Get Mystery Box with random crypto!

አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን በሱዳን የተፈጠረውን ችግር የኢትዮጵያ ጣልቃገብነት እንዳለ አስመስለው የ | LEYU NEWS

አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን በሱዳን የተፈጠረውን ችግር የኢትዮጵያ ጣልቃገብነት እንዳለ አስመስለው የሚያናፈሱት መረጃ መሰረተ ቢስ ነው- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን በሱዳን ግጭት የኢትዮጵያ ጣልቃገብነት እንዳለ አስመስለው የሚያናፈሱት መረጃ መሰረተ ቢስ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም÷ ኢትዮጵያና ሱዳን በመንግስታት መለዋወጥ ያልዋዥቀ ጽኑ ወዳጅ ጎረቤት ሀገራት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ሱዳን ካጋጠማት ወቅታዊ ፈተና እንድትወጣ ኢትዮጵያ በየትኛውም ሁኔታ ከሱዳናዊያን ጎን መሆኗንም አረጋግጠዋል።

ያም ሆኖ አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን በግጭቱ የኢትዮጵያ ጣልቃገብነት እንዳለ አስመስለው የሚያናፈሱት መረጃ የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ወዳጅነት የማይመጥንመሰረተ ቢስና ሀሰተኛ መሆኑን ተናግረዋል። ይህን ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት በሱዳን የተፈጠረውን ችግር አካባቢያዊ ከማድረግ የመነጨ ፍላጎት መሆኑን ነው የገለጹት።

የኢትዮጵያ መሪዎች ከቀዳማዊ አጼ ኅይለሥላሴ ጀምሮ እስከ ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አሕመድ ሱዳን ያጋጠሟትን ቸግርች በሰላም እንዲፈቱ ጉልህ ሚና መጫወታቸውን አስታውሰዋል።
@Leyu_News
  @Leyu_News