Get Mystery Box with random crypto!

ወደ ትግራይ የየብስ ጉዞ ተጀመረ። ' ሰላም ባስ ' ከአዲስ አበባ  ወደ መቐለ / ከመቐለ ወደ አ | LEYU NEWS

ወደ ትግራይ የየብስ ጉዞ ተጀመረ።

" ሰላም ባስ " ከአዲስ አበባ  ወደ መቐለ / ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ ሲሰጠው የነበረውና በጦርነቱ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የትራንስፓርት አገልግሎት ጀምሯል።

ከሁለት ዓመታት በኋላ የሰላም ባስ የመንገድ ትራንስፖርት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ጉዞ አድርጓል።

ከዚህ በተጨማሪ በዛሬው ዕለት 51 ተጓዞችን በመያዝ ወደ አዲስ አበባ አገልግሎት መስጠት ጀመሩን ለማወቅ ተችሏል።

ድምፂ ወያነ ፤ አገልግሎት መጀመሩን ተከትሎ ትኬት ሲቆርጡ አገኘኃቸው ያላቸው ደንበኞች ፥ ወደ አዲስ አበባ የየብስ ትራንስፖርት በመጀመሩ ደስተኞች መሆናቸውን በመግለፅ ወደ ሌሎች አጎራባች ክልልሎችም ተመሳሳይ አገልግሎት ቢጀመር ሰላሙን ይበልጥ እንደሚያጠናክር ገልፀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከ " ሰላም ባስ " የትራንስፖርት አገልግሎት ባገኘው መረጃ በየቀኑ ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ እና ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ ጉዞ የተጀመረ ሲሆን ጉዞው የሚደረገው #በአፋር በኩል ነው።

@Leyu_News
@Leyu_News