2022-07-15 09:54:00
" ከሞት ለተረፉ በነፍስ ድረሱ "
በቅርቡ በምዕራብ ወለጋ ቶሌ እና ቄለም ወለጋ በነበረው ጭፍጨፋ ከሞት አምልጠው ግማሽ ቤተሰባቸውን ቀብረው ( ለመቅበርም ያልታደሉ አሉ) ብዙዎቹ እዛው ቶሌ እና መቻራ ድንኳን ውስጥ ሌሎቹ ደግሞ ወደ አማራ ክልል ደብረ ብርሃን ፥ ሀርቡ ፥ አርጎባ ፥ ደሴ ዙሪያ ፥ ደጋን እና ወረባቦ በመሄድ በተገኘው መጠለያ ጣቢያ ሁሉ ሰፍረዋል። ሙሉ ቤተሰባቸውን ያጡ ፥ ከአንድ ወይም ሁለት ልጆቻቸው ጋር ብቻ ያመለጡ ፥ ሙሉ ልጆቻቸውን አጥተው የወላድ መሃን የሆኑና ጧሪ ቀባሪ አልባ የሆኑ አዛውንቶች ፥ ቤተሰብ አልባ የሆኑ የቲም ልጆች (እስካሁን እጃችን ላይ ባለን መረጃ 296 ህጻናት) ሁሉም ቦታ ይገኛሉ፡፡
ከጥቃቱ በኋላ ቦታው ላይ በመጠለያ የሰፈሩም ሆነ ወደ ሸዋና ወሎ የመጡት እስካሁን ይህ ነው የሚባል ድጋፍ ያልተደረገላቸው በመሆኑ ለከፋ ችግር ተጋልጠዋል፡፡
የአግማስ ኢትዮጵያ ቲም ተዘዋውሮ ባየባቸው መጠለያ ጣቢያዎች በሙሉ ሰዎች ለረሃብና በሽታ እየተጋለጡ መሆኑን አረጋግጧል፡፡ የሚላስ የሚቀመስ እንድሁም የሚለበስ ነገር የለም። በመጠለያ እጥረት ሰዎች በዚህ ክረምት ውጭ ላይ ለማደር ተገደዋል፡፡ ምስጥ የወጣባቸው አዛውንትና ህጻናት በሞት አፋፍ ላይ ያሉ ቁስለኞችን አይተናል፡፡ ለዚህም ሲባል ከሞት ያመለጡ ወገኖችን ረሃብ በሽታና ብርድ እንዳይገላቸው በሚል ከወገን ለወገን ድጋፍ ማሰባሰብ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
እነዚህ ወገኖቻችን በአስቸኳይ የምግብ ፥ የአልባሳት ፥ የመጠለያ ፥ የንጽህና መጠበቂያና የቁሳቁስ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፡፡
በመሆኑም ትላንት ለሌላ ይተርፉ የነበሩ አምራች እጆች ዛሬ የእኛን ድጋፍ ለመቀበል ተዘርግተዋልና " ከሞት ለተረፉ በነፍስ ድረሱ" በሚል አግማስ ኢትዮጵያ ጥሪውን ያቀርባል።
ማንኛውም መደገፍ የሚፈልግ ሰብአዊ ፍጡር ወገኖቻችንን ለመደገፍ
1- ከላይ የተጠቀሱት ቦታዎች በአካል በመገኘት
2- ከስር በተጠቀሱት የባንክ አካውንቶችና ፕላት ፎርሞች ገቢ በማድረግ
3- የቲሞችን እየደገፉ በቋሚነት ለማሳደግ ድርጅታችንን በአካልም ይሁን በስልክ በማናገር
4- በአይነት ደምበል ሲቲ ፊት ለፊት በሚገኘው ቢሯችን ይዞ በመምጣት
ድጋፍ ማድረግ ትችላላችሁና የተዘረጉ እጆችን በስጦታ ሞልተን እንመልስ - በጎነት ለራስ ነው-ለበጎ ስራ ረፍዶ አያውቅም እንላለን፡፡
Phone- 0901443322
AgmasEthiopia
Home of Humanity
Agmas Ethiopia Charity Organization
Accounts numbers
Abyssinia = 83644327
CBE = 1000446156784
Hijra = 1000724470001
Abay =5266617688909010
coop = 1022200052371
Oromia = 1479271500001
1.1K views06:54