Get Mystery Box with random crypto!

የዝናብ ነገስታት ጫምሲቱዎች በሀገራችን መንፈሳዊ በሆነ ጥበብ ዝናብን የሚቆጣጠሩ ሰዎች ናቸ | #LWEQESH-Ethiopia

የዝናብ ነገስታት
ጫምሲቱዎች በሀገራችን መንፈሳዊ በሆነ ጥበብ ዝናብን የሚቆጣጠሩ ሰዎች ናቸው።በተመሳሳይ ከሀገረ ደቡብ አፍሪካ ይህን በመሰለ ጥበብ የተካኑ ሰዎች ሲኖሩ ይህን አይነት ጥበብ የታደሉት ደግሞ ሴቶች ናቸው።
የባሎቤዱ ማህበረሰብ እነዚህን ሴቶች ዝናብን የመቆጣጠር እና የማዘዝ ሀይል አላቸው ብለው ያምናሉ።የአስተዳደሩንም ስርአት እነዚሁ ሴቶች ብቻ ይዘው ከትውልድ እየተላለፈ መጥቷል።
ስልጣኑ የሚተላለፈው ንግስቷ መሞቻዋ ሲቃረብ ይህ መንፈስ ላደረባት የንግስቲቱ ሴት ልጅ ከሌለችም ለቅርብ ዘመድ ስልጧኗን በማውረስ እሯሷን ታጠፋለች።
ከ1800 ዓም  በፊት ወንዶች የአስተዳደር ስርአቱን ሊቆጣጠሩ ቢሞኩርም ሴቶች ብቻ ስልጣኑን ይዘው ቆይተዋል።ለምሳሌ በቅርብ ዘመን የነበረች እና ከፕሬዝዳን ኔልሰን ማንዴላ ጋር የቅርብ ግንኙነት የነበራት (Mokope Modjadjiv) ትባላላች።
@LWEQESH_Events