2022-06-29 18:03:27
መጽሐፍት ( ቅዱስ መጽሐፍት ) በእግዚአብሔር መንፈስ ነው የተጻፉት መጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ያስፈልጋቸዋል
የቅዱስ ዮሐንስ ጥንተ ነገሩ እንደምንድን ነው ቢሉ #አባቱ #ዘብዴዎስ ባለ ጠጋም ነበር ( ማር 16 : 1 ) #ከቤተ #ይሁዳ ይወለዳል እናቱ #ሰሎሜ ትባላለች ( ማቴ 27:56 ) እርሷም #ከቤተ #ለዊ ናት።
ቅዱስ ያሬድ " ዮሐንስ ድንግል ሆይ ለምንልን አማልደን የመለኮት ወንጌልን ሰበክህ #አባትህ #ከቤተ #መንግስት ነው #እናትህም #ከቤተ-ክህነት ናት ስለዚህ አቡቀለምሲስ ተባልክ " ድጓ ገጽ 192 ። ....በድጋሚ
ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቅዳሴ መግቢያ ላይም " ዮሐንስ #ከቤተመንግሥት #ከቤተ #ክህነት #ይወለዳል " ብለው ጽፈዋል።
ዮሐንስም ከአባቱ ጋርም ይሰራ ነበር። ማርቆስ 1 ላይ ያለውን ጥቅስ ብንመለከት ግልጽ ያደርገዋል -
" ከዚያም ጥቂት እልፍ ብሎ #የዘብዴዎስን #ልጅ #ያዕቆብን #ወንድሙንም #ዮሐንስን ደግሞ በታንኳ ላይ መረባቸውን ሲያበጁ አየ። ወዲያውም ጠራቸው አባታቸውንም #ዘብዴዎስን #ከሞያተኞቹ ጋር በታንኳ ላይ ትተው ተከትለውት ሄዱ። " ማር 1: 16-17
የቅዱስ ዮሐንስ አባት ዘብዴዎስ ሞያተኞች እንዳሉት ማለትም ቀጥሮ የሚያሰራ የሚያስተዳድር ሰው እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። እዚህ ጋር ወንድሙ ሐዋርያት የተቆጠረው ከዮሐንስ ጋር ለዮሐንስ መጥምቅ ደቀ መዝሙር የነበረ " እነሆ የእግዚአብሔር በግ" ብሎ ሲናገር ሰምተው ጌታችንን የተከተሉት ከሁለቱ ደቀ መዝሙር አንዱ ያዕቆብ ይባላል። በንጉሥ ሄሮድስ እጅ የተገደለው ያዕቆብ ነው።
“የዮሐንስንም ወንድም #ያዕቆብን #በሰይፍ #ገደለው።”
— ሐዋርያት 12፥2
ተብሎ ተጽፏል።
ቅዱስ ዮሐንስ የጻፍቸው መጽሐፍት እና ስሞች በቀጣይ እንመለስበታለን።
586 viewsmuluken Ayele, 15:03