Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የነዳጅ ማደያ ድርጅቶች በሙ | LEYU NEWS

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የነዳጅ ማደያ ድርጅቶች በሙሉ ጥብቅ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

ከሚያዝያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ ተጠቃሚ ለሆኑ አካላት በሙሉ የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ሥርዓት ብቻ እንደሚካሄድ ያሳወቀዉ ንግድ ቢሮዉ በጥሬ ገንዘብ ክፍያ መፈጸም የተከለከለ መሆኑን አሳዉቋል፡፡

ከኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ውጪ በተለይ በጥሬ ገንዘብ ክፍያ መፈፀም የተከለከለ በመሆኑ ቢሮው በዕለቱ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል ነዉ ያለዉ፡፡ይህ በመሆኑም ከወዲሁ በቂ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ለማንኛውም የነዳጅ ተጠቃሚ አካላት የነዳጅ ሽያጭን በኤክትሮኒክስ ሥርዓት ብቻ እንዲያስተናግዱ አሳስቧል፡፡

@Leyu_News
@Leyu_News