Get Mystery Box with random crypto!

ሀፍለታ ሻሂ በሀገራችን የተለያየ አይነት የመረዳጃ ማህበራዊ ድርጅቶች ሲኖሩ በደስታም በሀዘንም ሁ | #LWEQESH-Ethiopia

ሀፍለታ ሻሂ
በሀገራችን የተለያየ አይነት የመረዳጃ ማህበራዊ ድርጅቶች ሲኖሩ በደስታም በሀዘንም ሁሉን የበኩልን አስተዋፅኦ ያደርጋል።በበርታ ማህበረሰብም ሀፍለታ ሻሂ/የሻይ እንጠጣ የተባለ ፕሮግራም በህብረተሰቡ የተለመደ የመረዳጃ ማህበር ነው።ማህበሩ አንድ ሚስት ለማግባት የሚጣል ለጥሎሽ የሚከፈል ገንዘብ እጥረት ሲኖር፣በማንኛውም ምክንያት ለረጅም ሆነ ለአጭር ጊዜ ቦታ ለመቀየር ገንዘብ ሲቸግር ከቤተሰብ እና ቅርብ ዘመድን ጋር በመሰባሰብ ሻይ እና የተለያዩ ነገሮቹን በማዘጋጀት መክረው ገንዘብ የሚሰበስቡብት እና አስፈላጊውን የሚያደርጉበት ማህበር ነው።በተጨማሪም ይህ ማህበር እርዳታ ለጠየቀ ብቻ ሳይሆን በጓደኞች እና በጎረቤቶች ተነሳሽነት ሊካሄድ ይችላል።በዝግጅቱም ወቅት ጭፈራና ዘፈን ስለሚኖር ለመተጫጨት ይጠቅማል።
@LWEQESH_Events