Get Mystery Box with random crypto!

​#የገና_ቀን_አርብ_ዉሏል_ፆም_ነዉ? የ በዓለ ልደት ዓርብ ቀን መዋል ይበላል ወይስ | ማኅቶት

​#የገና_ቀን_አርብ_ዉሏል_ፆም_ነዉ?


የ በዓለ ልደት ዓርብ ቀን መዋል ይበላል ወይስ አይብላም የሚል ጥያቄ ዘንድሮም በርክቷል።

የጌና (በዓለ ልደት) እና ጥምቀት ረቡዕ ወይም ዓርብ ቀን ቢውል ምን እናድርግ ለሚለው ጥያቄ መጽሐፈ ስንክሳር በስንክሳር ዘወርኃ ጥር 10 ይህን ይላል።

"በዚች ዕለት ምእመናን እስከ ምሽት እንደመጾሙን ያዘዙበት ምክንያቱ ይህ ነው የልደትና የጥምቀት በዓል በዓል በረቡዕ ወይም በዓርብ ቀን ቢሆን በበዓለ ኃምሳ የሚበላውን የጥሉላት መብል በጥዋት በመብላት ምእመናን ሁሉ በዓሉን እንዲአከብሩ የከበሩ አባቶቻችን ሐዋርያት አዝዘዋል እሊህ ሁለቱ የእግዚአብሔር ታላላቅ በዓላቶቹ ናቸውና።" (ስንክሳር ዘወርኀ ጥር 10)

አርብ ቀን ፆም አይደለም ሐሙስ እስከ ምሽት አንድ ሰዓት ተፁሞ አርብ የበዓሉ ለት ይበላል...

ይህም የሆነበት የጌታ የልደቱ ቀን በፍፁም ደስታ መከበር ስላለበት አባቶች የሰሩት ስርዓት ነዉ!

#share #ለሁሉም_ይድረስ
@Mahetotbot
@Mahetotbot
@Mahetotbot