Get Mystery Box with random crypto!

በዝሙት አንዘምን 🚫

የቴሌግራም ቻናል አርማ latekrebu_zina — በዝሙት አንዘምን 🚫
የቴሌግራም ቻናል አርማ latekrebu_zina — በዝሙት አንዘምን 🚫
የሰርጥ አድራሻ: @latekrebu_zina
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.80K
የሰርጥ መግለጫ

የተለያዩ ባለንበት ተጨባጭ በሆኑ ጉዳዮች ላይ እንመካከር እስካሁን በጣም ደስ የሚሉ አስተማሪ ፁሁፎችን አቅርበናል ቻናሉ ውስጥ ገብተው ሁሉንም ያንብቡ።
ከሃራም ፍቅር መውጣት ለምትፈልጉ
በውስጥ መስመር አማክሩኝ
inbox⇢ @Jezakellah
Join Group⇢ @bezemut_anzemn
كنتم خير أمة أخرجت للناس تأمرون
بالمعروف و تنهون عن المنكر

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-25 08:56:28 ክፍል አምስት

ሁሉም እህት ወንድሞቻችን ሊያነቡት የሚገባ በጣም ወሳኝና አንገብጋቢ ርዕስ! ተከተሉን

የመተጫጨት አደቦቹና ገደቦቹ


ከክፍል አራት የቀጠለ

ሌላው ልክ እንደዚሁ ሊያጫት የመጣ ወንድ ሲመጣ ሙሉ የሆነ ሂጃቧን ልትለብስ ይገባታል በጣም በሚፈትን አይነት ሁኔታ ላይ ሁና ልትታየው አይገባም። ያ ማለት ራሷን ትጣል ማለት አይደልም.. ምክንያቱም በዛ ሰአት ያላትን ነገር ነውንጂ ሊታይ የሚገባው የሌላትን ነገር በመቀባባት ሌሎችንም ጠባብና ሚፈትኑ አይነት ነገሮችን በመጠቀም መሆን የለበትም።!
  ከላይ እንዳልነው እጇን ማየት ከፈለገ ብትለብስ እንኳ እጇን ልታሳየው ትችላለች እግሯንም ከሆነ ታሳየው እጇንና እግሯን ለማሳየት ብቻ በጣም የተገላለጠ ልብስ መልበስ የለባትም ፀጉሯንም ከፈለገ ታሳየዋለች።
እጇን ወይም እግሯን ወይም ፀጉሯን አይቶ ይበቃኛል ካለም ይችላል ሲጀመር ፊቷን ካየ በቂ ነው ፊቷን አይቶ ሌላውንም ነገር መገመት ይችላል እጇንም ካየ የሰውነት አካሏን በእጇ መስሎ መረዳት ይችላል።  እናም ሂጃቧን ልትጠብቅ ይገባታል። ውድ እህቴ ጥንቃቄ አድርጊ የሌለሽን ነገር አሳይተሽ ነገ ያን ነገር ሲያጣው ጥሎሽ ሊሄድ ይችላል እናም ትክክለኛውን ያለሽን ነገር አሳይው።
ውድ ወንድሜም በተቀባባና በተገላለጠ ነገር ውሳኔ እንዳትወስን ጥንቃቄ አድርግ ተቀባብታ እንኳ ብታገኛት አሳጥበህ ነው ማየት ያለብህ።

ብዙ ጊዜ የሚፈጠር ነር አለ ልጅቱ ተቀባብታ ጨረቃ መስላ ትጠብቀውና ያያታል እሱም ያን አይቶ በችኳላ ኒካህ ያስራል ከዛም ያ ነገር ሲለቅ ይደነግጣል ኧረ እኔ ያየኋት እሷን አይደለም ሸውዳኛለች አታላኛለች እስከማለት ይደርሳል እናም ለትዳር የምታየትን ልጅ በተፈጥሮዋ ሁኔታ ላይ ሁና ልታያት ይገባል ተቀባብታም ከሆነ ፊቷን በውሃ አሳጥበህ ማለት ይኖርብሃል።

ተቀባብታ ጨረቃ መስላ አይተሃት ትዳር ውስጥ ከገባህ ላንተም ለሷም ጥሩ አይደለም በተለይ ለሷ ይጎዳታል ሸውዳኛለች አታላኛለች አይ አልፈልጋትም ብሎ በዚህም ምክንያት ትዳሩ ሊፈርስ ይችላል።
  እናም ሴቶችም ጥንቃቄ አድርጉ መዋዋብ ከትዳር በኋላ ለባልሽ ብቻ ትዋቢለታለሽ።

ሌላው ደግሞ ከተያዩ በኋላ ፎቶ መላላክ አለ ይሄም አይቻልም! ኡለማዎች ከልክለዋል መጀመሪያ ተያይተዋል ከዛ በኋላ አንዴ ተያይተናልና ተብሎ እሷም ለሱ እሱም ለሷ ፎቶ ሊላላኩ በጭራሽ አይቻልም። አላህን እንፍራ በሚዲያም የለቀቅነው ካለ ማጥፋት ይኖርብናል።

ሌላው ሚነሳው ጥያቄ በሚዲያ ወይም በፎቶ መተያየት ይችላሉ የሚል ነው በዚህ ጉዳይ ኡለማዎች የተለያየ አስተያየት ሰጠውበታል እሷን ለማየት የተለያየ ቦታ ላይ ከሆኑ ፎቶዋን አይቶ ሚወስን ከሆነ ችግር የለውም ብለዋል።(ሸህ ፈውዛን)
ሌሎች ኡለማዎች ደግሞ ይሄን የከለከሉበትም አሉ የተለያየ ሃገር ቢሆንም እዛው ሲሄድ ይያት የሚል አቋም ያላቸውም አሉ።

! ግን ይሄ በጣም ጥንቃቄ የሚገባው ነገር ነው ለምሳሌ በፎቶ ያያታል እሱም ልኮላት ታየዋለች ከዛ በኋላ እሷ ስታየው ላይመቻት ይችላል ከዛ አልፈልግም ስትለው የሷን ፎቶ ይዞ መጥፎ ነገር በማድረግ ያስፈራራታል በተለይ ኒቃብ የምትለብሱ እህቶች ጥንቃቄ አድርጉ።
  በፎቶ ይተያዩ ይቻላል ያሉት ኡለማዎች ልጁ በጣም ታማኝ ከሆነ ፎቶ የማይዝ ከሆነ ለሌሎችም የማያሳይ ከሆነ ነው። ብለዋል።
  ዛሬ ላይ በጣም ብሱ ሴቶች እያለቀሱበት አደጋ ላይ እየወደቁበት ያለው ጉዳይ ይሄ ነገር ነው። እና በጣም ጥንቃቄ ያስፈልገዋል። ፎቶዋን እበትነዋለሁ እያለ በፎቶ እያስፈራራ የማትፈልገው ህይወት ውስጥ እንድትገባ ልትሰራውም የማትፈልገውን ነገር እንድትሰራ ያደርጋል ብዙ አላህን የማይፈሩ አሉ ይሄን ፎቶ ለብዙ አላማ የሚጠቀሙ ወንዶች አሉ።
   እና ይሄን ፎቶ ስትልኪለት እንደሚያጠፋው ምን ያክል ዋስትና አለሽ!?
  ሸህ ፈውዛን ማየት ይፈቀድለታል ለጋብቻ ከሆነ ካሉ በኋላ ፎቶ ሃራም ነው ለጋብቻ ስለተፈቀደ ሃላል ነው ማለት አይደለም ብለዋል ያው በችግር ስለሆነ ፎቶው ከበቃው ይይ ግን በጣም ጥንቃቄ ያስፈልገዋል።!

ይሄ ፎቶ ነገ ምን እንደሚያመጣብሽ አታውቂም በጣም ብዙ ዋጋ ሊያስከፍልሽ ይችላል!
ውድ እህቴ ጥንቃቄ አድርጊ! በሚዲያ የለቀቅሻቸውም ካሉ አጥፊያቸው። ቁጥብነት ለራስ ነው ሚጠቅመው!

ባረከላሁ ፊኩም
(አላህ የላቀና ይበልጥ አዋቂ ነው)

ክፍል አምስት ይቀጥላል

ለአላህ ብለን በውስጥ መስመር በግሩፖችንም ቻናል ያለንም በቻናላችን ሼር እናድርገው።
በተለይ በውስጥ መስመር በምንችለው ሼር እናድርገው።

የሁላችንም ሃላፊት ነው ሃላፊነት የሚሰማን ሰው እንሁን! ለዲናችን ይችን ትንሽ ነገር እናድርግ!


በዚህ ህይወት ተጨማሪ ምክር ካስፈለጋችሁ እንዲሁም ጥያቄ ካላችሁና በሃራም ምንገድ ላይ ሆናችሁ ለመውጣት እገዛ ካስፈለጋችሁ በውስጥ መስመር አማክሩኝ ሚስጥራችሁ ሁሌም የተጠበቀ ነው።

@jezakellah @jezakellah

ለአላህ ብለን!
ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር
ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር


ያለፉትንና የቀሩትን አስተማሪ መልዕክቶች ቻናላችንን ተቀላቅላችሁ ተከታተሉን። አልሃምዱሊላህ የብዙዎች የመመለስ ሰበብ ሆኗል።
በዝሙት አንዘምን ๓ የቴሌግራም ቻናል
Join us on tg channel


https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina
1.9K viewsMuhi, edited  05:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 08:54:41 ክፍል አምስት
በጣም ይቅርታ ኔት አልሰራልኝ ብሎ ነው ማታ ያለቀኩላችሁ

https://t.me/latekrebu_zina
871 viewsMuhi, edited  05:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 19:30:51 ኢንሻ አላህ ከ³ሰዓት በኋላ ክፍል አምስት ይቀጥላል


ቻናሉን ተቀላቅላችሁ ተከታተሉን

https://t.me/+TFVBJ_TiBpFmNGI0
https://t.me/+TFVBJ_TiBpFmNGI0
https://t.me/+TFVBJ_TiBpFmNGI0
1.1K viewsMuhi, 16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 20:33:05 ክፍል አምስት
የመተጫጨት አደቦቹና ገደቦቹ

በቀጣዩ ክፍል
ያጫትን ሴት በምን አይነት ሁኔታ ላይ ይያት በሚል እርዕስ በግልፅ እንመካከራለን በተለይ ይሄን ነገር በጣም ብዙዎች ተሸውደውበታል!

አንዴ ከተያዩ በኋላ ፎቶ መላላክ ይቻላል? በዚህም..

እናም ደግሞ መጀመሪያውም በአካል ካልተያዩ ዝምብለው ለማያውቁት ሰው ላግባሽ ስላለ ብቻ ፎቶ ለምንልክ ሰዎች በጣም አስተማሪና ተጨባጭ የሆነ ማስታወሻ አለው በተለይ በዚህ ርዕስ ብዙ እህቶች ኒቃቢስቶች ሳይቀሩ የተሸወዱበት መንገድ ነው። በላኩት ፎቶ ምክንያትም ወደ ማይፈልጉት ህይወት የገቡ አሉ ሚስጥራቸው እንዳይወጣባቸው በመፍራት።

ኢንሻ በአላህ በቀጣዩ ክፍል ይጠብቁን

ክፍል አራት አንድ ሺ እይታ ስላላገኘ ነገ ልለቅላችሁ ተገድጃለሁ ከአምስት ሺ በላይ ተከታይ ኖሮን ቢያስንስ አንድ ሺ ሰዎች ሊያዩት ይገባል ቀጣዩን ለመልቀቅ።

እናም ኢንሻ አላህ ነገ እለቅላችኋለሁ።

በዱዓችሁ አትርሱኝ

ለማንኛውም አስተያየትና ጥያቄ
@jezakellah


ግሩፑ ላይ ያላችሁ ቻናል ላይ ያልተቀላቀላችሁ ብዙዎች አላችሁ ቻናሉን ተቀላቅላችሁ ያለፉትንና የቀሩትን መልዕክቶቻችንን ያምብቡ
Join us on telegram
Channel

https://t.me/+TFVBJ_TiBpFmNGI0
https://t.me/+TFVBJ_TiBpFmNGI0
https://t.me/+TFVBJ_TiBpFmNGI0
https://t.me/+TFVBJ_TiBpFmNGI0
1.3K viewsMuhi, 17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 09:43:08
ክፍል አምስት


የመተጫጨት አደቦቹና ገደቦቹ
ኢንሻ አላህ ክፍል አራትን ማታ እለቅላችኋለሁ።

በዚህ እርዕስ ከሸሪዓዊ አደብና ገደቦቹ ውጭ በጣም ጠቃሚ ምክሮች ተካተውበታል በትኩረት ተከታተሉን


ሼር ማድረግ አንርሳ ፎቶውንም ፕሮፋይል በማድረግ ሌሎችን እናስታውስ

ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር

ይህ ተጨባጭ የሆኑ ጉዳዮችን እያነሳ የሚያስታውሳችሁ የቴሌግራም ቻናል ነው አልሃምዱሊላህ ብዙዎች ተምረውበታል አላህ ፅናቱን ይስጠን!
እርሶም በመቀላቀል ከዚህ በረካ ራሰዎን ተጠቃሚ አድርጉ

ለማንኛውም ጥያቄና ማማከር ለምትፈልጉ
የውስጥ መስመር
@jezakellah

ለወዳጀዎ ሼር የሚያደርጉለት ምርጥ ስጦታ!
በዝሙት አንዘምን የቴሌግራም ቻናል

ያለፉትንም የቀሩትንም
ቻናላችንን ተቀላቅለው ይከታተሉን!

እንመካከር በመመካከር ህይወት ቀለል ትላለች!
አሁኑኑ ይቀላቀሉን

join Share
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina
1.3K viewsMuhi, edited  06:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 16:49:01 ክፍል አራት

ሁሉም እህት ወንድሞቻችን ሊያነቡት የሚገባ በጣም ወሳኝና አንገብጋቢ ርዕስ! ተከተሉን

የመተጫጨት አደቦቹና ገደቦቹ


ከክፍል ሶስት የቀጠለ

ስለዚህ በስልክ መደዋወል ከሆነ ለሃጃ መሆን አለበት ማለት ስለኒካሁ ጉዳይ፣ ወደፊት ስለሚሆነው ነገር በጣም አስፈላጊ ማውራት ያለባቸው ነገር ከሆነ ተደዋውለው በሃጃቸው ልክ አውርተው ይጨርሳሉ ከዛ ውጭ ድምፅ መለሳለስ፣መሳሳቅ፣ መቀላለድ፣ ምንድን ነው ምትወጂው/ምትወደው፣ ስላለፈው ህይወታችሁ ማውራት፣ ናፍቅሽኝ ናፈከኝና ሌሎችንም ትርፍ ወሬ ማውራት አይቻልም! በሸሪዓው የከለከለው ነው። መቀራረብ መዋደድ መፋቀር ከኒካህ በኋላ ነው ከዛ በፊት ፍቅር የለም የሸይጦን ወጥመድ ቢሆን እንጂ።! ፍቅርም ከተባለ የሃራም ፍቅር ነው ሚሆነው። የሃራም ፍቅር ደግሞ ገደል ውስጥ ነው የሚከተን። ከሸይጧን መረብ ውስጥ ነው የሚከቱን፣ ወደ ጀሃነም እሳት የሚያቃርብ እንጂ ወደ ትዳር መቃረቢያ አይደለም።!
በተለይ ትዳር በሱና መጀመር አለበት ገና ሲጀመር በሃራም መሆን የለበትም በሱና የሚጀመር ከሆነ ትዳሩ በረካ ይኖረዋል።
 ኒካህ እስካላሰረልሽ ድረስ የፈለገ ብትወጂውና ቢፈልግሽ አጅ ነቢይሽ ነው። አደራችንን ጥንቃቄ እናድርግ ካለፉት እህት ወንድሞቻችን ትምህርት እንውሰድ ይሄ መንገድ በጣም መጥፎና የብዙ እህቶቻችን ህይወት ምስቅልቅሉን አውጦታል! አላህ ይጠብቀን። ቁጥብነት ለራስ ነው። አይ አልሰማም የምን ከሆነ ወላሂ አላህ አያያዙ ብርቱ ነው በተለያዩ መንገዶች ይፈትነናል ተጋብተንም ሰላም ያለው ህይወት አይኖረንም ምክንያቱም መሰረታችን በሃራም የተጨማለቀ ስለሆነ ታዲያ እንደዚህ ከሆነ ለምን እንቀርበዋለን ይሄን መንገድ። አስቡት እስኪ ሃላል የሆነ ትዳር ይዛችሁ መዋደድ መተዛዘን የሌለበት ጭቅጭቅና ንትርክ የበዛበት ህይወት ትፈልጋላችሁ ይሄን ማንም አይፈልግም ስለዚህ በዚህ መንገድ ያልገባን ሰዎች ከዚህ በኋላም እንዳንገባ ጥንቃቄ እናድርግ በዚህ ህይወትም ውስጥ ያለን ሰዎች በአስቸኳይ ወደ ሃላል እንቀይረው ካልሆነ እስካሁን ላሳለፍነው ወንጀል ትክክለኛ ተውበት አድርገን ወደ አላህ እንመለስ ከምንገዱ እንራቅ።
በሃራም ነገር ላይም እያለን አላህን መገናኘት እንፍራ!

እናም በመልካም ንግግር ሃያዕ በተሞላበት ጥንቃቄ በተሞላበት ከፊትና የራቀ ንግግር ካልሆነ በስተቀር የሴት ልጅ ድምፇ ይፈትናል ምክንያቱም አላህ(ሱብሃነ ወተዓላ)"መልካም የሆነን ንግግር ተናገሩ ነገር ግን ለወንድ ልጅ ድምፃችሁን አታለስልሱ" ብሏልና
አዎ የሴት ልጅ ድምፅ በጣም ከባድ ነው ወንድ ልጅን በጣም ይፈትናል በተለይ ማለስለስ ማለዘብ የተለያዩ ቃላቶችን እየከሸነች የምትናገረው ከሆነ ይሄ ለወንድ ልጅ በጣም ፊትና ነው። ይሄን ነገር ሴቶች ልታውቁ ይገባል። ከዚህ ወንጀልም ልትርቁ ይገባል። ስለዚህ ባጭሩ ከትዳር በፊት እነዚህ መንገዶችን ልናደርጋቸው አይገባም ማለት ነው። ለዚህም ነው በሃጅ ላይ ያለች ሴት "ለበይክ አላሁመ ለበይክ" የሚለውን ቀስ ብላ ለራሷ በሚሰማት መልኩ እንድትል የተደረገችው። እንደ ወንዱ አትጮህም። ልክ አንደዚሁን አንድ ወንድ ልጅ በሶላቱ ውስጥ ቢሳሳት ወንድ ልጅ "ሱብሃናላህ" ብሎ ማስታወስ ተፈቅዶለታል ሴት ልጅ ግን አልተፈቀደላትም በእጇ ትንሽ እንድታጨበጭብ ነው የተፈቀደላት። ይሄ ሁሉ የተደረገበት ምክንያት የሴት ልጅ ድምፅ ስለሚፈትን ነው አዛን እንዳትልም ጩሃ ቁርዓንም እንዳትቀራ አልተፈቀደላትም። ስለዚህ ሴት ልጅ ወንድ ጋር ለሃጃ ስታወራ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ማለት ነው።

  ግን ከዚህ ሁሉ በላጩ በወልዮቿ ቢያልቅ ነው በአባቷ ወይም በውንድሟ በቤተሰቦቿ በኩል ቢያልቅ የተሻለ ነው ማለት ከተጫጩ ካያት ካየችው በኋላ እሱ ወደሷ ባይሄድ(ባይደውል)በቃ ሚፈልገውን ነገር ሁሉ ቤተሰቦቿን መጠየቅ ቢችል በጣም የተሻ ነው። ይሄ መሆኑ የተመረጠበት የተለያዩ  ወደሸይጦን ከሚወስዱ መንገድ ወደ ዚና ከመሄድ ለመጠንቀቅና ለመራቅ ነው።  ከዛ ኒካህ ካሰሩ በኋላ እንደፈለጉ መሆን ተፈቅዶላቸዋል። 

ባረከላሁ ፊኩም
(አላህ የላቀና ይበልጥ አዋቂ ነው)


ክፍል አምስት ይቀጥላል

ለአላህ ብለን በውስጥ መስመር በግሩፖችንም ቻናል ያለንም በቻናላችን ሼር እናድርገው።
በተለይ በውስጥ መስመር በምንችለው ሼር እናድርገው።


የሁላችንም ሃላፊት ነው ሃላፊነት የሚሰማን ሰው እንሁን! ለዲናችን ይችን ትንሽ ነገር እናድርግ!


በዚህ ህይወት ተጨማሪ ምክር ካስፈለጋችሁ እንዲሁም ጥያቄ ካላችሁና በሃራም ምንገድ ላይ ሆናችሁ ለመውጣት እገዛ ካስፈለጋችሁ በውስጥ መስመር አማክሩኝ ሚስጥራችሁ ሁሌም የተጠበቀ ነው።
@jezakellah @jezakellah

ለአላህ ብለን!
ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር
ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር


ያለፉትንና የቀሩትን አስተማሪ መልዕክቶች ቻናላችንን ተቀላቅላችሁ ተከታተሉን። አልሃምዱሊላህ የብዙዎች የመመለስ ሰበብ ሆኗል።
በዝሙት አንዘምን ๓ የቴሌግራም ቻናል
Join us on tg channel


https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina
2.9K viewsMuhi, edited  13:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 16:46:48 ክፍል አራት
1.1K viewsMuhi, 13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 19:51:45
ክፍል አራት


የመተጫጨት አደቦቹና ገደቦቹ
ኢንሻ አላህ ክፍል አራትን ነገ እለቅላችኋለሁ።

በዚህ እርዕስ ከሸሪዓዊ አደብና ገደቦቹ ውጭ በጣም ጠቃሚ ምክሮች ተካተውበታል


ሼር ማድረግ አንርሳ ፎቶውንም ፕሮፋይል በማድረግ ሌሎችን እናስታውስ

ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር

ይህ ተጨባጭ የሆኑ ጉዳዮችን እያነሳ የሚያስታውሳችሁ የቴሌግራም ቻናል ነው አልሃምዱሊላህ ብዙዎች ተምረውበታል አላህ ፅናቱን ይስጠን!
እርሶም በመቀላቀል ከዚህ በረካ ራሰዎን ተጠቃሚ አድርጉ
comment
@jezakellah

ለወዳጀዎ ሼር የሚያደርጉለት ምርጥ ስጦታ!
በዝሙት አንዘምን የቴሌግራም ቻናል

ቻናላችንን ተቀላቅለው ይከታተሉን!
እንመካከር በመመካከር ህይወት ቀለል ትላለች!

አሁኑኑ ይቀላቀሉን

join Share
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina
1.3K viewsMuhi, 16:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 21:16:13 ክፍል ሶስት

ሁሉም እህት ወንድሞቻችን ሊያነቡት የሚገባ በጣም ወሳኝና አንገብጋቢ ርዕስ! ተከተሉን

የመተጫጨት አደቦቹና ገደቦቹ


ከክፍል ሁለት የቀጠለ

እናም ለብቻ መገናኘት አይቻልም አባት መኖር አለበት ወይም እናት ወይም ወንድም መኖር አለበት ወይ አጎት ወይም አክስት ባጭሩ ሁለታቸው ለመገለለ የሆነ የልጅቷ ቤተሰቦች መኖር አለባቸው።
ከዛ ውጭ ግን ፈተናው ከባድ ነው አላህ(ሱብሃነ ወተዓላም)"ላ ተቅረቡ" (አትቅረቡ) ብሎ ልክ ከፍተኛ ቮልቴጅ እንዳለው የኤሌክትሪክ ሃይል አስጠንቅቆናል ሃሳባችን ትዳር ስለሆነ ብቻ እንደዚህ ልቅ የሆነ ግኑኝነት ልናደርግ አይገባም። አላህን እንፍራ በሃራም ያነካካነው ነገር መጨረሻው አያምርም ብንጋባም እንኳ።

"ሁለታቸው ለብቻ ከተቀመጡ ሸትጧን ሶስተኛው ነው"  ስለዚህ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ትዳር ማለት ከአላህ ፀጋዎች ትልቁ ፀጋ ነው ስለዚህ በትዳር ስም አላህን ልናምፅበት አይገባም። አላህ(ሱብሃነ ወተዓላ) ባስቀመጠበት አደብ ብቻ ነው ሊሆን የሚገባው።

አጀማመሩም በሱና ሊሆን ይገባል በሱና የተጀመረ እስከመጨረሻው ያምራልና ስለዚህ ጥንቃቄ እናድርግ። ብዙዎቻችን እዚህ ላይ እየተሸወድን ነው ምክንያቱም ትዳሩ ሊሆንም ላይሆንም ወንጀል ይዘን መሄድ የለብንም ስለዚህ ለብቻ መገለል ሚባል ነገር ሊኖር አየገባም።
ሃራም ነገር ላይ ሁነን በራስ መተማመን አይሰማን ወላሂ አላህ አያያዙ ብርቱ ነው በዚህ መንገድ አላህን ያውቁታል (ቀርተዋል)የተባሉ ልጆች ራሱ ተፈትነውበት ወድቀዋል። አላህ ይጠብቀን!
ስሜታችን ስላለን ሳይሆን አላህ ባዘዘን መንገድ እንሂድ!
የሁሉም ነገር ቁልፉ በአላህ እጅ ነውና አጋብቶን እንኳ ሰላም የሌለው ትዳር አድርጎ ይፈትነናል። ስለዚህ ቆም ብለን እናስብ በገዛ እጃችን ዱንያችንንም አኼራችንንም አናበላሸው።

ሌላኛው  የመተጫጨት አደብ በሚገናኙበት ግዜ መጨባበጥ፣መተቃቀፍ፣ መሳሳም፣ በጭራሽ በጥብቅ የተከለከለ ነው የወንጀሉ ቅጣትም በጣም ከባድ ነው እባካችሁ ጥንቃቄ እናድርግ ምክንያቱም አጅ ነቢ ስለምንሆን ነው ኒካሁ እስካልታሰረ ድረስ አጅ ነቢ ነው ምንሆነው። ብዙ ግዜ ሃገራችን ላይ አይታችሁ ከሆነ እከሌ እሷን አጭቷታል ከተባለ ተጋብተዋል የተባለ ነው ሚመስለው ግን ማጨትና ኒካህ ማሰር በጣም የተለያዩ ነገር ናቸው። ምን አልባት ቢያወራት ችግር የለውም ያው በጋብቻው የተያያዘ ወሬ አንዳንድ በጣም ወሳኝ ወሬ ብቻ ሌላ ፊትና ሚቀሰቅስ ነገር ሳያወራ ያም በጣም በትንሹ ነው።
ስለዚህ በነዚህ ነገራቶች ላይ በጣም ጥንቃቄ እናድርግ በተለይ ሸይጧን በነዚህ ነገራቶች በጣም ይበረታል። ጨዋ የሆኑ ሴትና ወንዶችን አንዴ ይሄ ነገር ከተጀመረ ነገራቶች ሁሉ የተበላሹበት ሁኔታዎች ናቸው ያሉት ነገራቶችም እየዞሩ ነው ወደ ሃራም። ስለዚህ ከተያየን በኋላ ወንጀል ሳይገባ ቶሎ ወደ ኒካህ መግባት ነው ያለብን።
ካልሆነ ምን አልባት ነገራቶች ላይመቹ ይችላሉ የተራራቀ ቦታ ካሉና ቶሎ ለመጋባትም ነገሮች ካልተመቹ ግዜው እስከሚደርስ መራራቅ አለብን። በምንም አይነት መንገድ ግኑኘወነት ሊኖረን አይገባም!

በስልክም ቢሆን ስለ ትዳሩ ካልሆነ ብቻ ሌላ ወሬ ሊያወሩ አይፈቀድላቸውም። እሷም በሚያወራት ግዜ ድምፁዋን በማታለሳልስ ልትፈትነው አይገባም።

ካጨናት ሴት ጋር በስልክ መደዋወል ማለት ለመጋባት ተስማሙ እንጂ ኒካህ አሰሩ ማለት አይደለም። ኒካህ ሚባለው ንካህ ሲታሰር ነው ከዚህ ጋ ብዙ ሰዎች ይሸወዳሉ አጫት ማለት አገባት ማለት አይደለም! በጣም የሚገርመው አንዳንድ እህትና ወንድሞት ለመጋባት በመስማማታቸው ብቻ ሁኔታቸውን ስናይ የተጋቡ ነው ሚመስለው ባልና ሚስት እራሱ እንደዛ ግኑኝነት አይፈጥርም ይሄ የሸይጦን መንገድ ነው የሚገርመው እንዲህ ተቀራርበው የተጋቡ ሴቶች ከተጋቡ በኋላ ጀርባ ሲሰጣጡ ይታያል ምክንያቱም በሃራም ምንገድ ስለሆነ የመጡት አላህ ውዴታቸውን ያወጣባቸዋል አላህ ይጠብቀን ይሄ ትልው አደጋ ነው ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባናል። ተጫጫችሁ ማለት ታጋባችሁ ማለት አይደለም ነገ ሳትጋቡ ሊቀር ይችላል።
በጣም ብዙ ሃራም ነገር ይሰራል ካጫት በኋላ በየሰዓቱ ይደውላል የት ዋልሽ፣ የት ገባሽ፣ ምሳ በላሽ ፣ራት በላሽ፣ ተኛሽ፣ ተነሳሽ፣ ሰገድሽ፣ ቀራሽ እያለ በየሰዓቱ ይደውላል ይሄ ትክክል አይደለም አንዳንዶችም እየያዙ ይወጣሉ በቃ ቤተሰቦቿ እንኳ ወስዶ ቤቱ ቢያሳድራት ምንም አይመስላቸውም እንደፈለገ ይሆናል ሱብሃናላህ!! ይሄ ሃራም ነው ወላሂ አላህን እንፍራ።!!

ባረከላሁ ፊኩም
(አላህ የላቀና ይበልጥ አዋቂ ነው)


ክፍል አራት ይቀጥላል

ለአላህ ብለን በውስጥ መስመር በግሩፖችንም ቻናል ያለንም በቻናላችን ሼር እናድርገው
በተለይ በውስጥ መስመር በምንችለው ሼር እናድርገው።

የሁላችንም ሃላፊት ነው ሃላፊነት የሚሰማን ሰው እንሁን!

በዚህ ህይወት ተጨማሪ ምክር ካስፈለጋችሁ እንዲሁም ጥያቄ ካላችሁና በሃራም ምንገድ ላይ ሆናችሁ ለመውጣት እገዛ ካስፈለጋችሁ በውስጥ መስመር አማክሩኝ ሚስጥራችሁ ሁሌም የተጠበቀ ነው
@jezakellah @jezakellah

ለአላህ ብለን!
ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር
ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር


ያለፉትንና የቀሩትን አስተማሪ መልዕክቶች ቻናላችንን ተቀላቅላችሁ ተከታተሉን አልሃምዱሊላህ የብዙዎች የመመለስ ሰበብ ሆኗል።
በዝሙት አንዘምን ๓ የቴሌግራም ቻናል

Join us on tg channel

https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina
2.5K viewsMuhi, edited  18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ