Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬም ልጅ ነኝ 😊

የቴሌግራም ቻናል አርማ kompany2141 — ዛሬም ልጅ ነኝ 😊
የቴሌግራም ቻናል አርማ kompany2141 — ዛሬም ልጅ ነኝ 😊
የሰርጥ አድራሻ: @kompany2141
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 629
የሰርጥ መግለጫ

እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-03 22:53:28 አያምርብንም


ሞቱ ለሃጢኣት ስርየት ሆኖ
ሞቱ ለሠው ነፍስ ሰላም አስፍኖ
ሞቱ ህይወትን ለሁሉ አድሎ
በመስዋቱ እርቅ ይሁን ብሎ
የሁላችንን እዳ ጠቅልሎ
ብቻውን ሰርቶ ብቻውን ከፍሎ
ኑ ወዲህ ብሎ የእዳችን ከፋይ
ሲገላግለን ከአለም ስቃይ
እፎይ ማለትን በእርሱ አውቀን
በእምነት በመዳን ልጆች ተብለን
ሀጥያት ተገፎ ጽድቁን ለብሰነው
የተሰራልን የሚቀልብን እንዴት ሆኖ ነው?


አ ይ ቀ ል ብ ን ም

የለም አይሰራም ድኖ ዝምታ
እዳ ተከፍሎ በጎሎጎታ
እንዴት ይቻላል በምህረቱ
እብድ አለመሆን ተገኝቶ ፊቱ

አሳዩኝ እስኪ ፍቅሩን ተረድቶ
ፍቅሩን ጠጥቶ ከፍቅሩ በልቶ
በፍቅሩ ንዳድ ውስጡ ያልነደደ
ውዴ ነህ ብሎ በእርሱ ያላበደ
ልጅ ነህ ተብሎ ልጅ ነኝ ያላለ
ኧረ እሱ ማነው ችሎ ዝም ያለ?

የተገዛነው ሆኖ በደሙ
እረፍት አግኝተን በቅዱስ ስሙ
በፀጋው ድነን በእርሱ ስራ
ህይወት ገብቶብን ሞት እንዳንፈራ
በሞቱ ሽሮ ሀጥያታችንን
የድል ሲያደርገው ህይወታችንን
ዝም ማለቱ አያምርብንም
የተሰራልን አይቀልብንም።

ቤቲ ፋሬስ
21 viewsAbeni(Ab), 19:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 22:20:54
አንድ ትልቅ ሀገር ውስጥ የሀገሩ ንጉስ ነበር እና እዚህ ሀገር ውስጥ ይሄ ንጉስ ያስለመዳቸው አንድ ነገር አለ በየአመቱ እጣ የወጣለት የጠየቀውን ሁሉ ይደረግለታል እና ይሄ እጣ ደርሶ ለአንድ ሰው ወቶለት ሰውየውም በሚሊየን የሚቆጠር ብር ጠይቆ እንደጥያቄው ብር ተሰጠው።

በሌላኛው አመት እንደዚ እጣ ወቶ ለአንድ ሴትዮ ይደርሳታል ይቺ ሴት የፈራረሰ ቤት ውስጥ የምትኖር ወደ ቤቷ እንኳን ለመሄድ መንገዶቹ የፈራረሱ ናቸው የንጉሱም ጠባቂዎች ንጉሱ ምን እንዲያደርግልሽ ትፈልጊያለሽ አሏት?

ሌሎች ሰዎች መኪና ይሏት ጀመር ሌሎች ደሞ አንቺ ደሀ ነሽ ቤትሽ የፈራረሰ እና ጭቃ ነው ስለዚህ ብዙ ብር ጠይቂ እና በብሩ ቤትም ግዢ አሏት ነገር ግን ልጅቷ አስተዋይ እና ብልህ ነበረች ማንንም አልሰማችም ለንጉሱ ጠባቂዎች እኔ ምፈልገው ነገር አለ አለች ንጉሱ ወደ ቤቴ ይግባ ጠባቂዎች ደነገጡ እንዴት ብትደፍሪ ነው ንጉሱን የፈራረሰ ቤትሽ ውስጥ የተከበሩትን ንጉስ የምጠሪው በማለት ሊመቷት ሞከሩ ንጉሱ ግን በታላቅ ድምፅ እንዳይነኳት ተናገሩና ንጉሱ ላያደርግ ቃል አይገባምና ልጂቱ የወደደችውን ይደረግላታል እኔም እገባለው ቤቷንም ለንጉስ እንዲመች አድርጋቹ ስሩት በማለት አዘዙ የንጉሱም ጠባቂዎች ቤቷን ለንጉሱ እንዲመጥን አርገው ከተማ የሚያክል ቦታ ላይ በጣም ትልቅ ቤት ውስጡ ውጪው በወርቆች የተከበበ መንገዶች በአልማዝ በብር ያጌጡ ሆነው ተሰሩላት የዚህ ሁሉ ምክንያት ወደ ውስጥ የሚገባው የከበረ ስለሆነ ነው።

ታዲያ ይሄን ሁሉ ለምን አወራ ካላቹኝ በምንም አይነት ድካም ውስጥ ብትሆኑ ሀጥያት ውስጥ ብትሆኑ የአይሁድ አንበሳ የነገስታት ንጉስ #ኢየሱስን ወደ ውስጣቹ ጥሩት አስገቡት #ኢየሱስ ለእራሱ እንዲመች አድርጎ ይሰራቸዋል።

#ትኩረት_ሁሉ_ወደ_ኢየሱስ

JOIN
CHANNEL @KOMPANY2141
236 viewsAbeni(Ab), 19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 16:14:44
#ይራራልናል
የሚራራልን ደካማ ስለሆንን ነው፤ በኃጢአት ለመውደቅ በጣም ቅርብ ስለሆንን እንዳንወድቅ ይደግፈናል።

“ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም።”
— ዕብራውያን 4፥15

''ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው'' የሚለው ሃሳብ የሚያሳየን፥ ኢየሱስ ንፁህ መሆኑንና በእኛ ኃጢአት ምክንያት የመጣውን ፈተና በሙሉ መፈተኑን የሚያሳይ ነው። ለምን? መሰላችሁ፤ እኛ ተፈትነን አንዱንም ፈተና ማለፍ አንችልም፤ ኢየሱስ ግን በምድር ላይ መጥቶ ፈተናችንን ሁሉ ተፈተነ፤ ለዚህ ነው የሚራራልን፥ አሜን።

ኢየሱስ በድካማችን፣ ይራራልናል
መንፈስ ቅዱስ ደግሞ፥ በድካማችን ያግዘናል
እግዚአብሔር አብ ደግሞ እጁን ዘርግቶ ያወጣናል፤ አባታችን ነውና

በየትኛውም ፈተና ውስጥ ብትሆኑ ለብቻችሁ አይደላችሁም፤ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው። አሜን
ሼር #Share @FromHeavenTube Join Telegram channel
130 viewsSami Faithful to Jesus, 13:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 09:35:15
#ለእኛ_ተናገረን
በቅርብ ቀን ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የሐዋርያው የጳውሎስ መልዕክት ወደ ዕብራውያን ሰዎች፦

ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ፥
ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤
ዕብራውያን 1፥1-2
ከእኛ ጋር ማጥናት የምትፈልጉ ከስር ያለውን ሊንክ በመጫን መቀላቀል ትችላላችሁ፤
Telegram Channel:-

@FromHeavenTube

Telegram Group
@FromHeavenTube_KeSemayTube

Facebook Page:-https://www.facebook.com/104374359007352/posts/104374695673985/?substory_index=0&app=fbl

Facebook Group:- https://facebook.com/groups/866871167164483/
163 viewsSami Faithful to Jesus, 06:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 14:27:52
#የዘላለም_መዳን(eternal salvation)
ኢየሱስ የዘላለም ሕይወት ምንጭ ነው።
ለሚታዘዙለት ሁሉ የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው።
ዕብ 5፥9-10
Jesus is the Savior of the world. He became the source of eternal salvation for all who obey him. Heb 5፥9

ስለ እርሱም የምንናገረው ብዙ ነገር አለን፥ ጆሮቻችሁም ስለ ፈዘዙ በቃል ልንተረጕመው ጭንቅ ነው። ዕብራውያን 5፥11

About him we have many words to say, and hard to interpret, seeing you have become dull of hearing. Hebrews 5፥11

@FromHeavenTube Telegram Channel

@FromHeavenTube_KesemayTube Telegram Group
160 viewsSami Faithful to Jesus, 11:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 04:34:09 ዛሬም ልጅ ነኝ pinned a photo
01:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 04:30:34
በማንኛውም ጊዜ ሰይጣን ማስለቀስ በፈለገ ጊዜ መሳቅ ጀምር ይህ ለሰይጣን ህልውናውን ችላ እንዲል ልትሰጡት የምትችሉት ትልቁ ኀፍረት ነው።

መልካሙን እሁድ ተመኘሁላቹ

Whenever Satan wants to cry, start laughing. This is the greatest shame you can give Satan to ignore his existence.

I wish you a happy Sunday
JOIN AND SHARE
@KOMPANY2141
@KOMPANY2141
2.6K viewsAbeni(Ab), edited  01:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 19:15:25 "ደህንነታችን ዘላለማዊ ነው"

ደህንነታችን ዘላለማዊ ነው በሚለው ትምህርት ብዙውን ጊዜ የሚነሳው ተቃውሞ ይህ አስተምህሮ ሰዎች ድነታቸውን ስለማያጡ እንደፈለጉ እንዲኖሩ ፈቃድ ይሰጣል ወይንም በሀጥያት መኖር ይችላሉ የሚል ነው። ይህ ደግሞ ስናየው እውነት ቢመስልም መፅሀፍ ቅዱሳዊ አይደለም።
አንድ ሰው በእውነት በኢየሱስ ክርስቶስ ከተዋጀ ሀጥያትን ልምምድ ያደረገ ህይወት አይኖረውም።
መፅሀፍ ቅዱስ ደህንነት በፀጋ ብቻ፥ በእምነት ብቻ እና በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ እንደሆነ ይነግረናል።( ኤፌ ምዕ. 2)8፤ ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤9፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።
ሰው በእውነት በኢየሱስ ክርስቶስ ባመነበት ቅፅበት ድኗል እንደገናም ደህንነቱም ዋስትና አግኝቷል። ነገር ግን አንድ ሰው ድነት በእምነት ነው የምንቀበለው ካለ በኋላ ፀንቶ ለመኖር መስራት አለብን ቢል ይህ መፅሀፍ ቅዱሳዊ አይደለም።
ጳውሎስ በገላቲያ መልዕክቱ
" እንዲህ የማታስተውሉ ናችሁ? በመንፈስ ጀምራችሁ አሁን በሥጋ ትፈጸማላችሁን? "(ገላትያ 3:3)
በእምነት ከዳንን ድነታችን ፀንቶ የሚኖረው እና ዋስትና የሚያገኘው
# በእምነት ብቻ ነው። ድነታችንን በራሳችን ጥረት ማግኘት አንችልም። ስለዚህ ድነታችንን በራሳችን ጥረት ማፅናትም አንችልም።
እግዚአብሔር ብቻ ነው ድነታችንን ማፅናት የሚችለው። ( ይሁዳ 24)
የእግዚአብሔር እጅ ነው ማንም እንዳይወስደን አጥብቆ የያዘን።( ዮሀንስ 10:28~29)
የእግዚአብሔር ፍቅር ነው ማንም ከእርሱ ሊለየን እንዳይችል የደረገው ( ሮሜ 8:38~39)
በዘላለም ዋስትና(ያለመጥፋት) ላይ የሚነሳ ማንኛውም ተቃውሞ ድነትን በሰው ጥረት እና አቅም የሚፀና እንደሆነ ማመን ነው።ይህ ደግሞ በፀጋ መዳን ከሚለው ጋር የሚጋጭ ነው። ምክንያቱም የዳንነው በኢየሱስ መልካምነት እንጂ በእኛ መልካምነት አይደለም።(ሮሜ 4:3~8)... ድነታችንን ለማፅናት/ላለመጥፋት የሙሴ ሕግ መጠበቅ ወይንም መስራት አለብን ማለት የኢየሱስ ሞት ለእኛ ሀጥያት በቂ ክፍያ አይደለም ማለት ነው።
# የኢየሱስ ሞት ግን ላለፈው ፥ላሁኑ እና ለወደፊቱ ሀጥያታችን የተከፈለ ከ በቂ በላይ የሆነ ዋጋ ነው። (ሮሜ 5:8 ;1ቆሮ 15:3 ; 2 ቆሮ 5:21)
ታዲያ ይህ ማለት አንድ ክርስቲያን እንደፈለገው መኖር ይችላል እና ድነቱን አያጣም ማለት ነውን?
መፅሀፍ ቅዱስ ለዚህ ጥያቄ መልሱ ክርስቲያኖች እነሱ እንደፈለጉ ሊኖሩ አይችሉም የሚል ነው።
ክርስቲያኖች አዲስ ፍጥረት ናቸው።( 2 ቆሮ 5:17)
ክርስቲያኖች የመንፈስ ፍሬዎች የሚገለጥባቸው ናቸው።( ገላ 5: 19~21)
ክርስቲያኖች ሀጥያትን እንደልምድ አርገው ሊኖሩ አይችሉም።( 1 ዮሀ 3:6~9)
ሐዋሪያው ጳውሎስ ስለዚህ ነገር ሲናገር ፥ ( ሮሜ ምዕ. 6)
1፤ እንግዲህ ምን እንላለን? ጸጋ እንዲበዛ # በኃጢአት_ጸንተን እንኑርን?
# አይደለም ።2፤ ለኃጢአት የሞትን እኛ ወደ ፊት እንዴት አድርገን በእርሱ እንኖራለን?
ስለዚህ የዘላለም ዋስትና የሀጥያት ፈቃድ ማለት አይደለም። የእግዚአብሔር ፍቅር በክርስቶስ ለሚያምኑ ለዘላለም እንደሚኖሩ የሚያረጋግጥ ዋስትና ነው።የእግዚአብሔርን ውድ የድነት ስጦታ ማወቅ እና መረዳት ለሀጥያት ፈቃድ ከመስጠት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም።
( ሮሜ ምዕ. 6)14፤ ኃጢአት አይገዛችሁምና፤ ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደላችሁምና።15፤
የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን!!

✞ድነት ያገኘ ሰው ✞
እውነተኛ አማኞች ያገኙት ድነት በምንም ሊጠፋ የማይችል እንደሆነና እማኞች በእግዚአብሔር ፀጋ እና ኃይል በቅድስና በመኖር እስከ መጨረሻ እንደሚድኑና ድነታቸውን የማጣት ፍርሃት እንደማይዛቸው ቃሉ ያስተምራል
ድነት የእግዚአብሔርም ነፃ ስጦታ ስለመሆኑ በተደጋጋሚ ይናገራል፡፡ ሰዎችም በክርስቶስ ከማመን በስተቀር ለመዳን የሚከፍሉት ወይም የሚሰሩት ስራ የለም፡፡
የተቀበልነው ድነት ዳግም ልደትን መፅደቅን ልጅነትን አስገኘልን። ቲቶ 1፡11 ሮሜ 6፡23፤2ጢሞ 1፡9) ይሁንና በዚህ አዲስ ህይወት የተጀመረው ድነትን በተለያዩ ምክንያቶች ሊታጣ ይችላል የሚለው ጥያቄ መመለስ አለበት ለዚህ መፅሀፍ ቅዱሳዊ መልስ ለመስጠት ከሁለት አቅጣጫ ማየት ግድ ነው።
የተቀበልነው ደህንነት ዋስታና
ከእግዚአብሄር አቅጣጫ ፡- የሰዎችን መልካምነት ግምት ውስጥ ሳያስገባ በቸርነቱ ድነትን የሰጠ እግዚአብሄር በጊዜ ሂደት የሰዎችን ባህርይ ተንተርሰን ሃሳብ በመለወጥ በነፃ የተሰጠውን ድነት መልስ አይወሰደውም ፡፡(ፊሊ 1፡6)
ከሰዎች አቅጣጫ ፡- በዳግም ልደት ህይወት የተለወጠ፤ በቅድስና እንዲያድግና ወደ ኋላ የመመለስ ፈተናዎችን እንዲያሸንፍ የሚያስችለውን የመንፈስ ቅዱስ ዕርዳታ በየእለቱ የሚያገኝ፣ክርስቶስ በአብ ቀኝ ሆኖ የሚማለድለት ሰው ይህን ሁሉ ድጋፍ ከእግዚአብሄር እያገኘ ጌታን ሊክድ ወይም በአመፅ ሊኖር አይችልም (ሮሜ 8፡31-39)፡፡
በመጨረሻም የዘላለም ህይወት የሚጠፋ ሕይወት አይደለም ፤የዘላለም ህይወት ያገኘ ሰው የዘላለምን ሞት አይሞትም፡፡ (ዮሐ 3፡15፣ ዮሐ 16፡34፣ ዮሐ 5፡24) ከሞት ወደ ሕይወት ተሸጋገር እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም፡፡ (አንድ ጊዜ የተሻገረ ሰው ተመለሶ ወደ ፍርድ አያመጣም (1የሐ 5፡10-13) 1ጳጥ 1፡3-5) ።
በጌታ በኢየሱስ በማመን የተወለደ ሰው ከተወለደ በኋላ አለመውለድ ወይም መሞት አይችልም፡፡ ዳግመኛ በመወለድ አዲስ ፍጥረት የሆነው ሰው ተመልሶ አሮጌ ፍጥረት ሊሆን አይችልም (1ጴጥ 1፡23) (ያዕ 1፡18) (ዮሐ 1፡3) (2ቆሮ 5፡17)፡፡
የድነታችን ዋስትና እና ጥበቃ
ያዳነን የዘላለም ህይወት በጸጋው የሰጠን እግዚአብሔር እስከ መጨረሻ ሊያድነንና መንግስቱን ሊያወርሰን የታመነ ነው (ሮሜ 8፡29-30) ፣1ቆሮ 1፡8-9 ፣ፊል 1፡6) ፡፡
እግዚአብሔር ከእርሱ የሚለየን እንዳይኖር ይጠብቀናል (የሐ 10፤1-7 ፤10፡28-29 1ጴጥ 1፡5 ፤ ዕብ 13፡20-21 ፤ሮሜ 8፡37-39 ፡፡
ሰውን የማዳን ኃላፊነት የእግዚአብሔር ሲሆን ከድነት በኋላ ድነቱን ጠብቆ የመያዝ በድነታችን መኖር የሰዎች ኃላፊነት ነው፡፡ እግዚአብሔር ድነታችንን ጠብቆ ለመያዝ የሚያስችለንን ፀጋ ሰጥቶናልና።
ድነትን ያገኘ ሰው ኃጢያት እየሰራ አይኖርም (ዮሐ 3፡4፣2ቆሮ5፡18፣ ኤፌ 2፡10)፡፡
ድነትን ያገኘ ሰው በተሰጠው በእግዚአብሔር ፀጋ ይኖራል (ሮሜ 12፤1-2፣ ርሜ 10፡1-3)
የፅድቅ እወነታዎች
እግዚአብሔር ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስን በኛ ምትክ መስዋት በማድረጉ እኛ ነፃ ነን፡፡
ፅድቅ የሚገኘው በእምነት እንጂ በስራ አይደለም፡፡
እኛ የእግዚአብሄር ፅድቅ ነን፡፡ (2ቆሮ 5፡21)
ተገቢውን ቅጣት መቀበል የነበረብን እኛ ነበርን፡፡
ፅድቅ ዘላለማዊ እንጂ ጊዜአዊ ስጦታ አይደለም፡፡
በክርስቶስ ፀድቀናል
የፅድቅ አስፈላጊነት
# ሰው ሁሉ ኃጢተኛ በመሆኑ እና በራሱ ጥረት በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነትን ሊያገኝ ስላልቻለ፡፡
“በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢያተኞች እንደሆኑ እንዲሁ ደግሞ በአንድ መታዘዝ ብዙዎች ፃድቃን ይሆናሉ (ሮሜ 5፡19)፡፡

@lechrstos
319 viewsAbeni(Ab), 16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 01:26:32 የሰው ልጅ ኢየሱስን መከተል ያቆመ እለት መሞት ይጀምራል
እንደውም ይሞታል

አቤኔዘር
Channale @KOMPANY2141
Group @AGchurchs
የተመቻቹ ብቻ ሰዎችን Add እና Join በማድረግ ድጋፋቹን አሳዩን ተባረኩልን።
252 viewsAbeni(Ab), 22:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-09 19:40:45
Christian has no choice
Christian has no shortcuts
The Christian option is one and the same: Jesus Christ, the true way and the life !!

ክርስቲያን አማራጭ የለውም
ክርስቲያን አቋራጭ የለውም
የክርስቲያን አማራጭ አንድና አንድ ነው እርሱም እውነትም መንገድም ህይወትም የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው!!

መልካሙን ሰኞ ምሽት ተመኘውላቹ
Join And Share
Channel @KOMPANY2141
@KOMPANY2141
4.3K viewsAbeni(Ab), 16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ