ወንጌሉን እንጀምራለን " በመጀመሪያው ቃል ነበር " ( ዮሐ ፩:፩) እዚህ ምዕራፍ ላይ ትንሽ እንቆያለን መሰረታዊ ምዕራፍ ስለሆነ ጊዜ ወስደን በተቻለ አቅም ሳይበዛ እንማማራለን #በመጀመሪያው - መጀመሪያ የሚለውን ቃል ስናይ መነሻ ያለው መጀመሪያ አለ ፤ መነሻ የሌለው መጀመሪያ አለ በሁለት ይከፈላል = ጥንት የሌለው መጀመሪያ ( ዮሐ 1:1 ) =መነሻ ያለው መጀመሪያ ( ዘፍ 1:1) “በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።” (ዘፍጥረት 1፥1 ) ዮሐንስ ወንጌል ላይ ያለው መጀመሪያ መጀመሪያ የሌለው መጀመሪያ መሆኑን የምናውቀው በመጀመሪያው ቃል #ነበር ይላል ኦሪት ዘፍጥረት ላይ ያለው መጀመሪያ መነሻ ያለው መሆኑን የምናውቀው በመጀመሪያ ሰማይ እና ምድር #ተፈጠሩ ብሎ ይነሳል #ነበርና #ተፈጠሩ ትልቅ ልዩነት አለው። ስለዚህ #በመጀመሪያው #የምትለው #ቃል #ጥንት #የሌለው #መጀመሪያ #መሆኑን #ያስረዳል። ቀጣይ በመጀመሪያ ሳይሆን የሚለው በመጀመሪያው ነው ለምን #"ው" የምትለው ቃል ተጠቀመ ለምን ??? እንመለስበታለን 499 viewsmuluken Ayele, edited 18:43