Get Mystery Box with random crypto!

ዒማሙ አህመድ መሆን ካቃተህ አቡል ኸይሰም ሁን የታላቁ ዒማም አህመድ ዒብኑ ኸንበል ልጅ | ለሙስሊሟ እህቴ

ዒማሙ አህመድ መሆን ካቃተህ
አቡል ኸይሰም ሁን

የታላቁ ዒማም አህመድ ዒብኑ ኸንበል ልጅ የሆነው አብደሏህ እንዲህ ሲል ይተርካል;

አባቴ ብዙ ጊዜ "አላህ ሆይ ለአቡ ኸይሰም ማረው, ለአቡል ኸይሰም ዕዘንለት" ሲል እሰማው ነበር።

አባቴ ሆይ አቡል ኸይሰም ማን ነው ብዬ ጠየቅኩት

"ከገጠሬዎች የሆነ አንድ ሰው ነው ፊቱን ራሱ አይቼው አላቅም።
ግን እነዝያ ያለፉት በሆኑ ስገረፍባቸው በነበሩት ሌሊቶች ውስጥ አንድ ቀን መግረፊያ ክፍል አስገብተው አስቀመጡኝ ሳለሁ; የሆነ ሰው ጀርባዬን መታ አረገኝና => {አህመድ ዒብኑ ኸንበል አንተ ነህን } አለኝ
አዎን አልኩት
=> {ታቀኛለህን }ሲለኝ
አላቅህም አልኩት

{እኔ አቡል ኸይሰም የተባልኩ የገጠር ሰው ነኝ, ኸምር እጠጣለሁ, የሰው ንብረትም ዕቀማለሁ, በዚህ ድርጊቴ መንግስት ፊት ቀርቤ አስራ ስምንት ሺህ ግርፋት በተለያዩ ጊዜያት ተገርፌያለሁ።
ይህ ሁሉ ስገረፍ ግን በሸይጣን መንገድ ላይ ሆኜም እችለው ነበር። አህመድ ሆይ አንተ ግን በአላህ መንገድ ላይ ነህና ሰብር አድርግ አለኝ።

ከዝያ በኋላ አስረው ሲገርፉኝ አንዲትን ግርፋት ባረፈችብኝ ቁጥር የአቡል ኸይሰም ንግግር ትዝ ይለኝና በውስጤ
{አህመድ ሆይ በአላህ መንገድ ላይ ነህና ሰብር አድርግ } እል ነበርኩ

አህመድ ዒብኑ ኸንበል መሆን ካቃተህ አቡል ኸይሰም ሁን

ምንም እንኳ ውድቅ የሆነ ነገር ላይ የተዘፈቅክ ብትሆንም የዕውነት ባልተቤቶችን ውደዳቸው

ምንም እንኳ በወንጀል የሰመጥክ ብትሆንም ደጋጎችን ውደዳቸው

ይ ላ ሉን share
┏━ ━━━━ ━┓
@DinisNesiha
┗━ ━━━━ ━┛