Get Mystery Box with random crypto!

አለ_ህግ🔵Ale_Hig

የቴሌግራም ቻናል አርማ lawsocieties — አለ_ህግ🔵Ale_Hig
የቴሌግራም ቻናል አርማ lawsocieties — አለ_ህግ🔵Ale_Hig
የሰርጥ አድራሻ: @lawsocieties
ምድቦች: ብድር, ግብሮች እና ህጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.97K
የሰርጥ መግለጫ

#አለ_ህግ🔵Ale_Hig ነፃ የህግ የማማከር አገልግሎት፣የተለያዩ ህጎች፤ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ ክሶች፣ የውል ፎርሞች፤ መፅሐፍቶች፣ https://www.youtube.com/@Lawsocieties ሁሉንም ሕጎችና ባለሙያዎች እዚሁ ያገኛሉ🔴 All in one, for All. መሰረታዊ የህግ መረጃ እውቀት፤ ሀብት እና ሀይል ነው @LawsocietiesBot / lawsocieties@gmail.com

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-30 12:56:50
ዳኛ ከስራ የሚነሳበት አግባብ በሕግ ተቀምጧል።

አብዛኛዉ ዳኛ ፕሮፈሽናል ፤ ስራዉን አክብሮ የሚሰራ ነዉ። ዳኞች የችግር አካል ናቸዉ ብሎ በሙሉ መፈረጅ ትክክል አይደለም። ዳኞ ከሥራ የሚነሳበት አግባብ በሕግ ተቀምጧል። ዳኛ አንዴ ከተሾመ በኋላ የሕግ ጥበቃ አለዉ። ይኸ የዓለም አቀፍ መርህ አካል ነዉ።

በስሜት ተነሳስቶ ዳኛን ከሥራ ማስነሳት ትክክል አይደለም።

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክብርት ወ/ሮ መኣዛ አሸናፊ ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም በፋና ቴሌቪዥን ከሰጡት ቃለ-መጠይቅ የተወሰደ
በደሳለኝ ከበደ
https://t.me/lawsocieties
2.1K viewsLawyer Mike የህግ ባለሙያ, edited  09:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 17:22:23 በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የማይገደቡ መብቶች
።።።።።።። ።።።።።።።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መንግስት የዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥ ሰብአዊ መብቶችን እንደአስፈላጊነቱ የሚገድቡ ህጎችን የማውጣት ስልጣን የሚያገኝበት አዋጅ ነው። የኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት በፌዴራል ደረጃ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ የሚከተሉትን ሕጋዊ ምክንያቶች አስቀምጧል።

1. የውጭ ወረራ ሲኖር

11. ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል እና በመደበኛው ህግ የማስከበር ስርዓት መቆጣጠር የማይቻል የሕግና የሥርዓት መፈራረስ ሲኖር

III. የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም

V. ተላላፊ በሽታ ሲመጣ ከላይ በተገለጹት ሁኔታዎች ውስጥ መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጥቶ የዜጎችን መብት ይገድባል። ነገር ግን እንደየቦታው አንዳንድ ሰብአዊ መብቶች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ እንኳን በፍፁም ሊጣሱ አይችሉም።

Non-Derogable Rights in a State of Emergency

A state of emergency is a circumstance in which a government is given the authority to enact laws that would limit essential human rights to ensure the safety and security of its citizens. The FDRE Constitution provides the following legitimate reasons to declare a state of emergency at the federal level:

I. external invasion
II. a breakdown of law and order which endangers the Constitutional order and which

be controlled by the regular law enforcement agencies and personnel,

III. a natural disaster

IV. an epidemic

In the above circumstances, the government enacts a state of emergency and it will derogate or limit its citizens' rights. However, depending on the jurisdiction, some human rights cannot be derogated even in a state of emergency.
#AleHig.... #lawsocieties #Share
https://t.me/lawsocieties
2.8K viewsEntrust ETC, edited  14:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 07:17:39 https://t.me/lawsocieties
#አለህግ #AleHig
@AleHig @Lawsocieties
https://t.me/AleHig
#አለ_ህግ፣ #Ale_Hig
የማማከር አገልግሎት፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ ክሶች፣ የውል ፎርሞች፤ መፅሐፍቶች ሁሉንም ሕጎችና ባለሙያዎች እዚሁ ያገኛሉ All in one, for All. መሰረታዊ የህግ መረጃ እውቀት፤ ሀብት እና ሀይል ነው።

contact us: @LawsocietiesBot or
email us: lawsocieties@gmail.com
3.0K viewsLawyer Mike የህግ ባለሙያ, edited  04:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 20:35:31 ስለ ቼክ ይርጋ ጊዜ
።።።።።። ።።።።።።።
ቼክ የወጣበት ቀን ከግምት ሳይገባ በቼክ ላይ ከተፃፈው ቀን አንስቶ በሚከተሉት 6 (ስድስት) ወራት ውስጥ እንዲከፈል ባንክ መቅረብ እንዳለበት በንግድ ሕግ ቁጥር 855 ሥር ተመልክቷል፡፡

በንግድ ሕግ ቁጥር ቁጥር 881(1) ሥር ደግሞ በቼክ የሚገደዱ ሰዎች ላይ ቼኩን የተቀበለው ሰው ክስ ማቅረብ የሚችለው ቼኩን ለክፍያ ባንክ ለማቅረብ የተወሰነው ጊዜ ካለፈ ጀምሮ እስከ (6) ስድስት ወር ድረስ ነው፡፡
በመሆኑም ቼክ የተቀበለ ሰው፣ ቼክ ሰጪው ላይ የፍትሀ-ብሄር ክስ ማቅረብ የሚችለው ቼኩ ላይ ከተፃፈው ቀን አንስቶ በ 1 (አንድ) ዓመት ጊዜ ውስጥ ነው፡፡
3.1K viewsEntrust ETC, edited  17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 13:21:46
የአዲስ አበባ የህግ ምሩቃንን ያገለለው የስልጠና እና ስራ ዕድል
የኢትዮጵያ ፍትህ ስርዓት አዳዲስ የህግ ምሩቃንን በዳኝት እና በዐቃቤ ህግነት አሰልጥኖ የሚቀጥር ነው። የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ ሰልጣኞች በቀጥታ የፍትህ ስርዓቱን ከመቀላቀላቸው በፊት የተግባር ልምምድ እንዲያገኙ ማስቻል ነው። 

የ አዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑ ተመራቂዎች  “በአዲስ አበባ የፍትህ አካላት የቅድመ ስራ ስልጠና ተቋም ባለመኖሩ ዓቃቤ ህግ ወይም ዳኛ ሆነው ለመሥራት መቸገራቸውን ይናገራሉ። ወደ ክልልሎች ሲሄዱም ስልጠና ለማግኘት የነዋሪነት መታወቂያና ቋንቋ እንደ ቅድመ ሁኔታ በመቀመጡ ስልጠናውን ማግኘት ሳይችሉ ይቀራሉ።
በተጨማሪም ከክልሉ ነዋሪ ውጪ እድሉን እንደማይሰጡና ቅድሚያ ለክልሎቹ ተመራቂዎች እንደሆነም ይነገራቸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ "አዲስ አበባ የራሷ የሆነ የፍትሕ አካላት ማሰልጠኛ ተቋም ባይኖራትም ከፌደራል የፍትህ እና የህግ ምርምር ተቋም በመቀናጀት ስልጠናው እየሰጠን መጥተናል፣ አሁንም እንሰጣለን። በመሆኑም ተቋም አለመኖሩ ችግር የሚያስነሳ ጉዳይ አይደለም” ባይ ናቸው። ከተማዋ የራሷ የሆነ የፍትህ አካላት የቅድመ ሥራ ማሰልጠኛ ተቋም እንዲኖራት እየተሰራ እንደሆነም ጠቁመዋል።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ  የህግ ባለሙያ “አንድ የህግ ባለሙያ  ስልጠና ካልወሰደና በዓቃቤ ህግነት ወይም በዳኝነት ተቀጥሮ የመስራት አድሉ ጠባብ ነው ለዚህ ችግር መፍትሄው  አዲስ አበባ የራሷ የሆነ የህግ የቅድመ ስልጠና ማዕከል ማቋቋም ወይም እንኳን አዲስ አበባ የፌደራል መንግስት መቀመጫ እስከሆነች ድረስ ነዋሪዎቿ በፌደራል የፍትህ ማሰልጠኛ ተቋማት ውስጥ ገብተው ስልጠናውን እንዲወስዱ ሊፈቀድላቸው ይገባል" ብለዋል።
አዲስ ዘይቤ
via #tikvahethmagazine
@lawsocieties
3.5K viewsLawyer Mike የህግ ባለሙያ, edited  10:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 09:49:56
https://t.me/lawsocieties
የዳኞች ዓለም አቀፍ ሕግ ዕውቀት ዝቅተኛ መሆን የባለሥልጣናትን ተጠያቂነት ዝቅተኛ እንዳደረገው ተገለጸ
3.1K viewsAsrat, edited  06:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 09:12:57 መልካም የእረፍት ቀን እና እሁድ ይሁንላችሁ
የመልካምነት ትንሽ የለውም ሼር/Share በማድረግ ለብዙዎች ተደራሽ እንሁን።


https://t.me/lawsocieties

Share
3.1K viewsLawyer Mike የህግ ባለሙያ, edited  06:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 20:37:33
በ2014ዓ.ም Exit Exam (የህግ መውጫ ፈተና) ላይ ምን ይላሉ?
Anonymous Poll
19%
ደስተኛ ነኝ
23%
ቅሬታ አለኝ
10%
ምንም አይልም
8%
እንደተለመደው ነው
10%
በጣም ከባድ ነበር
35%
አስተራረሙ ችግር አለበት
15%
ምንም ማለት አልፈልግም
362 voters3.7K viewsEntrust ETC, 17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 20:25:38 በexit exam ውጤት ቅሬታ ያላችሁ ቅሬታችሁን ለሚመለከተው አካል ለማመለከት የሚረዳችሁ ቅፅ ነው።
2.2K viewsEntrust ETC, 17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 16:40:39
2.7K viewsLawyer Mike የህግ ባለሙያ, 13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ