Get Mystery Box with random crypto!

ክፍል አምስት ሁሉም እህት ወንድሞቻችን ሊያነቡት የሚገባ በጣም ወሳኝና አንገብጋቢ ርዕስ! ተ | በዝሙት አንዘምን 🚫

ክፍል አምስት

ሁሉም እህት ወንድሞቻችን ሊያነቡት የሚገባ በጣም ወሳኝና አንገብጋቢ ርዕስ! ተከተሉን

የመተጫጨት አደቦቹና ገደቦቹ


ከክፍል አራት የቀጠለ

ሌላው ልክ እንደዚሁ ሊያጫት የመጣ ወንድ ሲመጣ ሙሉ የሆነ ሂጃቧን ልትለብስ ይገባታል በጣም በሚፈትን አይነት ሁኔታ ላይ ሁና ልትታየው አይገባም። ያ ማለት ራሷን ትጣል ማለት አይደልም.. ምክንያቱም በዛ ሰአት ያላትን ነገር ነውንጂ ሊታይ የሚገባው የሌላትን ነገር በመቀባባት ሌሎችንም ጠባብና ሚፈትኑ አይነት ነገሮችን በመጠቀም መሆን የለበትም።!
  ከላይ እንዳልነው እጇን ማየት ከፈለገ ብትለብስ እንኳ እጇን ልታሳየው ትችላለች እግሯንም ከሆነ ታሳየው እጇንና እግሯን ለማሳየት ብቻ በጣም የተገላለጠ ልብስ መልበስ የለባትም ፀጉሯንም ከፈለገ ታሳየዋለች።
እጇን ወይም እግሯን ወይም ፀጉሯን አይቶ ይበቃኛል ካለም ይችላል ሲጀመር ፊቷን ካየ በቂ ነው ፊቷን አይቶ ሌላውንም ነገር መገመት ይችላል እጇንም ካየ የሰውነት አካሏን በእጇ መስሎ መረዳት ይችላል።  እናም ሂጃቧን ልትጠብቅ ይገባታል። ውድ እህቴ ጥንቃቄ አድርጊ የሌለሽን ነገር አሳይተሽ ነገ ያን ነገር ሲያጣው ጥሎሽ ሊሄድ ይችላል እናም ትክክለኛውን ያለሽን ነገር አሳይው።
ውድ ወንድሜም በተቀባባና በተገላለጠ ነገር ውሳኔ እንዳትወስን ጥንቃቄ አድርግ ተቀባብታ እንኳ ብታገኛት አሳጥበህ ነው ማየት ያለብህ።

ብዙ ጊዜ የሚፈጠር ነር አለ ልጅቱ ተቀባብታ ጨረቃ መስላ ትጠብቀውና ያያታል እሱም ያን አይቶ በችኳላ ኒካህ ያስራል ከዛም ያ ነገር ሲለቅ ይደነግጣል ኧረ እኔ ያየኋት እሷን አይደለም ሸውዳኛለች አታላኛለች እስከማለት ይደርሳል እናም ለትዳር የምታየትን ልጅ በተፈጥሮዋ ሁኔታ ላይ ሁና ልታያት ይገባል ተቀባብታም ከሆነ ፊቷን በውሃ አሳጥበህ ማለት ይኖርብሃል።

ተቀባብታ ጨረቃ መስላ አይተሃት ትዳር ውስጥ ከገባህ ላንተም ለሷም ጥሩ አይደለም በተለይ ለሷ ይጎዳታል ሸውዳኛለች አታላኛለች አይ አልፈልጋትም ብሎ በዚህም ምክንያት ትዳሩ ሊፈርስ ይችላል።
  እናም ሴቶችም ጥንቃቄ አድርጉ መዋዋብ ከትዳር በኋላ ለባልሽ ብቻ ትዋቢለታለሽ።

ሌላው ደግሞ ከተያዩ በኋላ ፎቶ መላላክ አለ ይሄም አይቻልም! ኡለማዎች ከልክለዋል መጀመሪያ ተያይተዋል ከዛ በኋላ አንዴ ተያይተናልና ተብሎ እሷም ለሱ እሱም ለሷ ፎቶ ሊላላኩ በጭራሽ አይቻልም። አላህን እንፍራ በሚዲያም የለቀቅነው ካለ ማጥፋት ይኖርብናል።

ሌላው ሚነሳው ጥያቄ በሚዲያ ወይም በፎቶ መተያየት ይችላሉ የሚል ነው በዚህ ጉዳይ ኡለማዎች የተለያየ አስተያየት ሰጠውበታል እሷን ለማየት የተለያየ ቦታ ላይ ከሆኑ ፎቶዋን አይቶ ሚወስን ከሆነ ችግር የለውም ብለዋል።(ሸህ ፈውዛን)
ሌሎች ኡለማዎች ደግሞ ይሄን የከለከሉበትም አሉ የተለያየ ሃገር ቢሆንም እዛው ሲሄድ ይያት የሚል አቋም ያላቸውም አሉ።

! ግን ይሄ በጣም ጥንቃቄ የሚገባው ነገር ነው ለምሳሌ በፎቶ ያያታል እሱም ልኮላት ታየዋለች ከዛ በኋላ እሷ ስታየው ላይመቻት ይችላል ከዛ አልፈልግም ስትለው የሷን ፎቶ ይዞ መጥፎ ነገር በማድረግ ያስፈራራታል በተለይ ኒቃብ የምትለብሱ እህቶች ጥንቃቄ አድርጉ።
  በፎቶ ይተያዩ ይቻላል ያሉት ኡለማዎች ልጁ በጣም ታማኝ ከሆነ ፎቶ የማይዝ ከሆነ ለሌሎችም የማያሳይ ከሆነ ነው። ብለዋል።
  ዛሬ ላይ በጣም ብሱ ሴቶች እያለቀሱበት አደጋ ላይ እየወደቁበት ያለው ጉዳይ ይሄ ነገር ነው። እና በጣም ጥንቃቄ ያስፈልገዋል። ፎቶዋን እበትነዋለሁ እያለ በፎቶ እያስፈራራ የማትፈልገው ህይወት ውስጥ እንድትገባ ልትሰራውም የማትፈልገውን ነገር እንድትሰራ ያደርጋል ብዙ አላህን የማይፈሩ አሉ ይሄን ፎቶ ለብዙ አላማ የሚጠቀሙ ወንዶች አሉ።
   እና ይሄን ፎቶ ስትልኪለት እንደሚያጠፋው ምን ያክል ዋስትና አለሽ!?
  ሸህ ፈውዛን ማየት ይፈቀድለታል ለጋብቻ ከሆነ ካሉ በኋላ ፎቶ ሃራም ነው ለጋብቻ ስለተፈቀደ ሃላል ነው ማለት አይደለም ብለዋል ያው በችግር ስለሆነ ፎቶው ከበቃው ይይ ግን በጣም ጥንቃቄ ያስፈልገዋል።!

ይሄ ፎቶ ነገ ምን እንደሚያመጣብሽ አታውቂም በጣም ብዙ ዋጋ ሊያስከፍልሽ ይችላል!
ውድ እህቴ ጥንቃቄ አድርጊ! በሚዲያ የለቀቅሻቸውም ካሉ አጥፊያቸው። ቁጥብነት ለራስ ነው ሚጠቅመው!

ባረከላሁ ፊኩም
(አላህ የላቀና ይበልጥ አዋቂ ነው)

ክፍል አምስት ይቀጥላል

ለአላህ ብለን በውስጥ መስመር በግሩፖችንም ቻናል ያለንም በቻናላችን ሼር እናድርገው።
በተለይ በውስጥ መስመር በምንችለው ሼር እናድርገው።

የሁላችንም ሃላፊት ነው ሃላፊነት የሚሰማን ሰው እንሁን! ለዲናችን ይችን ትንሽ ነገር እናድርግ!


በዚህ ህይወት ተጨማሪ ምክር ካስፈለጋችሁ እንዲሁም ጥያቄ ካላችሁና በሃራም ምንገድ ላይ ሆናችሁ ለመውጣት እገዛ ካስፈለጋችሁ በውስጥ መስመር አማክሩኝ ሚስጥራችሁ ሁሌም የተጠበቀ ነው።

@jezakellah @jezakellah

ለአላህ ብለን!
ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር
ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር


ያለፉትንና የቀሩትን አስተማሪ መልዕክቶች ቻናላችንን ተቀላቅላችሁ ተከታተሉን። አልሃምዱሊላህ የብዙዎች የመመለስ ሰበብ ሆኗል።
በዝሙት አንዘምን ๓ የቴሌግራም ቻናል
Join us on tg channel


https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina