Get Mystery Box with random crypto!

ኮኬት

የቴሌግራም ቻናል አርማ koketi2012poultry — ኮኬት
የቴሌግራም ቻናል አርማ koketi2012poultry — ኮኬት
የሰርጥ አድራሻ: @koketi2012poultry
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.30K
የሰርጥ መግለጫ

ስለ ዶሮ እርባታ እና እንቁላል መረጃ ለማግኘት በዚህ Link ወደ channalachn ይቀላቀሉ።
https://t.me/joinchat/Skco_yn435jyGhWv
"መረጃ (Information) ማለት ገንዘብ ማለት ነው...."

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-07-01 06:58:58 አዲስ ዜና

ግብርና ሚንስቴር የዶሮና እንቁላል ዝውውር በተመለከታ አዲስ መመርያ አውጥቶአል።
በመመሪያው መሰረት ፣
1ኛ• ወረርሽኙ ያልተከሰተባቸው አካባቢዎች ( free zone) ያሉ ፋርሞች የምያመርቱትን እንቁላል እና ሥጋ ግብይት ማድረግ የሚቻል መሆኑ
2ኛ• ወረርሽኙ በተከሰተ አከባቢ ያሉት ፋርሞች የምያመርቱትን እንቁላል እና ሥጋ በግብርና ሚናስቴር እውቅና በተሰጠው አካል እና ባለሙያ አማካኝነት የላብራቶሪ ምርመራ ( lab.Test) አድርጎ ከበሽታ ነፃ መሆኑ ከተረጋገጠ የእንቁላል እና የሥጋ ምርቶች ግብይት መፈፀም የሚቻል መሆኑ...

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዶሮ አርቢዎች እና አቀናባሪዎች ማህበር (EPPPA Board)
1.1K views03:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 21:12:13
እንቁላልና አቮካዶ ከልብ በሽታ ጋር ያላቸው ግንኙነት

ሰውነታችን በሕይወት ለመቆየት የሚያስፈልገው ዋናው ምግብ ቢሆንም፣ የይዘቱና የመጠኑ መለያየት ጤናማ ሆኖ ለረጅም ዘመን ለመቆየት የመቻላችንን ሁኔታ ይወስነዋል። የሰው ልጅ እንደሚበላው የምግብ ዓይነትና ጥራት በሽታን የመቋቋም ተፈጥሯዊ ብቃት እንደሚኖረውም ይታወቃል። አንዳንድ የምግብ ክፍሎችም በራሳቸው እንደመድኃኒት ስለሚያገለግሉ ጥቅማቸው ሰፊ እንደሆነ ይነገርላቸዋል።

@EthiopianBusinessDaily
598 views18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 19:53:59 yetekeberachu ye ye getsachn teketatayoch endet ameshachu?

Eskahun ehen yembal yeteregaget zena be higaw akal yeweta alagegnenm.

Esk enate kagegnachu linkun lakuln.
672 views16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 17:36:48
በወልቂጤ የዶሮ በሽታ ባልተከሰተበት ሁኔታ አምራቾች ለከፍተኛ ኪሳራ መዳረጋቸውን ተናገሩ

የግብርና ሚኒስቴር በዶሮ ላይ በተከሰተ በሽታ በርካታ ዶሮች መሞታቸውን ተከትሎ እንቁላል እና የዶሮ ግብይት ላይ እገዳ መጣሉ ይታወሳል፡፡ ሆኖም ግን በሽታው ባልተከሰተበት በወልቂጤ ከተማ የሚገኘው የጃሮ አግሮ ኢንዱስትሪ በእየለቱ ምርት እያመረተ ቢሆንም ሽያጭ ማከናወን ባለመቻሉ ለከፍተኛ ኪሳራ መዳረጉን በአንድ አምራች የዶሮ እርባታ ላይ የተሰማሩት አቶ ብርሃኑ ደምሴ ቅሬታቸውን ለብስራት ሬዲዮ ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባና በቢሸፍቱ በተወሰኑ የዶሮ እርባታ ማዕከላት የተከሰተው የዶሮ በሽታ ወደ ሌሎች የእርባታ ጣቢያዎችና የሀገሪቱ ክፍሎች እንዳይዛመት ግብረሀይል ተቋቁሞ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ የግብርና ሚኒስቴር ማሳወቁ ይታወሳል፡፡ሆኖም ግን የበሽታው ደረጃ በተመለከተ ወቅታዊ መረጃ ባለመገለፁ አርቢዎች እንቁላል ሸጠው ለዶሮዎች መኖ መግዛት አለመቻላቸውን ቅሬታ አቅራቢዎች ገልፀዋል።

ለአብነትም በመኖ እና በሰራተኞች ክፍያ ከሁለት ሚሊየን ብር በላይ ለኪሳራ መዳረጋቸውን ቅሬያ አቅራቢው ይገልጻሉ፡፡የበሽታውን መንስኤና ምንነት ለማጥናት የጥናት ቡድን ተቋቁሞ ናሙና እየተሰባሰበ መሆኑ በመግለጽ ውጤቱ ሲታወቅ ለሕዝብ ይፋ ይደረጋል ሲል ግብርና ሚንስቴር አሳዉቆ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ሆኖም ግን ብስራት ሬዲዮ በተደጋጋሚ ጉዳዩ ከምን ደረሰ በሚል ላነሳዉ ጥያቄ መግለጫ እንሰጥበታን በሚል ምክንያት ምላሽ ማካተት አልተቻለም፡፡ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት በአርቢዎቹ፣ በዘረፉ ብሎም በሀገሪቷ ኢኮኖሚ ላይ እየደረሰ ያለውን ትልቅ ተፅዕኖ ከግምት ውስጥ ሊገባ እንደሚገባ በዘርፉ ባለሙያዎች ቅሬታ እየቀረበ ይገኛል፡፡
516 views14:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 17:35:14
635 views14:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 16:59:51
683 views13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 15:08:44
700 views12:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ