Get Mystery Box with random crypto!

አባባ ተስፋዬ(የኢትዮጵያ የልጆች አባት) በሙሉ ስማቸው ተስፋዬ ሳህሉ በኢትዪጵያ ልጆችን ማዕከል | #LWEQESH-Ethiopia

አባባ ተስፋዬ(የኢትዮጵያ የልጆች አባት)
በሙሉ ስማቸው ተስፋዬ ሳህሉ በኢትዪጵያ ልጆችን ማዕከል ያደረገ መርሃግብሮችን በማዘጋጀት እና ለ41(፵፩) አመታት ያለመታከት ያደረሱ ናቸው።ትውልዳቸው በ1916 አ.ም ሰኔ 20 ቀን በባሌ ኮዳ በምትባል መንደር ሲሆን በጎባ ከተማ በቄስ ት/ቤት ፊደል ቆጥረው በኮከበ ፅባህ ት/ቤት።አዲስ አበባም ሲገቡ ገና የ14 አመት ታዳጊ ነበሩ።የጣልያንኛ እና የፈረሳይኛ ቋንቋ ይችሉ ስለነበረ በአስተርጓሚነት እንዲሁም በእትጌ ሆቴል(ራስ ሆቴል) ይሰሩ ነበር።የኪነጥበብን ዘርፍ የተቀላቀሉት በ1937 በማዘጋጃ ትያትር ቤት ሲሆን በ1948 በተከፈተው የብሔራዊ ትያትር ቤትን ተቀላቅለዋል።በዛም ከ70 በላይ ቲያትሮች ላይ ተሳትፈዋል።ሌላው ደግሞ በዘመኑ ሴት ተዋናዮችን ማግኘት ከባድ ስለነበር የሴት ገፀባህሪን ተላብሰው ተጫውተዋል።ኮሪያ በዘመተው የቃኘው ሻለቃ ጦር ቡድንም አባል ነበሩ።የውዝዋዜ አሰልጣኝ ደራሲ የልጆች መፅሐፍት አዘጋጅ ዜማና ግጥም ደራሲ ወዘተ የእርሳቸው ሙያዎች ናቸው።እኚህ ታላቅ አባት በ93 አመታቸው በ2009 ሐምሌ 24 ቀን ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።
@LWEQESH_Events