንዳይፈስ ተሸክሟልና በዚህ ዓለም ፍጥረታት አይኖሩም።

2ኛ, ከምድር በታች ያለው እሳትን የተሸከመው ነፋሳ ነው ይህ ንፋስ እስከ ምፅዓት ድረስ ዓለመ እሳትን ተሸክሞ የኖራል። ይህ ዓለመ ነፋስ በ12 ይከፈላል። 4ቱ የምህረት ንፋሳት እና 8ቱ የማአት ንፋሳት ተብለው ይጠራሉ።
4ቱ የምህረት ነፋሳት በዝች አለም ፍጥረታትን ያገለግላሉ 8ቱ የማአት ንፋሳት እግዚአብሔር ሲቆጣ መሬትን የሚያገላብጡና በዕለተ ምፅዓት ዓለማትን ሁሉ የሚደመስሱ ናቸው።
~~~~

ቀጣይ ትምህርታችን
በገነት ስለ ነበሩት ጠቅላላ ዕፀ በለስ
#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!

@mahiberekidusan
@mahiberekidusan
@mahiberekidusan

❸➑