Get Mystery Box with random crypto!

​#ቀሳ (#የፀበል_ስንብት_ምልከታ_ክፍል_1) 'አንተ ኖሮህ ሌሎች የሚጠይቁት ምንአልባት በመለኮታ | ማኅቶት

​#ቀሳ
(#የፀበል_ስንብት_ምልከታ_ክፍል_1)

"አንተ ኖሮህ ሌሎች የሚጠይቁት ምንአልባት በመለኮታዊ ሐይል ብቻ የሚቻል ነዉ ፤ ሌሎች ኖሯቸዉ አንተ የምትጠይቀዉ ግን የጎጆህን በሮች ከፍቶ ዙሪያህን የመቃኘት ያህል ጥረት ብታደርግ በቀላሉ የሚመለሱ ሊሆኑ ይችላሉ ። "

አዉቃለሁ ጊዜ የለህም፤ የሳምንቱን ቀናት በስራ ነዉ የምታሳልፈው ፤ buys ነህ ፤ የኑሮ ዉጣ ዉረድ ሰቅዞ ይዞሐል...!

ቢሆንም ሮጥ ብለህ እስኪ በየፀበሉ ከአራቱም ማዕዘናት ዕልፍ የስጋና የነፍስ ጥያቄያቸዉን አንዥርግገዉ የሚተሙ ወገኖችህን ተመልከታቸዉ...!

ግማሹ እግሩ ታስሮ መራመድ ተስኖት በራስ መተማመን መንፈሱን የስጋ ደዌ ስልቦት በሌሎች ዕርዳታ ከቦታ ቦታ ይንቀሳቀሳ ... አንተ ግን አትንኩኝ ባይ ነህ ፤ተሳስቶ የነካህም ይቅርታ ጠይቆህ ነዉ የሚያልፈዉ

ገሚሱ የሰዉነት ክፍሎቹ መስራት አቁመዉ አንተ ሮጥ ብለህ አንድ አፍታ የምታደርጋቸዉን ቀላል ነገሮች ማድረግ ቅንጦት (ጭራሽ የማይታሰብ ) ሆኖበት ታገኘዋለህ

ከፊሉ በመንፈስ መታወክ ከሰዎች ተገልሎ በሰንሰለት ታስሯል። አንተ ግን ዛሬም በናፍቆት የምትገናኛቸዉ ወዳጆች አሉህ ፤የማይረሱ ጊዚያትን ከቤተሰብህ ጋር እያሳለፍክ ነዉ ፤ ከትላንት ትማራለህ ፤ ዛሬን ትኖረዋለህ ፤ ለነጌህ ታቅዳለህ...

እነዚህን ስትመለከታቸዉ የራስህን ጥያቄዎች ትዘነጋቸዉና "ጌታ ሆይ እባክህ ፈዉስን ላክላቸዉ ምህረት አድርግላቸዉ መድኃኒትነትህን ግለጥ ".... እያልክ መለመን ትጀምራለህ (ሂድና ሞክረዉ)

በየሆስፒታሉና የየሰዉ ቤት የሸፈነዉም ገመና ከዚህ የተለየ አይደለም!

"አንተ ኖሮህ ሌሎች የሚጠይቁት ምን አልባት በመለኮታዊ ሐይል ብቻ የሚቻል ነዉ። ሌሎች ኖሯቸዉ አንተ የምትጠይቀዉ ግን የጎጆህን በሮች ከፍተህ ዙሪያህን የመቃኘት ያህል ጥረት ብታደርግ በቀላሉ የሚመለሱ ሊሆኑ ይችላሉ"

#ለዚህ_ብቻ_ተመስገን

@mahetotorto
@mahetotorto
@mahetotorto
@mahetotorto