Get Mystery Box with random crypto!

​#ለባለ_ልደቱ_ምን_አዘጋጀን? ምንም እንኳ እንደ ሰብአ-ሰገል ንፁህ ነህ እያልኩኝ - ወርቅ | ማኅቶት

​#ለባለ_ልደቱ_ምን_አዘጋጀን?

ምንም እንኳ
እንደ ሰብአ-ሰገል
ንፁህ ነህ እያልኩኝ - ወርቅ ባ'ላመጣም ለፈዋሽነትህ - ከርቤ በ'ላቀርብም
ሊቀ ካህን ስልህ - ዕጣን ባልገብርም
ለልደት ስጦታህ
ዙፋን እንዲሆንህ
ልቤን አልሰስትም

እንኳን ለጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ዋዜማ በሰላም አደረሳችሁ

ይህን ፅሁፍ በልደቱ ዋዜማ የለጠፍኩት ለባለ ልደቱ የልደት ስጦታ የማዘጋጃ ጊዜ እንዲሆነን በማሰብ ነዉ!

አንድ ጥያቄ አለኝ

ወዳጃችሁ ልደቱን ታከብሩለት ዘንድ ቤቱ ጋበዛችሁ እንበል ...እናንተም ያስደስተዋል ብላችሁ የገመታችሁትን ስጦታ ይዛችሁ ወዳጃችሁ ቤት ተገኛችሁ ከዚያም የስጦታዉ ስዓት ሲደርስ ዋናዉ ልደት አክባሪዉ እያለ የተወለደው ተቀምጦ ቤቱ ድረስ የጋበዛችሁን አስቀምጣችሁ ሁላችሁም ያመጣችሁትን ስጦታ እርስ በእርስ ብትሰጣጡ ባለ ልደቱ ልደት አክባሪዉ ምን የሚሰማዉ ይመስላቸዋል?

ወዳጅ ብዬ የጠራዋችሁ ጤነኞች አይደሉም እንዴ እኔን አስቀምጠዉ ለራሳቸዉ ስጦታ የሚሰጣጡ ?...

የተወለደዉን ክርስቶስን አስቀምጦ የኛ እርስ በእርስ ስጦታ መሰጣጠት ምን ይሉታል ?

በእርግጥ ስጦታ የፍቅር ምለሰክት ነዉ ተስፋ ይገለፅበታል መዉደድ ነፍስ ይዘራበታል...ለገና ስጦታ መሰጣጠት በራሱ የከፋ አይደለም መልካም ነዉ ...ግን ዋናዉን ባለ ልደት ክርስቶስን ረስተነዉ ለእርሱ አንድም ስጦታ ሳናዘጋጅለት ከሆነ ችግሩ እዛ ላይ ነዉ

ታዲያ ምን እንስጠዉ?

#በንስሐ
_አንፅተን_ልባችንን_እንስጠዉ!

#እኛዉ_እንድንባረክበት_ዘመናችንን_ለእርሱ_መባ_አድርገን_ለልደቱ_እንለግሰዉ
በተቻለን_መጠን_የማይጠቅመንን_የስጋ_ፍላጎታችንን_አሳልፈን_እንስጠዉ
.
.
.
#በድጋሚ_መልካም_የልደት_በዓል_አልኳችሁ

በዚያም የመልካም ምኞት መግለጫ share ይደረግ
@Mahetotbot
@Mahetotbot
@Mahetotbot