Get Mystery Box with random crypto!

የዲዚ ማህበረሰብ የዲዚ ማህበረሰብ በደቡብ ኢትዮጵያ ማጂ ወረደ የሚገኙ ኑሮአቸውን በግብርና ላይ | #LWEQESH-Ethiopia

የዲዚ ማህበረሰብ
የዲዚ ማህበረሰብ በደቡብ ኢትዮጵያ ማጂ ወረደ የሚገኙ ኑሮአቸውን በግብርና ላይ ያደረጉ የኦሞቲክ ቋንቋ ተናጋሪ ህዝብ ናቸው።ማህበረሰብ በዘመናት ሂደት የራሱን ባህል እና የኑሮ ዘዴ ያዳበሩ ሲሆን በተለያየ ርዕሰ ጉዳይ ላይ የራሳቸውን አፈታሪክ አዳብረዋል።ከነዚህም ስለሞት የሚነገረውን አፈታሪክ ነው።አፈታሪኩ ጥንት በዲዚዎች ምድር ሰማይና ምድር የተቀራረበ ደስታ የሞላበት እና ሞት የማይታወቅበት ቦታ ነበር።ነገር ግን እንግዳ ሰዎች መጥተው ክፉ ነገር እነሱን በማስተማራቸው ሰማይ ምድር ተራርቀው ሞት በምድሪቱ ነገሰ ብለው ይተርካሉ።
በተጨማሪም በማህበረሰብ ናሊ የተሰኘ የጓደኝነት አመሰራረት ስርአት ሲኖራቸው በተመሳሳይ ፆታዎች መካከል የጠበቀ ወዳጅነት ከዛም አልፎ እንደ ስጋ ዝምድና ለመመስረት ሲፈለግ የሚደረግ ስርአት ነው።
@LWEQESH_Events