Get Mystery Box with random crypto!

ጫምሲቱ ጫምስቲ በኦሮምኛ ቋንቋ ዝናብ የሚያቆም ማለት ነው።ይህ ስያሜ ከተፈጥሮ ለየት ባለ መል | #LWEQESH-Ethiopia

ጫምሲቱ
ጫምስቲ በኦሮምኛ ቋንቋ ዝናብ የሚያቆም ማለት ነው።ይህ ስያሜ ከተፈጥሮ ለየት ባለ መልኩ አንዳንድ ዝናብ እንዳይዘንብ የሚያደርጉ አልያም ከዘነበ በኋል እንዲቆም ማድረግ የሚያስችል ስልጦን ወይም እውቀት አላቸው ተብሎ ለሚታመን ሰዎች የሚሰጥ ሲሆን በውርስም በመማርም ሊገኝ ይችላል።
ይህንን በሚያደርጉበት ወቅት እርሾ ያልገባበት ቂጣ ሲመገቡ ለዚሁ ተግባር ብቻ የሚውል ቅጠል ቋጥኝ ላይ በማስቀመጥ ለረጅም ሰአት እራሳቸው ብቻ የሚረዱትን ፀሎት ይደግማሉ።
በተጨማሪ በደዌ ምክንያት ጫምሲቱ የሚሆኑ ሲኖሩ ጋፎ ይሰኛሉ።ዝናብ ሲመጣ ህመሙ ይነሳብናል ብለውም ስለሚያስቡ ዝናቡ እንዳይዘንብ ያደርጋሉ ተብሎ ይታመናል።
@LWEQESH_Events