Get Mystery Box with random crypto!

የጥርስ ነቀላ(የኬት) ስነስርአት በመኢኒት ማህበረሰብ እንደማህበረሰብ ገለፃ መኢኒት ማለት ሰው | #LWEQESH-Ethiopia

የጥርስ ነቀላ(የኬት) ስነስርአት በመኢኒት ማህበረሰብ
እንደማህበረሰብ ገለፃ መኢኒት ማለት ሰው ነኝ ማለት ነው።ማህበረሰብ በደቡብ ብሔረሰብ በቤንች ማጂ ዞን ሲገኝ የአካባቢው ተወላጆች እንደሚጠቅሱትም ከደቡብ ኦሞ ወንዝ ፈልሰው እንደመጡ ይነገራል።
በማህበረሰብ አስገራሚ ከሆኑ ባህሎች መካከል የጥርስ ነቀላ ወይም የኬት ስነስርአት ነው።የጥርስ ነቀላ አንድ ጎረምሳ ወይም አንዲት ኮረዳ ለጋብቻ መድረሳቸውን የሚያመለክት ክብረበአል ነው።በዚህ መሰረት አንድ ሰው ወደወጣትነት የመሸጋገር ባህሪ ወይም የሰውነት አካል ለውጥ ሲያመጣ ሁለት የታችኛውን የፊት ጥርስ በማውለቅ ለጋብቻ መድረሱን/መድረሷን ያሳውቃሉ።
ለስርአቱ ድምቀትም ወጣቶች የተለያዩ ባህላዊ ዘፈን እና ጭፈራ በመጫወት እንዲሁም ቫሉ የተሰኘ ባህላዊ መጠጥ በማዘጋጀት ደስታቸውን ይገልፃሉ።
@LWEQESH_Events