Get Mystery Box with random crypto!

ሮዋ የመኢኒት ብሔረሰብ የለቅሶ ስርአት የመኢኒት ማህበረሰብ በቤንች ማጂ ዞን የሚገኙ ከደቡብ ኦ | #LWEQESH-Ethiopia

ሮዋ የመኢኒት ብሔረሰብ የለቅሶ ስርአት
የመኢኒት ማህበረሰብ በቤንች ማጂ ዞን የሚገኙ ከደቡብ ኦሞ ወንዝ ፈልሰው የመጡ ህዝቦች ናቸው።እነዚህ ህዝቦች ካላቸው ለየት ያሉና ትልቅ ቦታ ከሚሰጣቸው ባህሎች መካከል ለለቅሶ የሚድረግ ስርአት ነው።ስርአቱ በእድሜ ክልልና በማህበራዊ ስልጠና የተለያየ ሲሆን ለአዋቂዎች የሚደረገው ከህፃናትና ከወጣቶች የተለየ ነው።በመሆኑም አዋቂ ከሆነ የሞተው ትልቅ ድግስ ተደግሶ እየተበላ እየተጣ ለቅሶው ይካሄዳል።በተጨማሪም በድንጋይ እየተቀጠቀጠ በሬ፣ኮርማና ጥጃ ይገደልና ለቀስተኛ ስጋውን እየበሉ ወደ ቀብሪ ቦታው ያመራሉ።ቀብሩ የሚፈፀመው ተቀጥጦ በተገደለው በሬ ቆዳ ተከፍኖ ነው።በተጨማሪም ለቅሶው በዘፈን እና በተለያዩ የሙዚቃ መሳሪያዎች በመታገዝ ስርአቱ ይፈፀማል።
@LWEQESH_Events