Get Mystery Box with random crypto!

ብቸኝነቴን ..... መልሺልኝ ክፍል ሰላሳ ሰባት (37) . ሚካኤሌ መኪናው ከሆስፒታል ግቢ ው | ETHIO BOOKS PDF

ብቸኝነቴን ..... መልሺልኝ

ክፍል ሰላሳ ሰባት (37)
.
ሚካኤሌ መኪናው ከሆስፒታል ግቢ ውስጥ አቁሞ ወደ መኝታ ክፍሉ መግቢያ
በር ላይ አቁሞ ወደ ሆ/ሉ መኝታ ክፍል ገባ አንገቱን ደፍቷል ያኮረፈ ይመስላል
በቀጥታ በኮሪደሩ በመሄድ በሩን እንኳኩቶ ገባ ማክዳ ብቻዋን ተቀምጣለች ቃል
ኪዳን ኦክስጅኑ ተነቅሎላት በእራሷ አቅም በመተንፈስ ላይ ነች ። እንዴት
እንደሆነች ጠየቃት ጥሩ ለውጥ እንዳመጣችና ደህና መሆኗን ነገረችው እሱም
ቁጭ አለ ትክዝ ብሏል ማክዳ ደጋግማ ዘወር ብላ ተመለከተቺው
" ምን ሆነሀል ሚኪ ጥሩ አይደለህም " አለችው ዘወር ብሎ ተመለከታት ለደቂቃ
ፍዝዝ ብሎ።
" አንቺና ኬብሮን እዚህ ተጣልታችሁ ነበር እንዴ?" አላት
" አዎ ...ዝም ብሎ እራሱን እየቆለለ ታፈቅሪኝለሽ እውነቱን ንገሪኝ እያለ
ሲጨቀጭቀኝ አናደደኝና ተናገርኩት ሰደብኩት "
" እና እውነት አንቺ እሱን አታፈቅሪውም " አላት ጠንከር ብሎ
" ማ .... እኔ እሱን ላፈቅረው እንዴ ትቀልዳለህ ድፍረታቹሁ በምን ሂሳብ ነው
እሱን የማፈቅር የሚመስላቹሁ?" አለችው
" ፍቅር የሚመስልና የማይመስል ነገር አይደለም ........... ለማንኛውም እኔ
እዚህ እቆያለው ወደ ቤት ከሄድሽ በዛው አየት እያረግሽው ብቻውን ስለሆነ ጥሩ
አይደለም ።" አላት
" እንዴ ምን ሆነ ደግሞ ?" አለች ደንገጥ ብላ
" መንገድ ላይ ወድቆ ልቡንና ጭንቅላቱን አሞት ተኝቷል" አላት እሷ ደንግጣ
ከተቀመጠችበት በመነሳት አይን አይኑን ስታየው እሱም ተገርሞ አያት።
" በእኔ ነው እንደዚህ የሆነው ..... እሱ ቀልድ አያውቅም እንዴ እንዴት እንዲህ
ያመራል ምን ዓይነቱ ልጅ ነው በፈጣሪ"
" ታፈቅሪዋለሽ ማለት ነው?" አላት እሷ ደንገጥ አለችና።
" እሺ አሁን የት ነው ያለው ?........ ተወው ለካ እቤት ነው ብለሀኛል ..... በቃ እኔ
ሄጃለው " አለችውና ቻው ሳትለው እየሮጠች ሄደች።
በፖሊስ ጣቢያ የምርመራ ቢሮ ውስጥ መርማሪው ከሰላም ጋር ፊት ለፊት
እየተያዩ በምርመራ አጣድፏታል እሷ ግን ካለ ምንም ጭንቀት በአግባቡና
በተረጋጋ ስሜት ውስጥ ሆና ትመልሳለች ።
" ቆይ ያኔ ምሽት እኔጋ እንደነበረ ማን ነው የተናገረው" አለች
" ምን ይሰራልሻል ማወቁ ግን የሙያ ግዴታችንም አይፈቅድም መናገር
አንችልም ግን አንቺ እውነቱን ብትነግሪን ይሻላል " አላት መርማሪው ።
" እንግዲያውስ ምንም የምነግርህ ነገር የለም እኔ አልገደልኩም ነፍሰ ገዳይም
አይደለሁም " አለች በተረጋጋ ስሜት ። መርማሪው በግርምት ፍጥጥ ብሎ
ተመለከታት ።
" በጣም ግራ ያጋባል በዛች ደቂቃ ከአንቺ ጋር ከነበረ ከዛ በኋላ ወጥቶ በሌላ
ሰው መገደሉ አስገረመኝ " አላት።
" እኔ ....... እኔጋ ነበር ያን ምሽት አልኩሁ እንዴ?" አለችው
" አንቺማ አላልሺም ነገር ግን ያን ምሽት አንቺ ጋር እንደነበረ አሳማኝ ማስረጃ
አለ" አላት መርመሪው በአትኩሮት እየተመለከታት ።
" በቃህ ሌላስ የለህም ...... ትሰማኛለህ ባልተረጋገጠ መረጃ አንድ ግለሰብ
በቂም ተነሳስቶ ይሁን በሌላ ሳታውቅ ከመሬት ተነስተህ ይሄን ያህል ሰዓት
በማጉላላትህ በህግ እጠይቀሀለው እኔ ንፁሁ ኢትዮጵያዊ ዜጋ እንጂ ገዳይ እና
ባለጌ ሰው አይደለሁም ገላለች ወይም ስትገል አይቻታለው የሚል ምስክር ካለህ
እሰረኝ እሺ " አለች በጩሀት
" ልታስፈራሪኝ እየሞከርሽ ነው " አላት በግርምት እያያት ።
" ለምን አስፈራራሀለው እውነታውን መናገሬ ነው ስገል ያየኝ ምስክር ካለህ
እሰረኝ አለበለዚያ ግን ስራዬን አታስተጓጉልብኝ እሺ መርማሪ " አለች ቆፍጠን
ባለ ንግግር ።
" ጥሩ ነው በእራስ መተማመንሽ " አላት
" ታውቃለህ ከልጅነት ጀምሮ አንድ ቀን ደስታየን ማየት ለነፈቃት ምስኪን ሴት
እስር ቤት መግባት ለእሷ ምንም ማለት አይደለም ........ ቆይ አንተ ዛሬ እኔን
አስቀምጠህ ህግ ምናምን የምትለኝ እኔ ዘላለሜን በሰው ልጅ ስሳቃይ የት
ነበራቹሁ ህግ ለእኔ የታሰረ ለሌላው የተፈታ ነው እኔ በህግ ፊት በተደጋጋሚ
ቆሜ ለምኛለው ማን ሰማኝ አሳማኝ ማስረጃ አምጪ እንጂ የተባልኩት ስለዚህ
ተውኝ እሺ ..... መሄድ እችላለው የምትለኝ ከሌለ" አለችው
" ትችያለሽ ሂጂ አሁን ማንም ሳይሆን ተጠርጣሪው አንቺ ነሽ ማስረጃውን
በመያዝ ዳግም እንደምንገናኝ ተስፋ አረጋለው "
" ካገኘህ የእዛ ሰው ይበለን .... ይቅናህ " ብላው ገልምጣው በሩን ከፍታ
ከታረቀኝ ጋር ወጣች ።
" እንዴት እና ምን ብለሽ አመለጥሽ " አለ ታረቀኝ በጣም ከመፍራቱ የተነሳ ላብ
በላብ ሆኖ ሰውነቱ እየተቀጠቀጠ ።
" እኔ እንደ አንተ ላባም ቀጥቃጣ አይደለሁም ለእያንዳንዱ ውሳኔ መልስ ምት
እያዘጋጀው ነው አሁን ምንም አያመጡም አትፍራ እሺ " አለችው ታረቀኝ በደስታ
ዘሎ አቀፋት እና ሲስማት ከሰውነቷ እራቅ አረገቺውና " .... ባክህ ልቀቀኝ
ልጅነትህን አልጨረስክም እኔ ፊጥጥ ብለህ መታዘል የምትፈልገው " አለችና
ተያይዘው ወደ መኪናቸው ሄደው በመግባት መብረር ጀመሩ ።
ማክዳ የኮዶሚኒየውን ደረጃ በፍጥነት በመውጣት ቁና ቁና እየተነፈሰች ኮሪደሩን
ቤቷን እንኳን ዘወር ብላ ሳታይ አልፋ የዕነ ሚኪን በር ከፍታ ዘላ ገባች ። ኬብሮን
ጀርባውን ለበሩ ሰጥቶ ተኝቶ ያቃስት ነበር ደንግጣ ሄደች ተንበርክካ እያለቀሰች

" አሳመምኩሁ አይደል እኔ እኮ ደደብ ጨካኝ የማረባ ነኝ ይቅርታ አድርግልኝ
እባክህ .... እስቲ ቆይ ምንህን ነው ዘወር ብለህ እየኛ ....." አለች እያለቀሰች ዕነ
ሚጣ ከጀርባዋ ሆነው እያያት ሲሳሳቁ ቆዩና ተነስተው ሊወጡ ሲሉ አየቻቸው እና
ነገሬም ሳትል ዘወር ብላ ወደ እሷ ገለበጠችውና ግንባሩን እየሳመችው
ጠየቀችው ልቡንና ጭንቅላቱን አሳያት ።
" እሺ ተነስ ና ሀኪም ቤት እንሄዳለን ተነስ ዶ/ር ይይህ " አለች
" እእእ ....አልሄድም " አላት ለምን እያለች ስተጨቀጭቀው
" ... ምክንያቱም በሽታዬም ዶክተሬም አንቺ ስለሆነሽ" አላት እና ጣቶቹን ፀጉራ
ውስጥ ሰክቶ ጭንቅላቷን ጉቱቶ ከንፈሯን ከንፈሩ ላይ ለጠፈው አፏ ተግደረደረ
ግን ልቧ አሸነፈ አንዱን እጁን ይዛ ከጡቶቿ ውስጥ ከተተችው የፈለገውን
እንዲነካካ ፈቀደችለት ልብስ ለማውለቅ ደቂቃ አልፈጀባቸውም።......

@Kooblife
@Kooblife

For any comment
@Ethio96bot