Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና አቶ ግርማ የሺጥላ ላይ በተቃጣው ጥቃት ከእርሳቸዉ ጋር ሌሎች 4 ሰዎችም ህይወታቸውን | LEYU NEWS

ሰበር ዜና

አቶ ግርማ የሺጥላ ላይ በተቃጣው ጥቃት ከእርሳቸዉ ጋር ሌሎች 4 ሰዎችም ህይወታቸውን አጥተዋል

ከመሃል ሜዳ ወደ ደብረብርሃን በመጓዝ ላይ ሳሉ ጥቃቱ መፈጸሙን የክልሉ መንግስት አስታዉቋል


በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በተከበሩ አቶ ግርማ የሺጥላ፣ በግል ጥበቃዎቻቸው እና በቤተሰቦቻቸው ላይ የመንግሥትና የድርጅት ሥራዎችን በአካባቢው ላይ ሠርተው ከመሃል ሜዳ ወደ ደብረ ብርሃን እየመጡ በነበረበት ሰዓት መንዝ ጓሳ ላይ በታጠቁ ኢ-መደበኛ ኃይሎች ጥቃት ተፈጽሟል፡፡

በዚህም አቶ ግርማ የሺጥላን ጨምሮ እስካሁን በደረሰን መረጃ የአምስት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡ በደረሰው ልብ ሰባሪ ጥቃት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰማውን መሪር ሐዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጿል፡፡

እንዲህ አይነት አጥፊዎች እያደረሱት ያለው መረን የለቀቀ የሽብር ድርጊት ክልሉን እየመራ ያለውን መንግሥትና መላውን ሕዝብ የበለጠ ሊያጠናክር እንጂ በጥፋት ሃይሎች ሴራና ፍላጎት የሚሳካ ምንም አይነት ተልዕኮ የለም፡፡

ስለሆነም ይህንን የሽብር ሥራ እየሠሩ ያሉ እንዲህ አይነት ኃይሎች ላይ የክልሉ መንግሥት የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል፡፡ የጥቃቱን አድራሾችም ለሕግ ያቀርባል፡፡ ማንኛውም በእንደዚህ አይነት ድርጊት የተሳተፉ ኀይሎችንንና ተባባሪዎችን ሁሉ ከያሉበት ለሕግ በማቅረብ አስፈላጊው ፍትሕ እዲረጋገጥ ይደረጋል ሲል የክልሉ መንግስት አስታውቋል።

@Leyu_News
@Leyu_News