2022-07-11 17:48:36
" ቃል "
ከላይ መጀመሪያ የሚለውን ተመለከትን መጀመሪያው ያለው ጥንት የሌለው መሆኑን ተመልክተናል
ቃል " LOGOS" የምንለው ምንድን ነው ?
ቃል ስንል በሁለት መንገድ ይፈታል
፩) ዝርው ቃል የምንለው ( የንግግር ቃል ፣ ተበታኝ ) ቃል
ይህ ቃል ሕያው አይደለም ይነገራል ይጠፍል የሚጠቅመው ለመስማት ነውና
ይህ እራሱ በሦስት ይከፈላል
* ቃለ ሰብ ( የሰው ቃል )
* ቃለ እንስሳ ( እባብና ሔዋን የተነጋገሩበት ቃል )
* ቃለ መላእክት ( አተርጋዎን ) 1ኛ ቆሮ 13፤1 " በመላእክት ልሳን እንኳን ብናገር ፍቅር ከሌለኝ ከንቱ ነኝ " ቅዱስ ጳውሎስ በመላእክት ልሳን ሲል በመላእክት ቃል ሲል ነው።
፪) አካላዊ ቃል
ይህ ቃል ሕያው የሆነ ቃል ነው። ዝርው ቃል የማይላክ ቃል ነው የአብ ቃል ግን የሚላክ አካላዊ ቃል ነው።
" ቃሉን ላከ ፈወሳቸው ከጥፍታቸውም አዳናቸው " ( መዝ 107 ፤ 20 )
ስለምን ቃል ተባለ ? የሚለው እንመለከታለን
318 viewsmuluken Ayele, 14:48