Get Mystery Box with random crypto!

/2ኛ ኮርስ - ነገረ ሃይማኖት/ #በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን | ማኅበረ ቅዱሳን (Mahibere Kidusan)

/2ኛ ኮርስ - ነገረ ሃይማኖት/

#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን

#የቀጠለ.......
__
#ዕፀ_በለስ
ይህቺ ዕፅ እግ
ዚአብሔር በገነት በምዕራብ በኩል የተከላት ሲሆን አዳምና ሔዋን እንዳይበሏት የከለከላቸው ብቸኛይቱ ዕፅ ነች፡፡
እንዳይበሏት ሲከለከሉ እንኳን ሔዋን ራሷ እንደ ተናገረችው ነፍጓቸው ወይም ተመቅኝቶዋቸው ሳይኾን፦

አንደኛ) ስለ ፍቅሩ ለፈጠረው ለእግዚአብሔር በፍቅር በመታዘዝ እንዲመልስ

ሁለተኛ) ፍጡርነቱን እንዲያውቅባት

ሦስተኛ) ነጻ ፈቃዱ እንዲገልጥባት የተሰጠችው ናት፡፡
ቸሩ እግዚአብሔር “ትሞታለህ” ሲለው እንኳን እግዚአብሔር ስለ ጥልቅ ፍቅሩ አዳምን የመከረው እንጂ ጠበኛ አምላክ ሆኖ የተናገረው አይደለም፤ እገድልሃለሁ አላለውምና፡፡

እዚህ ጋር መረዳት ያለብን ዕፀ በለስ በራሷ መልካም መሆኗን ነው፡፡
ፍሬዎቿም እንደዚሁ መልካም ናቸው፡፡ በውስጧ ሞትን የተሸከመች ወይም መርዝነት ያላት አይደለችም፡፡ ስለዚህ ዕፀ በለስ ልክ በዕፀ ሕይወት ላይ እንደተነጋገርነው የሕግ ምልክት ናት፡፡ በመሆኑም አዳም የሞት ሞትን የሞተው የሕግ ምልክት ኾና የተሰጠችውን ዕፅ ባለመታዘዙ ስለ በላት እንጂ ዕፀ በለስ የምትገድል ኾና አይደለም፡፡

በሌላ አገላለጽ አዳምን የጣለው አለመታዘዙ ነው። እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ደግሞ ግድ የለሽነቱ ነው፡፡

በዕፀ በለስ ውስጥ ከዕውቀት በቀር ምንም የለም፡፡ ዕውቀት ሲባል ራሱ አዳምና ሔዋን ከክብር መዋረዳቸውን ማወቅን ነው እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ አንዳንድ ሰዎች እንደሚሉት ዕፀ በለስ በጎ ዕውቀትን የምታሳውቅ ዛፍ ብትኾን ኖሮ ኃጢአት “ኃጢአት” ሳይሆን “የዕውቀት አስተማሪ” በተባለ ነበር፤ እባብ በእርሱ አንጻርም ዲያብሎስ ባልተወቀሰ “የሐሰት” ሳይሆን “የጥበብ አማካሪም” በተባለ ነበር፡፡
ነገር ግን አይደለም አዳምና ሔዋን መልካም የተባለው መታዘዝ፣ ክፉ የተባለውንም አለመታዘዝ ከመውደቃቸው በፊት ያውቁ ነበር፡፡

ዛሬ በዕፀ በለስ ምክንያት የመጣው ሞት በዕፀ መስቀል ምክንያት ተወግዶልናል፡፡
~~~~

ቀጣይ ትምህርታችን
የዕለት ረቡዕ ሥነ ፍጥረታት
#ወስብሐት ለእገዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!

@mahiberekidusan
@mahiberekidusan
@mahiberekidusan

❹⓪