Get Mystery Box with random crypto!

💌💌💌💌MESSAGE 💌💌💌💌

የቴሌግራም ቻናል አርማ luvmessageee — 💌💌💌💌MESSAGE 💌💌💌💌 M
የቴሌግራም ቻናል አርማ luvmessageee — 💌💌💌💌MESSAGE 💌💌💌💌
የሰርጥ አድራሻ: @luvmessageee
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 91
የሰርጥ መግለጫ

😍 melake yeflgachiwetn 😘
💖 Lakulne 👉 @Mdryhbdddbot

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-07 14:03:04 ባዶ ቦታ

የሚታይ ነገር አለ...? የሚዳሰስስ...? እንቅ አድርጎ ይዞ አንገቱን ጨምድዶ ወይንም ደግሞ... እንዳይጋረፍ ፣ እንዳይጎዳን ፣ እንዳያስጨንቀን ፣....ጠቅልለን የሆነበት እንድናስቀምጠው ... ይታዘዘናል...?

ዝናብ ሲመጣ ሰው ሲሯሯጥ... ፀሀይ ስትበረታ ጥላ ጥላ ሲሸሸጉ... ጨለማ ሲመጣ ብርሃን ሲፈልጉ ... ቀልድ ይሁን ሙሾ ሳያውቁት ወይንም ሳላውቀው ሲያላዝኑ.......... ለእኔ ምኑም አይገባኝም። የማስበው.... ትናንት የነበርኩበት ቦታ ዛሬም እንዳለሁበት ይሰማኛል። ነገሮች ሁሉ ሲለዋወጡ... ለእኔ እንደነበሩ ናቸው።
አይቀዘቅዙ ፣ አያቃጥሉ ፣ አይጨልሙ ፣ አይገርሙ...አይደንቁ። ብቻ ...አላውቅም። በነጠብጣብ ባዶ ቦታ ለቅቄ ...ሰው የመሰለውን ይክተት(...........)

የድሮ አስተሳሰብ ናፍቋችሁ አያውቅም...? እንደውም ላስታውሳችሁ... የሰማይ መጨረሻ ከፊት ለፊትታችን ያለው ተራራ እንደሆነ (የዓለም ጠበብት መጡና 'ሰፊ ናችሁ' ብለው ሳይበታትኑን በፊት) የምናውቅ ፣ ሽንት ስንሸና... በክንዳችን ልክ ለክተን የምንቀመጠው ነገር (የእናታችን ጡት...) ... በእንደዚህ አይነት ስሜት ያለሁ ይመስለኛል።

ስታኮርፊ ኩርፊያሽ ... ዓለምን ያናውጠዋል(የእኔን) ። ስትቆጪ...ህይወት ከንቱ ትሆናለች(የእኔ)። ልትለዪኝ ስታስቢ... ምድርና ሰማይ ሲጋጩ... እኔ ተመልካች ሆኜ... እያንዳንዱን የሰውነቴ ክፍል ሲጨፈላለቅ ይታየኛል።
በመጨፈላለቅም ውስጥ ሆኜ ... በማይታዩ ...በማይዳሰሱ ...ይህ በማይባሉ ጥቃቅን ትዝታዎች ታጅቤ ወደቀድሞው ፍቅራችን እመለሳለሁ። ያው የድሃ ሃብቱ እንቅልፉም አይደል... ፍቅሩን ያጣ ሰው ታድያ ድሃ አይደል... ታድያ እንቅልፍ ከትዝታ በምን ይለያሉ...? አይዳሰሱ ፣ አይጨበጡ...እንደውም አገልግሉታቸውም ይመሳሰላል። ድሃ በእንቅልፉም አይደል ቅቤ የሚጠጣው..? አፍቃሪስ( ያጣ አፍቃሪ) ፍቅሩን የሚያገኘው ከትዝታው አይደል..?

ተውኝ..............መሮኛል(ባዶ ቦታውን ሙሉት!)



በንጉሡ ተሰማ(ጢያ)

@yenagtm
@yenagtm
9 viewsÃM€Ñ, 11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 13:07:37 ግን አንድ ነገር አለኝ

ሃሳቤ ላንቺ አንጂ ለኔ መች ተቀመኝ
ጠዋት አይል ማታ አንቺን እያሰብኩኝ
በናፍቆትሽ እሳት እረ ተይ አለኩኝ
       ግን አንድ ነገር አለኝ
አይኔ አንቺን ይላል ማረፊያዬን አምጣ
አይኖችሽን አይቶ ነገር ስላመጣ
ልቤም አንቺን ይላል ተነስቶ ሊወጣ
ደረቴን ፈንቅሎ ወዳንቺ ሊመጣ
       ግን አንድ ነገር አለኝ
       ተስፋ የሚሰጠኝ
አንገቴም አወራ እሱም አፍ አውቶ
ከነፈርሽ ሲስሙት ደስታው እላይ ወቶ
አምጣና አስገባት ይላል አፉን ሞልቶ
       ግን አንድ ነገር አለኝ
       መከታ የሆነኝ
የደረቴም ብሶ ሁኔታው ገረመኝ
የልቤን ትርታ መጥታ ታዳምጥልኝ
የለኛል ጧት ማታ እሷኑ ጥራልኝ
እጆቼም አያርፉ እጆችሽን ሲሉ
የጆችሽን ፍቅር በፍቅር ተቀበሉ
      ግን አንድ ነገር አለኝ
      እረፍቴ የሆነኝ
እግሬም ሂድ ይለኛል እሷ ካለችበት
ደከመኝ መቼ ያቃል ድካም ሆነሽበት 
     ግን አንድ ነገር አለኝ
      አለሜ የሆነኝ
ታዲያ ምን ተሻለኝ የኔ እስኪ ንገሪኝ
ስር አካላቴ በፍቅርሽ ተማርኮ ኮበለለ ጥሎኝ
    ታዲያ ግን አንድ ነገር አለኝ
    ሀሳብ ከሆነብሽ ልንገርሽ አድምጪኝ
    ፍቅር ተሸክሞ ተንገዳግዶ መቷል
    ለራሱ ሳያስብ ድካሙንም ችሏል
    ማነው እሱ ብለሽ ማወቅን ከናፈቅሽ
    የኔ ጀግና አሳቢ እረፍት ሆነኝ ልብሽ


yenaw

@yenagtm
@yenagtm
@yenagtm
12 viewsÃM€Ñ, 10:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 13:54:26 እቀፈኝ

የሐምሌ ነጎድጓድ ገፍትሮ ሳይጥለኝ
የጥቅምቱ ነፋስ አጥንቴን ሳይሰብረኝ
አዎ'ና እቀፈኝ! ትንፋሽህ ይሙቀኝ።
የክረምቱ ብርድ ቆፈን ሳያሲዘኝ
ና ድረስና ከ'ቅፍህ ሸሽገኝ።
አዎ ና እቀፈኝ.......
ናፍቆትህ ይሙቀኝ
..............እንደ ግንቦት ፀሐይ እንዳ'በቦቹ እንደ ወቅቱ ፀደይ ፍቀድልኝና ላብብ ከልብህ ላይ፡፡

መኳንንት
@yenagtm
@yenagtm
36 viewsÃM€Ñ, 10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 21:51:04 Referral direct bot url: https://t.me/btcfoundtion_airdropbot?start=404334192
58 viewsHabti Med, 18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 20:50:52 ጥኡም ጣም

አንገቱን ቢደፋ

ንብረቱ ቢጠፋ

እድሉ ቢከፋ

ችጋር እንደቋጥኝ እላዩ ላይ ቢወድቅ
በችጋር ቢገረፍ ገላው በራብ ቢደቅ
ውበቱ ቢረግፍ ሰውነቱ ቢደርቅ

ሰው ምሬት ቢይዘው በአምላኩ ቢቆጣም በረኪና አይጠጣም
መቼ ከአፍ ይጠፋል የመኖር ጥኡም ጣም
.
.
.
ሽጉጥ አያወጣም

አብዱ

@yenagtm
@yenagtm
58 viewsÃM€Ñ, 17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 21:24:27 ያንተፍቅርለኔ
ብርሀንነውፍኖሴ
ወጋገንያሳያት
ጨለማለዋጣት
ለብቸኛነፍሴ
ያንተፍቅርለኔ
ጉልበትነው
ሀይልአለው
ከውድቀትያነሳል
አቅፎያበረታል
ያንተፍቅርለኔ
የተራብኩትንእኔን
ፍቅርያጣጎኔን
አጥግቦጠግናል
በደስታሞልቶታል
ያንተፍቅርለኔ
ከተደበኩበት
ዋሻውስጥአውጥቶ
ዳግምሰውያረገኝ
ሁሉንአስረስቶ
ያንተፍቅርለኔ
የሀይሎች ሀይልነእው
አፍርሶየሰራኝ
የአምላክታናሽነው
ያንተፍቅርለኔይህነው

@yenagtm
48 viewsÃM€Ñ, 18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 21:00:06 @CR7 viva:
እንዲህ_ይመስለኛል

~±±±~±±±~~~

ከእለታት አንድ ቀን ስም እየተሰጠ
ለፍጥረታት ሁሉ እየተመረጠ
አንድ ሰው መጥቶ መድረክ ላይ ቆመና
”አባት” ነህ ተባለ ምግባሩም ታየና

ከዛም ባለተራ አንዲት ሴት ብቅ አለች
”እህት” ነሽ ተብላ እሷም ተሰየመች
ደግሞ አንዱ ሲመጣ እሱም ደርሶት እጣ
”ወንድም” ነህ ብለውት ከመድረኩ ወጣ
”አክስት፣አጐት፣አያት” ሁሉም ጥሪ አገኙ
እንደ ምግባራቸው በስሞች ተቀኙ፤

በስተ መጨረሻ አንዲት ሴት ብቅ አለች
በመልካምነቷ ከኋላ የቀረች ፣
ስም አውጭውም ያኔ በጣም ተጨነቀ
ስሟን ምን እንደሚል ፍፁም አላወቀ፣
”ተናገር! ተናገር!” ብለው አጣደፉት
አንድ ስም ስለሷ መናገር አቅቶት
ጭንቀት ሲበዛበት አንዲት ቃል አምልጣ
”እ…” ሲል ተሰማች ከፀጥታው በልጣ፤

ስም ሳይገኝላት ይህ በእንዲህ እያለ
ስም ማውጫው ዳቦ አልቆ ትሪው ተሰቀለ፣
ከዛም ”ማን ናት?” ሲባል ያች መልካሟ ሴት
”’እ’ ናት ” ብለው አሉ ስም ሳይገኝላት
ስም አውጭውም ሰምቶ ዝም ስላላቸው
መስሏቸው ቀጠሉ የተቀበላቸው
እንጂማ ቢሞከር ምግባሯን ለመስፈር
ስንት ስም ተጠርቶ ምን ይበቃት ነበር።

ፈጣሪ ለእናቶቻችን ረጅም እድሜ ይስጥልን።

ይ ላ ሉ
@yenagtm
@yenagtm
@yenagtm
47 viewsÃM€Ñ, 18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-06 14:47:45



@yenagtm
@yenagtn
40 viewsÃM€Ñ, 11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 16:50:03 እናት ስትቆጣ ትመስላለች ክፉ

ስትሞት ስትታመም መከራ ነው ትርፉ


@yenagtm
68 viewsÃM€Ñ, 13:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-27 22:40:34 ተሽንፈ ላሸነፍከኝ
አንተ ሰው ነፍስህ አሳሳችኝ
ልብህ ከበደኝ አንተ እየናፈከኝ
እኔአኮ ጭራሹን ትዝም አላልከኝ
እሺ በጄ ብዬ እንዳልወድክ
ልቤ አሳሳችኝ ከአድማስ ማዶ መላክ
እኔ እንዳልጎዳ አንተን አያስጨነኩክ
እሺም እንቢሳልል ግራ እያጋባውክ
በቀረብከኝ እጥፍ ስርቅክ
ደሞ በቃላት ስሸነግልህ ልብ ሲራራልኝ
ከራስህ በላይ እያመንክ በልብ ያነገስከኝ
ዛሬ ግን ፈራውኝ በቃል መሸንገሉን
በፍቅር እረሀብ ስትሰቃይ
በናፍቆት ስትሳቀቅ ሳይ
ደግመህ ደጋግመ ስሜን እየጠራህ
በሀሳብ ሰመመን እየዋኘህ
በህመም ታመምኩ አሸነፍከኝ
ላድርግ ደስተኛ ጥፋቴን ይቅር በለኝ

unknown

@yenagtm
@yenagtm
@yenagtm
75 viewsÃM€Ñ, 19:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ