Get Mystery Box with random crypto!

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን📖

የቴሌግራም ቻናል አርማ lorate_tsegaye_gebremedihen — ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን📖
የቴሌግራም ቻናል አርማ lorate_tsegaye_gebremedihen — ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን📖
የሰርጥ አድራሻ: @lorate_tsegaye_gebremedihen
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.08K
የሰርጥ መግለጫ

ጥበብ ይናፍቀኛል፤ ተቻችሎ የሚኖር ህዝብ ያስቀናኛል፤ ድንቁርና ያስፈራኛል።
©ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን
❤️JOIN (ተቀላቀሉን)
@lorate_tsegaye_gebremedihen
ቢያንስ ለ10 ሰው #share #forward በማረግ ለተከብሩ የአለም ብላቴ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን
አክብሮታችንን እንግለፀለት!!!!!! ከሎሬቱ

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-03-26 23:07:12 ብርድ ብርድ ይለኛል

አንሶለ ገልጬ ብተኛም ከውስጡ
አልመቸኝ ሲለኝ ብወጣም ከቆጡ
ብርድ ብርድ ይለኛል ሲመጣ ክረምቱ
እጠቅብሻለሁ አትመጪም ወይ እቱ

ወራት እየቆጠርሽ ልብሽ ካላሰበኝ
ነይልኝ እላላለሁ ናፍቆትሽ ገደለኝ
አምናና ካቻምና አለሁኝ ዘንድሮም

እሳቱን አንድጄ ስቀመጥ ከደጄ
ይከፋኝ ጀምሯል ሳጣ አንቺን ለምጄ
ምናለ ብትመጪ በክረምት በዚ ብርድ
ማን ይሆን ከልካዩ ያስቀረሽ ከሱ ዘንድ
እኔ ከአንቺ ወስዶ ቤቴን ያፈረሰው
ንዳድ እሳቴ ላይ ውሀ የቸለሰው

ብቻ እሱልተወው ብርድ ብርድ ይለኛል
አብረን ምንሆንበት ቀኑ አልደርስ ብሎኛል

ምስልሽ ይታየኛል ከፊቴ ተሰቅሎ
አረንጓዴ ለብሰሽ ገላሽ ተሸፍኖ

ጸጉርሽን አቅልመሽ ካንገትሽ ደፍተሽው
ጥርስሽን በስሱ ገርበብ አድርገሽው

ማየት ንፍቅ አለኝ አይኔ አንቺን እያለ
ዘንድሮ በቆሎ ስንት ነው ተባለ...


JOIN

@lorate_tsegaye_gebremedihen
@lorate_tsegaye_gebremedihen
@lorate_tsegaye_gebremedihen
2.9K views20:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 16:27:50 "እንደምነህ ህውሀት ፣ እኔ አለሁ በጤና
ጤና እንደነሳኸኝ ፣ ጤና ይንሳህና
አለሁ ደሜን ላቤን ፣ እድሜዬን ገብሬ
ከሻብያ መንግስት
ተላላኪ ሴት ጋር ፣ ቀለበት አስሬ
ትውልድን ልቀጥል
ፍቅር እያነሳሁ ፣ ጥላቻዬን ስጥል
አለሁ ቃል ገብቼ ፣ ሀገር ላልገነጥል።
።።።።።።።።
አንተ ግን እንዴት ነህ
ተጠማሁኝ ላለ ፣ ሆምጣጤ ምትጥል
የወንድ ብልት ላይ
አምስት ሌትር ውሃ ፣ የምታንጠለጥል
ወንድ የምታኮላሽ ፣ ወንድ የምታመክን
እንደምነህ ህወሀት ፣ እንደምነህ አትክን?
ህዝቡን በዘር በዘር ፣ ከፍለህ ምታፋጀው
የገዛ ህዝብህን ፣
ጠባብ አሸባሪ ፣ ብለህ ምትፈርጀው
በገዛ ህዝብህ ላይ ፣ ጦር ምታደረጀው
በዘግናኝ ሁኔታ ፣ ዜጋህን ምትረሽን
ሰማህ ወይ ሲወራ
ውሸት መሸነፍ ነው ፣ ያለፈበት ፋሽን
የወደቀ ሀሳብ ፣ መሆኑ ሲነገር
በወደቀ ሀሳብ
እንደማትነሳ ፣ የወደቀች ሀገር
ሰማህ ወይ ሲነገር?
።።።።።
እኔማ ይኸውልህ ፣ የለም የማልሰማው
የለም የማላየው ፣ በቀን በጨለማው።
እንደውም ሰሞኑን
መግለጫ ምታመርት ፣ ያንተ የውሸት በር
ባየር ሰአቷ ላይ ፣ እውነት ስትናገር
እውነት ይዛ ስትበር
አየናት እያሉ
ሲነግረኝ ሰው ሁሉ
"ካላየሁ አላምንም !" ፣ በማለት ሞግቼ
ወደ ቤት ገብቼ
ቲቪዬን ብከፍታት
ጧ ብላ ፈነዳች
እውነት መናገሯን ፣ ማመን ስላቃታት ።
ፈንድታ በጠፋች
የቲቪዬ እስክሪን ፣ ማታስተላልፈው
የከረመ አቧራ ፣ በላይዋ ያረፈው
ምን አፈላሰፈው?
የህይወት ታሪኳን ፣ ስትጠፋ እንዴት ፃፈው? !
"ዘላለም ከምኖር ፣ በውሸት ታስሬ
አንደኛውን ልጥፋ ፣ እውነት ተናግሬ
ያለች ይመሥለኛል
።።።።።
እንደምነህ ህወሀት ፣ እኔ አለሁ በጤና
ጤና እንደነሳኸኝ ፣ ጤና ይንሳህና
አለሁ ሰው አፍቅሬ
አለሁ ተጣምሬ
የመለስን ራእይ ፣ በቅዠት መንዝሬ
በሀገር ዘራፊው ላይ ፣ አለሁ ቅኔ ስዘርፍ
በፍቅር ስሰለፍ።
እንደውም እዚህ ጋር
የመለስን ራእይ ፣ ለማስፈፀም ብሎ
ጠብ የሚፈጥርብን ፣ ጠብመንጃ አንጠልጥሎ
የነበር ፌደራል ፣ ጊዜ የቀየረው
ለወታደር ድጋፍ ፣ ይዞት የነበረው
ሚያሰክር መፈክር
"ፍቅር ያሸንፋል
የመለስ ራእይ ፣ ገና ይንሻፈፋል!
ህይወት ይቀጥላል ፣ ህወሐት ይጠፋል"
ሚል ፅሁፍ ነበረው
መለኮት ነው ሀይሉ
ጠብመንጃ ይጥላል ፣ ፍቅር ያስተማረው ።
።።።።።።
የሆነው ሆነና ፣ እንደምነህ ህውሀት
የመአቶች መአት
ከምፅአት ቀድመህ የመጣህ ምፅአት
በመለስ ራእይ
ራእይ የሌለው ፣ ትውልድ የፈለፈልክ
የወንዶች ሀገር ላይ ፣ ወንዶችን ያመከንክ
ግፍና ጭካኔህ ፣ የሚልቅ ከሰይጣን
የሚጫወትብህ ፣ ጥጋብና ቁንጣን
ተርበናል ስንል ፣ ጀሶ ምታነኩር
ባንዲራ ጨርቅ ነው ፣ ብለህ ምትደሰኩር
ኢሳያስ አፎርቄን
እንሰጭራቅ ስለህ ፣ ያሳየኸን መድረክ
አየህ ወይ ሰው ሆኖ ፣ ለፍቅር ሲማረክ
ሰማህ ወይ ስለሱ ፣ በፍቅር ሲተረክ
አየኸው ወይ ቤቱን
አየኸው ወይ ሀብቱን ፣
አየኽ ወይ ስለሱ ፣
ኑሮው ማንነቱን ፣ እየመሰከረ
ህዝቡን እና ሀገሩን እንዳልመዘበረ
ንጉስ ሆኖ ሳለ ፣ ህዝብ ሆኖ እንደኖረ
አየህ ወይ ስለሱ?
እንደውም እንደውም
እኔን ከዚህ ቀደም
በሰደፍ ቀጥቅጦ ፣ ያረገኝ ደም በደም
የሻብያ መንግስት
ተላላኪ ብሎ ፣ ጥርሴን ያረገፈው
የሆነ አጋዚ ፣ በቀደም ባለፈው
የህወሀት መንግስት
ተላላኪ ብሎ ፣ ነገር ሲፈልገኝ
ጥርሴን ቀድሞ አርግፎት ፣ በድዴ አስፈገገኝ።
።።።።
የሆነው ሆነና
እንደምነህ ህውሀት ፣ እኔ አለሁ በደህና
ጤና እንደነሳኸኝ ፣ ጤና ይንሳህና
አለሁ ተስፋ አዝዬ
ባንዲራ ደም እንጂ ፣ ጨርቅ አይደለም ብዬ።
አለሁኝ።"
#Share
Belay....
@lorate_tsegaye_gebremedihen
@lorate_tsegaye_gebremedihen
@lorate_tsegaye_gebremedihen
1.8K viewsedited  13:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-23 23:38:14 ህወሀት እና ጥበቡ
(በላይ በቀለ ወያ በበዕውቄ ስታይል)
.
.
መጀመሪያ ህወሐት ሳተ
ከቤተ መንግስት ተጐተተ፥
ህወሐት ከአራት ኪሎ ሲባረር
አነሆ በV8 ነበር
ትችት ስድብ ወረደበት
በሸበጥ የሚያውቁት ህዝቦች፣ በV8 ሲያዩት ሳቁበት።
ያኔ ህወሐት ተማረረ
ተማረረና ተመራመረ
ተመራምሮም አልቀረ
መብረቃዊ ርምጃ ጀመረ
ጅማሬውን እጅግ ወደደ
ተጀምሮ ሳይፈፀም ፣ መንከባለልን ለመደ
ያሳዝናል!
ማይጨርሰውን ጦርነት ፣ ጀምሮ ህዝቡን ማገደ።

#ከወደዱት_ሼር_ያድርጉ

@lorate_tsegaye_gebremedihen
@lorate_tsegaye_gebremedihen
@lorate_tsegaye_gebremedihen
2.4K viewsedited  20:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-23 21:36:34 "የተዘጋ ሀሳብ"

☞ እዚህ……
ሙዚቃ ከሌለው ስሜት ከማይሰጥ ቤት
ሀዘን ያልተለየው የከሰለን ህይወት
አዳፋ ለባሾች የቀን ሰራተኞች
ንቃቃታም ሴቶች ጉሊት ቸርቻሪዎች
አግዳሚ ወንበሩን ሚስኪኖች ከበውት
ማገር የሌለውን ጠባቡን ያፈር ቤት
በጠላ ባረቂ በጠጅ አጅበውት።
.
ከኑሯቸው በላይ ጫጫታቸው በዝቶ
ካዘናቸው ይልቅ ሳቃቸው ተሰምቶ
አንዱ ድሀ ዘፋኝ አንዱ አጨብጫቢ
አንድኛው ፎካሪ የጋባዥ አጃቢ
ባንድነት ተፋፍገው እየተማማሉ
ምግብ አልበላንም እየተባባሉ
ለድሃ እሚራራ ነፍስን ያደማሉ።
.
☞ እዚያ....
ጥቂት ሹማምንቶች የመተያያን ገንዘብ 'ሚጥሉበት
አጥተው
የግፍ ነጋዴዎች ንጋት ሳይቀድማቸው
ያልፈኩ አበቦች ከሚቆረጡበት
ለአይን የሚያሳሱ እንስቶች ካሉበት
ልክ በሌለው አፍ ዘፈኑ ተከፍቶ
የሚረግጠው ስፍራ እግራቸው ቦታ አጥቶ
በሬጌና በቫልስ፣ በቡጊ በቻቻ በሳንባና በራፕ፤
እንዲሁም በስክስታ ጭፈራቸው ደርቷል
የቀን ግፋቸውን ግድ የለሽ አይምሮን በውስኪ ያጥቡታል።
.
ከደጅ ከሀብታሞች ቡና ቤት፣ ድሆችም ባሉበት ካረቂ ቤቱ በር
ከገንዳ ላይ ለቅሞ ሆዱን የሚሞላ አንድ ሚስኪን ነበር።
.
☞ እኔ .....
ሀብትን ከማይጠሉት ለድሆች ከሚያዝኑት መካከል ላይ ቆሜ
እሰቃይ ነበረ...
እውነት በሚሰፍር ቀን በሚታይ ህልሜ።
.
☞ ገንዳ ለቃሚው....
ኑሯቸው ነው ብለህ ስለነዚህ ድሆች ስለምን ታዝናለህ
እኒህ ትንሽ ድሆች ሀብት ቢሞላቻው ብር ቢተርፋቸው
ከባንኮኒ ቆመው ከመጠጣት ሌላ ምንድን ነው ትርፋቸው?
ምንድን ነው ተስፋቸው ገንዳው ላይ ለቆመው?
.
እኒህስ ሀብታሞች ከውስኪ ቤት አልፈው
ከመግባት ውስኪ ቤት
አንዷን ቆንጆ ትተው ከማቀፍ ሌላ ሴት
አይምሮአቸው ሂዶ ደርሶ የሚያርፍበት
አዲስ ኬላ የለም ሰርተው የሚፈጥሩት።
.
ስለዚህ ግጥምህን እንዲህ ብለህ ዝጋው
እንደዚህ አትማው
ሰካራም ድሃና መጠን አልባ ሀብታም
ፍፃሜው አንድ ነው
ከባንኮኒ ቆመው ከአግዳሚ ተነስተው ውስኪ ለማድረግ ነው
አረቄውን ደፍተው።

ኤፍሬም ስዩም

#share
#Have_nice_night

@lorate_tsegaye_gebremedihen
@lorate_tsegaye_gebremedihen
@lorate_tsegaye_gebremedihen
1.5K views18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-19 22:23:25 #ዕለተ_ቅዳሜ_ፒያሳና_ቦሌ
(ኤፍሬም ስዩም)

ቀጭን ወገቧ ላይ
ከእንብርቷ በላይ ልብሷ ተንጠልጥሏል
የወርቅ መስቀሏ
ጡቶቿ መካከል ዘንበል ብሎ ወድቋል
መንገድ ላይ ያየኋት
የማላውቃት ሴት ናት።
ወዴት እንደምትሄድ ባሳቤ ገመትኩኝ
አንድ የቀጠራትን ወንደላጤ አሰብኩኝ
ሠባት እንቁላሎች
ግማሽ ኪሎ ሥጋ ... (ገዝቶ)
ከርሷ ጋር ካልሆነ
ቡና አልጠጣም ብሎ አሥሬ እያዛጋ
መጽሐፉን ከፍቶ
በሩን ክፍት ትቶ
መልሶ መላልሶ ሠዓቱን እያየ
የሚጠብቃት ሠው
ሐሳቤ ውል አለው
ምክንያቱም ቀኑ ቅዳሜ ነው።
-
እርሷ አለፍ እንዳለች
መሐሙድ ፊት ለፊት
አራዳ ሬሰቶራንት
አራት ጎረምሶች ሰባት ምግብ አዘው
ለመመገብ ሳይሆን
ምግቡን ለመጨረስ እጅጉን ተጣድፈው
በቆየ ጋዜጣ
የተጠቀለለ ምናምን አስቀምጠው
ፊት ለፊቴ አሉ
ምግቡን ሳያኝኩት ቶሎ መጉረሳቸው
አራት ሆነው ሳሉ ዝም ማለታቸው
ገባኝ ሁኔታቸው
ምክንያቱ ምንድን ነው?
ቀኑ ቅዳሜ ነው።
እግሬን ለማፍታታት እየተራመድኩኝ
ወደ ሆነ መንደር በድንገት ገባሁኝ
የሆነ በራፍ ላይ
ውስጥ ልብስ ያረገች
ልብስ አጠባ ውላ ትንሽ የደከመች
ፀጉሯን ልትሰራ
ጓደኛዋ ጭን ስር ሽጉጥ ልጥፍ ያለች
እግሯ ከፈት ያለ
ጡቷ ወፈር ዯያለ
የአንድ እጇን መዳፍ
በስተግራ በኩል የፀጉሯ ክፋል ላይ
የአንድ እጇን መዳፍ
ክፍት እግሮቿ መሃል
አንገቷ ወደላይ
ረፍት የሚመስል ሰማዩ ላይ ወድቋል
አይኗ ከሩቅ አልፏል
እፎይ . . . የሚል ፊደል ገላዋን በሞላ
እንደ ልጅ አቅፎታል
የዚህ ሁሉ ነገር
የዚህ ሁሉ ዉበት ምክንያቱ ምንድን ነው
ቀኑ ቅዳሜ ነው።
-
እዚህ መንደር ጫፍ ላይ
አንድ ያቧራ ሜዳ ከሩቅ ይታየኛል
እንደ መዝሙር ሆኖ
የሕፃናት ጩኸት ወደኔ ይመጣል
ከሜዳው መሃል ላይ አቧራው ይበናል
ሕፃናት ነበሩ አበቦች ነበሩ
ምሳቸውን ትተው
በጨዋታ ምሳ ጠግበው የሰከሩ
ምክንያቱ ምንድን ነው
ቀኑ ቅዳሜ ነው።
-
Oslo በረንዳው ላይ
አንድ ጥቁር ቡና ከተቆራጭ ጋራ
በቀኙ ጋዜጣ
ግራ እጁ ጣት መሃል ሮዝማን ሲጋራ
ቀልቡን ጋዜጣው ላይ
የሲጋራውን ጢስ ከጋዜጣው በላይ
ቡናውን ሲጎነጭ ንባቡን ሲያቆም ዐይኖቹ ውብ ሴት ላይ
እያቀያየረ
በልቡ ባሳቡ እያመነዘረ
Oslo በረንዳው ላይ ተቀምጦ ያለ
አንድ ጎልማሳ አለ።
ምሑር የሚመስል እንደዚህ ያለ ጎበዝ
ከኬክ ቤት በራፍ ላይ ሊቀመጥ የቻለው
ምክንያቱ ምንድን ነው?
ቀኑ ቅዳሜ ነው።
-
የሆነች ሕፃን ልጅ
የቅዳሜ ጠዋት ፀሐይ የሚመስል
ጉንጯ ላይ ፈገግታ በደማቁ ፅፋ ባጠገቤ አለፈች
ሠላሣ ማለቂያ
አርባ መጀመሪያ . . . አካባቢ ያለች
የተጠቀለለ የታሸገ ነገር በጇ ላይ የያዘች
የሕፃኗን መንገድ እየተከተለች
ጠይም ሴት አለፈች።
ለቅድሟ ሕፃን እናቷ ነች መሰል
(ይመስለኛል መሰል)
የሴቷ ባለቤት
የልጅቷ አባት
ትንሽ አመም አርጎት ሆሰፒታል ተኝቷል
ወይም . . .
የተጠቀለለው የታሸገው ነገር
የወይን የውስኪ ጠርሙስ ግን ከሆነ
ጠይም ቆንጆዋ ሴት
አንድ የተፋታችው አንድ የምትፈልገው
የሆነ ሰው አለ . . .
ትንሿን ሕፃን ልጅ የምታስተዋውቀው
እና . . .
የ’ርጅና ፍርሃቷን አብራ ምትጋራው።
አያገባኝ ነገር
ያገባኛል ብዬ ይህን ያሰብኩበት ምክንያቴ ምንድ ነው?
ያ ቀን ቅዳሜ ነው።
-
ይህንና ያንን
የግራ የቀኙን
ከፒያሳ መሐል እስከ ጣልያን ሠፈር . . .
አንዱን እያነሳሁ
አንዱን እየጣልኩኝ
በሐሳብ ሕንፃ ላይ አንዱ እየተሰራ አንዱ እየፈረሰ
ከልጅቷ ጋራ
የተቃጠርኩበት ሠዓቱ ደረሰ
መጣች ተገናኘን
ዮኧምያ ምሳ ቶምካ ቡናችን
የደንቡን አደረስን።
ልብሷን ሳታወልቀው ራቁቷን ሳልኳት
ዘወትር አንድ ቤት
ደንብ አይደለም ብዬ ቦሌ እንሂድ አልኳት
የተስተካከለ
ጥሩ አልጋ ያለው የማውቀው ቤት አለ።
ፒያሳን ለቀቅን . . .
ቦሌ ላይ ደረስን . . .
የቦሌ ቅዳሜ ያራዳን አይመስልም
የቦሌ ቆንጆ ሕልም ከፒያሳ ቅዥት አይስተካከልም
የቦሌ ኮረዶች
በቀለማት ብዛት ውበታም ቢመስሉም
ጣልያን ሠፈር መሐል
ፀጉር እየተሰራች ያስተዋልኳት ሴት ላይ
ጥፍሯ ላይ አይደርሱም
የቦሌ ቅዳሜ ያራዳን አይመስልም።
ቦሌን ታዘብኳትኝ
ቦሌን እርም አልኳትኝ
ቆንጆ አልጋ አለበት
ካልኩት መንገድ መሐል
አንድ የለቅሶ ድንኳን
ጎዳናውን ከድኗል።
ድንኳን ያ’ዘን ድንኳን
በ’ለተ ቅዳሜ በውበት በሕይወት ቀን
አብራኝ ያለችው ሴት
ተከተለኝ ብላ ወደ ኋላ ዞረች
እጆቿን ዘርግታ
አንድ ትንሽ ታክሲን ፒያሳ አዘዘች
ፒያሳ ደረስን
የቦሌውን ድንኳን እንዲያስረሳን ብለን
Sunshine ጎራ አልን . . .
ሙዚቃ
ሙዚቃ
ቢራ
ውስኪ
ቢራ . . .
ጫጫታ
ዳንኪራ
ዳንኪራ
ጫጫታ
ድንኳኑን ረሳን
ውበት ባህር ገባን
የዚህ ሁሉ ደስታ የዚህ ሁሉ ሐሴት . . .
ምክንያቱ ምንድን ነው?
ቀኑ ቅዳሜ ነው።
ያውም የፒያሳ
እውነት ለመናገር . . .
የቦሌ ቅዳሜ ያራዳን አይመሥልም
የቦሌም ቆንጆ ሕልም ከፒያሳ ቅዠት አይስተካከልም።
ያም ሆነ ይህ ግና
የዚህ ሁል ዉበት ምክንያቱ ምንድን ነው?
ቀኑ ቅዳሜ ነው

#Have_nice_night

@lorate_tsegaye_gebremedihen
@lorate_tsegaye_gebremedihen
@lorate_tsegaye_gebremedihen
1.7K viewsedited  19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-19 07:44:35 ነጋ ደግሞ
*
ነጋ ደግሞ ጎህ ቀደደ
አዲስ ተስፋ ተወለደ
ጽልመት አለፈና ብርሃን ተሰደደ
ጀመረ ግርግር
ዝምታዋን ለብሳ ባደረች ምድር
ከትናንት ያለፈን ዛሬን ልትሰፍር
ጀመረ ግርግር እውነትና ውሸት
ምስጋናና ትዝብት ውልደትና ህልፈት
እድገትና ውድቀት እንባና ፈገግታ
ጀመረ ሁካታ
ነጋ ደግሞ ጎህ ቀደደ
አዲስተስፋ ተወለደ
ጽልመትአለፈና ብ ርሃን ተሰደደ
አለቃና አላቂ መሪና ተከታይ
ጅምር ሊፈጽሙ በማለዳውጸሃይ
ጀመረ ግርግር
ከትናያደረን ዛሬን ልትሰፈር
ዝምታዋን ለብሳ ካደረቺው ምድር
እፎይ ያለውን እሪ ልታሰኘው
ወየውየሚለውን እፎይታ ልትሰጠው
ሰውሄደ መንገዱን በጨረቃ
የረሳውን ጽሃይቱን ያስታወሰቺውን
ዛሬን ሊደግመው የትናንትናውን
ጨንቆት የረሳውን ደስ የሚለውን
ደስ የማይለውን
ምንም የማታህል ምንም ነኝነቱን
ሰውሄደ መንገዱን
የትናንትናውን ዛሬ ላይሊ ደግመው
የአምና ውጥኑን ዘንድሮ ሊያሳካው
ሰው ሄደ መንገዱን
ነጋ ደግሞ ጎህ ቀደደ
አዲስተስፋ ተወለደ
ሰው ሄደ መንገዱን
ዛሬን ይሁን ብሎ የትናንትናውን

ኤፍሬም ስዩም

@lorate_tsegaye_gebremedihen
@lorate_tsegaye_gebremedihen
@lorate_tsegaye_gebremedihen
1.4K views04:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-18 22:16:06 ከሀገር በላይ ነፋስ
-------= ------

ሀገሬ ሆይ ስሚ...!

እኔ ባንቺ ሰማይ፤እኔ ባንቺ ምድር
መጠለያ አጥቼ፤ከሸለቆ ባድር
በረሃብ አለንጋ፤አንጀቴ ቢገረፍ
ባልችል ማንቀላፋት፤ባልችል እንኳን ማረፍ
አካሌ ቢቀጥን፤ፊቴ ቢገረጣ
ለገላዬ ልብስን፤ለእግሬ ጫማ ባጣ
ሳቄን ተቀምቼ፤ለቅሶ ቢሆን ቀኔ
ላንቺ አይሁን እንጂ...
ይሄ ሁሉ ስቃይ፤ምንም አይደል ለኔ!!

Jon

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@lorate_tsegaye_gebremedihen
@lorate_tsegaye_gebremedihen
1.4K viewsedited  19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-11 20:08:18 https://t.me/lorate_tsegaye_gebremedihen
2.8K views17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-08 06:02:14 https://t.me/YeGitem
2.7K viewsedited  03:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-04 08:49:39
1.9K views05:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ