Get Mystery Box with random crypto!

አብሽር ይደረሳል ከስጋህ ልቀህ ለነብስህ እደር፣ ወትሮውንም ብሂሉ ' | ለሙስሊሟ እህቴ

አብሽር ይደረሳል



ከስጋህ ልቀህ ለነብስህ እደር፣ ወትሮውንም ብሂሉ " ስጋ ባዳ ነው " አይደል የሚለው ?
በውስጥህ ከተጧጧፈው የሞት ሽረት ትንቅንቅ፣ የሞራል ልዕልናህን ከፍ ለሚያደርግልህ፣ ውሎ አድሮም ዋጋ ለማያስከፍልህ ሀሳብ አድላ። ጭላጭ ስሜትን ከማነፍነፍ ተቆጥበህ፣ እንደባህር ሰርጎ ፣እንደተራራ ለሚፀና እሴት ግንባታ ታትር
ወደ ግብህ ለመድረስ በምታደርገው ግስጋሴ ፣ ትዕግስት እጅግ ጉልህ ሚናን ይጫወታል፣ በመታገስህ ውስጥ ያለው መራር ጣዕም፣ ቀጥሎ የሚመጣውን ጣፋጩን የድል ጣዕም አብሳሪ ነው።
አይዞህ በርታ
አይዞህ ፅና
አይዞህ ታገስ
ምንም ቢያደክም፣ የቱንም ያህል ቢሰለች፣ እመነኝ አስካልቆምክ ድረስ መድረስህ አይቀሬ ነው ።

“ታገስም፣ መታገስህም በአላህ እገዛ እንጂ በሌላ አይደለም ” ኢስራእ (17)