Get Mystery Box with random crypto!

የዝነቱ ነብይ በአንድ ወቅት ነብዩ #ﷺ ቢላል ኢብኑ ረባህን ከኃላው በፍቅር ስሜት አይኑን በመሸ | ለሙስሊሟ እህቴ

የዝነቱ ነብይ
በአንድ ወቅት ነብዩ #ﷺ ቢላል ኢብኑ ረባህን ከኃላው በፍቅር ስሜት አይኑን በመሸፈን እቅፍ አድርገው ይይዙትና ድምፃቸውን ቀይረው..."እኔ ማን ነኝ"?
ቢላል (ረ.ዐ) :- ዑመር (ረ.ዐ) ነህ?
ነብዩ #ﷺ :- አይደለሁም
ቢላል (ረ.ዐ) :- አቡብክር (ረ.ዐ) መሆን አለብህ?
ነብዩ #ﷺ :- አሁንም ተሳስተሃል
ቢላል (ረ.ዐ) :- በቃ ዑስማን (ረ.ዐ) ነህ?
ነብዩ #ﷺ :- አላወቅከኝም
ቢላል (ረ.ዐ) :- ዓልይ (ረ.ዐ) ነህ ማለት ነው... እያለ
ያቀፈውን ሰው ማንነት ሲጠይቅ ይቆያል። ከዚያም
ረሱል #ﷺ ለቀቅ አደረጉትና ከፊት ለፊቱ በመምጣት "ቢላል ሆይ! እውነት እኔ መሆኔን አላወቅክም ነበር እንዴ"? ሲሉ ጠየቁት ቢላልም "የአላህ መልእክተኛ ሆይ!" በደንብ አውቄዎታለሁኝ ነገር ግን ለረጂም ጊዜ እንድታቅፉኝ ስለፈለኩኝ ነው ሲል መለሰላቸው።
ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙ አለይከ ያ ረሱሊላህ
ሳኒ & መሀመድ
https://t.me/lemuslimuaehte