Get Mystery Box with random crypto!

​​ ብቸኝነቴን ..... መልሺልኝ ክፍል ሰላሳ ስምንት (38) . . . ሚካኤሌ ሆ/ል ቶማስን | ETHIO BOOKS PDF

​​ ብቸኝነቴን ..... መልሺልኝ

ክፍል ሰላሳ ስምንት (38)
.
.
.
ሚካኤሌ ሆ/ል ቶማስን አስቀምጦ እሱ ወደ ቤቱ መጥቷል። እናም መካናውን
አቁሞ ደረጃውን በመውጣት ወደ ቤቱ የዕነ ሰርካለም ቤት ሰላም በማለት
ሊያልፍ ሲል ሚጣ እና ስጦታ ወደ ቤቱ እንዳይገባ እሮጠው ሄደው ያዙትና
" ሚክ አባቴ የሆነ ሽታ አይሸትህም " አለችው ስጦታ ሚካኤሌ በአፍንጫው
አየሩን ዛቅ ዛቅ አርጎ ወደ አፍንጫው ሞጀረው ግን ምንም አዲስ ሽታ
አልሸተተውም ።
" እረ ምንም የለም ልጆቼ " አለ ግራ ተጋብቶ
" አይ ፋዘር በቃ አራድነት ትንሽ ይጎልሀል " አለች ሚስጥረ።
" እረ ምን አራድነት ብልጥነትም ጭምር ሞቅ ያለ ፈራም ነው እንጂ ...... እረ
ፕሊስ አታዋርደን " አለች ሚጣም ሚካኤሌ ግራ ተጋብቶ የሆነ ጨዋታ
ሊጫወቱበት እንደሆነ ገብቶታል ። ያላወቀው ምን እንደሆነ ነው ግራ የገባው ።
" ይሀውልህ እዚህ አንተ ቤት ጥሩ የፍቅር ጠረን እየነፈሰ ነው እዚህ እኛ ጋር ግን
መጥፎ አየር ነው የሚነፍሰው " አለች ሚጣ እንደማዘን ብላ።
" የዚህኛው የእኛ ቤቱ ገብቶኛል ያልገባኝ ይሄኛው ነው ቤት ነው ሁለተኛው ቤቴ "
አለ ማክዳን የላካት አሞታል ብሎ ከኬብሮን ጋር ተመሳጥሮ ነው የዕነ ሰርካለም
ቤት ግን አልገባውም ምን እንደተፈጠረ።
" ይሄኛው እንኳን ሁለተኛው ቤትህ የአንተ መሆኑ ያጠራጥራል ለምን መሰለህ
ሰርኬ ከዚህ በኋላ እንዳይመጣብኝ ላየው አልፈልግም ብላ ከጠዋት ጀምሮ በሩን
ዘግታ ስቅስቅ እያለች እያለቀሰች ብኗኳኳ ብኗኳኳ የሚከፍትልን አጣን እንቢ
አለች " አለች ስጦታ።
" ምን አረኳት ምን በድያት " አለ እየደነገጠ ።
" የበደልካት አንተ ሳትሆን ሀብትህ የድርጅት ባለቤት መሆንህ ነው " አለች
ሚጣ።
" እና እሱ ከእሷ ጋር ምን ግንኙነት አለው " አላቸው ።
" አለው እኔ አባቴ እንድትሆን የተመኘሁት እን እኛ ምስኪን ድሀ መስለሀኝ ነው
ሚኪ እኛ የመነጠቅን የምንበላው እንኳን የሌለን ድሀዎች አንተ የተከበርከት
የትልልቅ ድርጅቶች ካፓኒዎች ባለቤት የእኔ እናት አንተን ብታገባ ተፋቅረው ተጋቡ
ሳይሆን ሴት ልጅ ብር ትወዳለች የሚሉ የአንዳንድ ሰዎች አመለካከትን እኛ ላይ
አገኙት ማለት ነው " አለች ስጦታ።
" እንዴ ምን ማለት ነው ይሄ ሰው ምንም ቢሆን ወሬ አያጣም ስለ ሰው ብለን
የራሳችንን ህይወት እንበጥብጥ መተው ካለብኝ ሀብት ንብረቴን ጥዬ አገባትና
ለእሷ ስል ከሀ እጀምራለሁ እሺ የት ነው ያለችው " አለና ወደ ቤት ተከታትለው
ገቡ።
" አንተ ውጣልኝ .......ውጣልኝ ....." አለች ሰላም በጩሀት ሶፋ ላይ ተቀምጣ
ከፊቷ ካለው ጠረጴዛ ላይ ከተቀመጠው ውስኪ እየቀዳች በደረቁ እንደ ውሀ ወደ
ጉሮሮዋ እያንቆረቆረች ፊቷ እና አይኗ ቀልቶ ደም መስሏል በግንባሯ ላይ
በተለያየ አቅጣጫ ተገታትረዋል አንድ ለእናቱ የሆነው የአ.አ ጎተራው የብሄር
ቤሄረሰብ ቀለበት መንገድ ይመስል ተጠላልፏል። ታረቀኝ የሰላም ሁኔታ
አስፈርቶታል ለዕዛ ሲል ጥሏት ለመሄድ አልፈለገም እሷ ግን ብቻዋን መሆን
እንደምትፈልግና እንዲሄድላት በጩሀት ደጋግማ ተናገረችው
" ....... ምንድን ነው ጀርባዬ ላይ ያለ መዥገር የምትሆንብኝ በጥይት ግንባርህን
ብዬ ልድፋህ ወይስ ከዚህ ቤት ትወጣልኛለህ .... የሆንክ አጋስስ " አለችው ።
ታረቀኝም እንዳመረረች ስለገባው ተነስቶ ወጣ የሄደ መስሎ በሩ ላይ መሬት ላይ
ቁጭ ብሎ ይጠብቃት ያዘ።
ሰላም ውስኪውን ትጨልጣለች ትስቃለች እንደገና ታለቅሳለች ግራ የገባው
ህይወት።
" ቆይ ለእኔ እንደዚህ መሆን ማን ነው ተጠያቂ እኔ እራሴው ነኝ ወይስ ፍቅር
እንዳይገባኝ ያደረጉኝ ለልጄ ፍቅር መስጠት እንዳልችል እና እንድጠላት ያደረጉኝ
እናቴ እንጀራ አባቴ እና የሰው ልጅ ወይስ ከፍቅር ገንዘብ እንደሚበልጥ ለገንዘብ
ስል መግደል እንዳለብኝ ያስረዳኝ አድማሱ ነው ?..... እሱን እኮ ከልቤ አፍቅሬው
ነበር እሱ ግን...." አለችና በሀሳብ ተጓዘች።
ከዓመታት በፊት ወደ ኋላ እንመለስ
በአንድ ሆቴል አድማሱና ሰላም አብረው እራት እየበሉ እሷን የብዙ ወንዶች አይን
አርፎባታል በጣም ተውባ ነበር አድማሱ የሚካኤሌን ሀብት እና ንብረት እንዴት
መቀማት እንደሚችል ያስባል እሷ ደግሞ የአድማሱን ፍቅርና እሱን ብቻ ነው
የምታስበው።
" እና ያልኩሽን አሰብሽበት ከአንተ ውጪ ሌላ ገላ ሌላ ምናምን እንዳትይኝ ብቸኛ
እና ትዳር የሌለው ምስኪን ሰው ነው በቀላሉ ሊታለል የሚችል " አላት
" ሰውዬው ምስኪን ስለሆነ ለምን እንቀማዋለን የራሳቾንን ኑሮ ለምን አንኖርም
ባለን ነገር " አለችው በልመና።
" ምን ፃድቅ ፃድቅ ያረግሻል አንቺ ባትሰሪው ሌላ አሰራለው ስንት ሀብታም
መሆን የሚፈልግ አለ ወስኚ አሁን " አላት ግራ ገባት ለእራሷም በዚህ ምድር
ጥሩ ሰው እንደሌለ አሰበች በቃ እሷም ተመሳስላ መጥፎ መሆን ከብዙ ክርክር
በኋላ ተስማማች።
ከሀሳብ ስንመለስ
" ..... እስቲ ወገተኛ ካልሆናቹሁ መልሱልኝ ለእኔ እንዲህ መሆን ማን ነው
ጥፋተኛ ?" አለች
ስጦታ እና ሚጣ በሳሎን ውስጥ ቁጭ ብለው በጩሀት ለመግባባት የከበዳቸው
የሚመስሉትን የሚካኤሌን እና የሰርካለምን ክርክር የሰማሉ ድምፅ አነስ
ሲልባቸው ሄደው በር ስር ተለጥፈው ይሰማሉ በመጨረሻ ከብዙ ጭቅጭቅ
በኋላ ተስማሙ ዕነ ሚጣም በእፎይታ ተነፈሱ ሲሳሳሙ ሰሙና በደስታ
ተጨባብጠው ተሳሳሙ። እቺን ዕቅድ አቅደው ሚጣ እናቷ ሀብታም ወንድ
አለመውደዷን ስጦታ ሚኪ ለአመነበት ነገር ግትር እንደሆነ ተናገረች በዚህ
ጉዳይ አውርተው ሁለቱን ለማገናኘት አቀዱ እቅዳቸውም ተሳካ።
ሚኪና ሰርኬ ከመኝታ ክፍሉ ተቃቅፈው በደስታ ፈገግ ብለው ወደ ሳሎን ሲመጡ
ሁለቱም ህፃናት ቆመው እጃቸውን ዘርግተው ጠበቋቸው አያቸውና ግራ ሲጋቡ።
" እናንተን ዕነ ኬቡን ለማጣበስ ያየነው መከራ ስቃይ ኡሁሁ ገገማ ፋራዎች ናቹሁ
ዕቅድ ስናወጣ ስታፈርሱ አደከማቹሁን አሁን አጣብሰን ስራችን አልቋል ሂሳብ
ይከፈለን "አለች ሚጣ
" የቀረ በዝምድና አንሰራም ሌላው የልጆችiን መብት ወደ ኋላ ጥላቹሁ መኝታ
ክፍል ከመሳሳም ባለፈ በልጅ አፍ የማይነገር ነገር ሳታፍሩን በማረጋቹሁ ሳንከስ
ሂሳብ ካሳ ይሰጠን " አለች ስጦታ ኮስተር ብላ ዕነ ሚኪ እየተያዩ ሳቁ።......
ይቀጥላል

@Kooblife
@Kooblife

For any comment
@Ethio96bot