Get Mystery Box with random crypto!

የአገልጋይ ብርሃኑ ገፅ

የቴሌግራም ቻናል አርማ preac — የአገልጋይ ብርሃኑ ገፅ
የቴሌግራም ቻናል አርማ preac — የአገልጋይ ብርሃኑ ገፅ
የሰርጥ አድራሻ: @preac
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 526
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የአገልጋይ ብርሃኑ ገፅ ነው።ዓላማዬ የተለያዩ መፅሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶችን ማካፈልና ማድረስ ሲሆን ምክሮችን፥አባባሎችን፥ፀሎቶችንና ትዝብቶቼን የማካፍልም ይሆናል።የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወደ ልቤ ያመጣውንና የተናገረኝንም እፅፋለሁ።ትውልዱን ወደ ኢየሱስ የሚያስጠጋውን የትኛውንም ነገር የምፅፍበት ገፄ ነው።በማንበብና ሼር በማድረግ ከአገልግሎቴ ጎን ይቁሙ።0984005562.

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-28 18:07:51
124 views15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 11:23:50
1.5K views08:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 11:32:58
2.0K views08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 16:52:39
285 views13:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 22:44:42
ትናንት በነበረን ልዩ መርሐግብር ጌታ የከበረበት ልዩ ነገር ሆኖልናል ።
271 views19:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 12:25:56
321 views09:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 16:30:39
ቅዱሳን ኑ አብራችሁን አምልኩ የእግዚአብሔርን ቃል እንማር ።
387 views13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 08:20:26 #ኢየሱስ_የአብ_መገለጥ

በአገልጋይ ብርሃኑ ታምራት

እግዚአብሔር የሚናገር አምላክ ነው።ተናጋሪነቱና ራሱን መግለጥ የሚወድ አምላክ መሆኑ ዋነኛ መገለጫው የእግዚአብሔር ቃል ተብሎ የተጠራው ኢየሱስ ነው።ዕብ.1:1-2፤ራእይ.19:13

ጌታ ኢየሱስ የአብ ክብርና መንፀባረቅ ደግሞም የባሕርዩ ምሳሌ ነው።ያልታየው ደግሞም የማይታየው አብ የተገለጠው በኢየሱስ ነው።ዕብ.1:1-2፤ዮሐ.1:18

አብን ማብራራት አትችሉም ኢየሱስ ግን ተርኮታል።ዮሐ.1:18

አብን ማየት አትችሉም ኢየሱስን ማየት ግን አብን ማየት ነው።ዮሐ.14:8-9

አብ በሰማይና በምድር ያለ አባትነት የተሰየመበት ነው ኢየሱስ ደግሞ የአብ አንድያ ልጅ ሆኖ ብዙ ልጆች ወደ ክብር የመጡበት ነው።ኤፌ.3:14-15፤ዮሐ.3:16፤ዕብ.2:10

አብ ከሁሉ በላይ የከበረ ነው ኢየሱስ ደግሞ ራሱ የአብ ክብር ነው።የሐዋ.7:55

አብ የሚታየውና የማይታየው ፍጥረት ሁሉ ፈጣሪ ነው ኢየሱስ ደግሞ ፍጥረታትን ሁሉ የፈጠረበት ኃይሉና አቅሙ ነው።ዮሐ.1:1-3፤ዕብ.1:1-3

ሁሉም ነገር የአብ ነው፤ ኢየሱስ ደግሞ የአብ የሆነው ሁሉ የእርሱ መሆኑን ተናግሯል።ዮሐ.16:15፤ዮሐ.17:10

አብ ያሰበውን ወልድ ያደርገዋል።አብ ያቀደውን ወልድ ይፈፅመዋል።ኤፌ.1:4-7

አብ ወልድን ያከብረዋል።ወልድም አብን ያከብረዋል።ዮሐ.17:1-2፣5

ሳይበላለጡ ሁሉን ይገዛሉ።ሳይቀዳደሙ ሁሉን ይይዛሉ።ሳይለያዩ እኩል ናቸው።ዮሐ.1:1፤ዮሐ.10:30

ይሄንን እውነት መንፈስ ቅዱስ ወደ አማኞች አደረሰው።ዮሐ.16:13-15

በአብ የታቀደው በወልድ የተሠራው በመንፈስ ቅዱስ የፀናው ደኅንነት አግኝቶናል።ኤፌ.1:4-14

ክብር ሁሉ ለሥሉስ ቅዱስ ይሁን።

23/09/2014 የጌታ ዓመት
2.3K views05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 08:11:46 #የኢየሱስ_ቅድምና ( #2 )

በአገልጋይ ብርሃኑ ታምራት

ጌታ ኢየሱስ በሥጋ የተገለጠው ከጊዜ በኋላ ከድንግል ማርያም ነው።ይሄ ግን ለመገለጥ ሥጋን መዋሃድን እንጂ ጅማሬን አያሳይም።ኢየሱስ አልፋ ነው። #የመጣውም_ከአለበት_ወደ_አለበት_እንጂ_ከአለበት_ወዳልነበረበት_አይደለም።እንዲህ ተብሎ እንደተፃፈ፦

ዮሐንስ 1
¯¯¯¯¯¯⁹ ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን #ወደ_ዓለም_ይመጣ_ነበር።
¹⁰ #በዓለም_ነበረ፥ #ዓለሙም_በእርሱ_ሆነ፥ #ዓለሙም_አላወቀውም።

#ወደ_ዓለም_በሥጋ_የመጣው_ኢየሱስ_በዓለም_ውስጥ_የነበረው_ነው። #የነበረው_መጣ።ያልታየው በሥጋ ተገለጠ።ዓለምን የፈጠረውም እርሱ ነው።በዓለምም ነበረ።ዓለም እንዲያየውና የማዳን ሥራውን ለመፈፀምም በሥጋ ተገለጠ።

በሥጋ ተገልጦ መመላለሱን፤ከሴት ተወልዶ የሰው ልጅ መባሉን ያዩ ሕልውናውን በሥጋ ከተገለጠበት ጊዜ ጀምረው እንዳይቆጥሩት "በመጀመሪያው ቃል ነበር…ቃልም ሥጋ ሆነ" በማለት የኢየሱስ ክርስቶስን ቅድምና አሰምቶ ዮሐንስ ተናገረ።

ያመንበት ኢየሱስ አልፋ ነው።ለፍጥረት መጀመሪያን የሰጠ መጀመሪያ የለሽ ቀዳማዊ እርሱ ነው።መጨረሻ የሌለው ዖሜጋም እርሱ ነው።ለፍጥረት ፍፃሜን ይሰጣል።እርሱ ግን ፍፃሜ የለውም።

በለበሰው ሥጋ ዘመን ቢቆጠርለትም በመለኮታዊ ማንነቱ መጀመሪያም መጨረሻም የለውም።
እንዲህ ተብሎ እንደተፃፈ፦
ዮሐንስ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵⁷ አይሁድም፦ ገና አምሳ ዓመት ያልሆነህ አብርሃምን አይተሃልን? አሉት።
⁵⁸ #ኢየሱስም፦ #እውነት_እውነት_እላችኋለሁ፥ #አብርሃም_ሳይወለድ_እኔ_አለሁ አላቸው።

ደግሞም ባለ ራእዩ ዮሐንስን እንዲህ አለው፦
ራእይ 1
¯¯¯¯¯¯¹⁷ ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ፦ አትፍራ፤ #ፊተኛውና_መጨረሻው_ሕያውም_እኔ_ነኝ፥
¹⁸ ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።

የኢየሱስ ሕልውና(መኖር) ዓለም ከተፈጠረ ዘመን ከተቆጠረ በኋላ ሳይሆን ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠር ነው።
ዓለም ሳይፈጠር ለኖረ፤ዓለምንና በዓለምን ያለውን ለራሱ ለፈጠረ ለጌታ ኢየሱስ ክብር ይሁን።አሜን።።

16/09/2014 የጌታ ዓመት
1.6K views05:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 19:53:49 #የኢየሱስ_ቅድምና

በአገልጋይ ብርሃኑ ታምራት

የኢየሱስ ሕልውና የጀመረው በድንግል ማርያም ማኅፀን አይደለም። #ኢየሱስ_መጀመሪያ_ነው_እንጂ_መጀመሪያ_የለውም።ጊዜን የፈጠረ እርሱ ነውና ዘመን አይቆጠርለትም።

ዮሐንስ ወንጌሉን ሲጀምር የሚሰብከው ኢየሱስ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት እንደነበር በመናገር ይጀምራል።

"በመጀመሪያው ቃል ነበር" በማለት በመጀመሪያ ያለው ጊዜ የመለኮትን ቅድምና ለመናገር ነው።በሥጋ መገለጥ ከዘመን ኋላ የተከናወነ ሲሆን የኢየሱስ ሕልውና ግን ከዘመን ዘመናት በፊት ዘመን የሚባል ቆጠራ ሳይኖር፤ዓለማት ገና ሳይፈጠሩ ነው።

#ኢየሱስ #ቃል_የተባለው_በሁለት_ምክንያት_ነው።

#አንደኛ፦ የመሆን(የኲነት) ስሙ ነው።ማለትም ለአብ ቃሉ ነው።አብ የሚናገረው በኢየሱስ ቃልነት አማካኝነት ነው።በአጭሩ ኢየሱስ የአብ ቋንቋው ነው።የሰው ሁሉ ቃል ዝርው(በአየር ተጭኖ ወደ ጆሮ የሚደርስ ከዛም የሚበተን) ሲሆን ኢየሱስ ግን ለአብ አካል ያለው ቃሉ ነው።እንዲህ ተብሎ እንደተፃፈ፦
“በደምም የተረጨ ልብስ ተጐናጽፎአል፥ #ስሙም #የእግዚአብሔር_ቃል ተብሎአል።”
— ራእይ 19፥13

#ሁለተኛው፦ ቃል የተባለው የአብ መገለጥ ስለሆነ ነው።አብን ያየው ማንም የለም።ኢየሱስ ግን አብን ገለጠው፥ተረከው፥አብራራው።ስለዚህ በልብ ያለ ሀሳብ በቃል ሲነገር እንደሚገለጥ እንዲሁ ኢየሱስ የአብ መገለጥ ነው።ኢየሱስ የአብ መልክ፥የባሕርዩና የክብሩም መንፀባረቅ ነው።እንዲህ ተብሎ እንደተፃፈ፦

ዕብራውያን 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¹ ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ፥² ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት #በልጁ_በዚህ_ዘመን_መጨረሻ_ለእኛ_ተናገረን፤³ #እርሱም #የክብሩ_መንጸባረቅና #የባሕርዩ_ምሳሌ_ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤

ስለዚህ ኢየሱስ የአብ ቃሉ ነው።አንድም አብ የሚናገርበት፥አንድም አብ የተገለጠበት ነውና።

ይቀጥላል………

15/09/2014 የጌታ ዓመት
1.5K views16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ