Get Mystery Box with random crypto!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ ዘለዓለም ሥላሴ አሜን፡፡ #እንኳን-ለደብረ ታቦር | ማኅበረ ቅዱሳን (Mahibere Kidusan)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ ዘለዓለም ሥላሴ አሜን፡፡
#እንኳን-ለደብረ ታቦር በዓል በሰላም አደረሰን፡፡
#ደብረ-ታቦር/ቡሔ
ነሐሴ 13 ቀን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሀነ መለኮቱን የገለፀበት ዕለት ነው፡፡ በዚች ዕለት አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሶስቱን ደቀ መዛሙርቱን ጴጥሮስን፣ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ ወደ ተራራ ላይ ወጡ መልኩም በፊታቸው ተለወጠና ብርሃነ መለኮቱን ገለጸባቸው ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ ሉቃ 9፥28 ማቴ 17 ፥1
እነሆ ሙሴን ከመቃብር ኤልያስን ከብሔረ ህያዋን ጠቅሶ አምጥቶ አሳያቸው፡፡ ጴጥሮስም ይህንን አይቶ ጌታችንን እንድህ አለው፡፡አቤቱ ጌታ ሆይ በዚህ መኖር መልካም ነው ሶስት ሰቀላዎችንም እንስራ አንዱን ለአንተ አንዱን ለሙሴ አንዱን ለኤልያስ አለው፡፡ይህንንም በተናገረ ጊዜ ጌታችን በሰው እጅ የተሰራ ማደሪያ የማይሻ መሆኑን ለጴጥሮስ ያሳየው ዘንድ እነሆ ደመና ጋረዳቸው የጌታችንን ጌትነቱን የሚገልፅ በሐዋርያትም ልቡና እምነትን የሚያጸና እንድህ የሚል ቃል ከደመና ውስጥ መጣ ይህ የምወደው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት ሙሴና ኤልያስም ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩት ትንቢታቸውንም በቸርነቱ አረጋግጦ ወደ ተራራ ላይ በመውጣቱ ነቢያት እና ሐዋርያት ደስ አላቸው፡፡ በአጠቃላይ ይህ ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ሙሴና ኤልያስን ለሶስቱ ምስጢረ ሐዋርያት ያሳየበት እርሱም ሁለመናው ነጭ ልብስ መልኩ እንደመብረቅ ሆኖ የታየበት ዕለት ነው ፡፡ በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ይህ በዓል ከጌታችን አበይት በዓላት አንዱ እንደሆነ ታስተምራለች፡፡ ምዕመናንም በዓሉን በድምቀት ያከብሩታል፡፡ ዳቦ በመጋገር ምሳሌውም እረኞች በተራራው ላይ ብርሀኑን እያዩ በወጡበት አልተመለሱም ነበረና ቤተሰቦቻቸው ዳቦ ይዘው የመሄዳቸው ምሳሌ ነው ጅራፉ የነጎድጓድ ችቦ የሚበራው ወይም ደመራው የብርሃነ መለኮቱ ምሳሌ ነው፡፡ እናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሁሉንም በምሳሌ ሰንዳ አስቀምጣለች፡፡ ለአባቶቻችን ምስጢሩን የገለጸ ለእኛም ይግለጽል፡፡ ስለ ሁሉም ነገር የቸርነቱን ስራ ይስራልን፡፡ ከበዓሉ በረከት ከቅዱሳን ምልጃና ጸሎት ከመላዕክት ጠባቂነት ከቅድስት ድንግል ማርያም እናትነትና ምልጃ ይክፈለን፡፡ "አድህነኒ እግዚኦ እስመ ኃልቀ ኄር ወውህዴ ኃይማኖት እመእጓለ እመህያው" መዝ 11፥1 አቤቱ ደግ ሰው አልቋልና አድነኝ፤ ከሰው ዘንድም መተማመን ጎድሏልና ።
#ሼር-ያድርጉ
#መልካም-በዓል-
#ወስብሐት-ለእግዚአብሔር ወለወላድቱ ድንግል ወለመስ ቀሉ ክቡር አሜን፡፡

@mahiberekidusan
@mahiberekidusan
@mahiberekidusan