Get Mystery Box with random crypto!

የ5 አመቱን ህፃን አፍኖ በመውሰድ የ1.5 ሚሊዮን ብር ክፍያ የጠየቀው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ! | LEYU NEWS

የ5 አመቱን ህፃን አፍኖ በመውሰድ የ1.5 ሚሊዮን ብር ክፍያ የጠየቀው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ!


የአጋች ታጋች የወንጀል ጉዳይ ልፋትን የጠየቀ አዲስ አበባን ጨምሮ አራት ከተሞችን ያደረሰ እንደሆነ ተገልፆል፡፡

ህፃኑ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የጠቆመ ሲሆን በህፃኑ እገታ ዋና ወንጀል ፈፃሚ የሆነው አማኑኤል ተክላይ የተባለው ግለሰብ ቤተሰባዊ ጉዳይን ምክንያት በማድረግ  የ5 ዓመቱን ህፃን ናታኒ ጎይቶምን ሚያዚያ 3 ቀን 2015 ዓ/ም አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው አለም ባንክ ስድስት ጎጆ ከሚባል አካባቢ ከሚገኘው የህፃኑ ወላጆች ቤት አፍኖ በመውሰድ 1.5 ሚሊዮን ብር ካልተከፈለው ልጁን እንደሚገድለው ይዝታል፡፡

የህፃኑ መታገት መረጃው የደረሰው አዲስ አበባ ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ጋር በጥምረት ባከናወነው ብርቱ የምርመራና የክትትል ተግባር ሦስት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ህፃኑን ለወላጆቹ ማስረከቡን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ወንጀል ፈፃሚዎቹ ከአርባ ምንጭ ቀጥሎ አዋሳ ከዚያም አዳማ ከተማ  እየተዘዋወሩ አድራሻቸውን ለማጥፋት ጥረት ቢያደርጉም የፖሊስ የክትትልና የምርመራ አባላት 24 ሰዓት ባደረጉት ጠንካራ ክትትል እና ምርመራ ሚያዝያ 14 ቀን 2015 ዓ/ም ቢሾፍቱ ከተማ ሸማኔ ሜዳ አካባቢ ህፃን ናታኒም ጎይቶም ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስበት ማግኘታቸው ታውቋል፡፡ ተጠርጣሪው አማኑኤል ተክላይ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ለፖሊስ በሰጠው ቃል የህፃኑ አክስት ገንዘብ ስለወሰደችበት ብሩን ለማስመለስ ወንጀሉን እንደፈፀመ አስረድቶ ባልጠቀቀው ሁኔታ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ተናግሯል።

@Leyu_News
@Leyu_News