Get Mystery Box with random crypto!

በደብረ ታቦር መለኮት ተገለጠ በደማቅ ብርሃን አበራ በተቀደሰው የታቦር ተራራ። የአብ አባትነት | መንፈሳዊ ኪነ ጥበብ ብቻ

በደብረ ታቦር


መለኮት ተገለጠ በደማቅ ብርሃን አበራ
በተቀደሰው የታቦር ተራራ።
የአብ አባትነት የወልድ ልጅነት
በግልጽ ታወቀ ተነገረ በእውነት
ዮሐንስ ጴጥሮስን ያዕቆብን ጠርቶ
ሙሴን ከመቃብር ከሙታን አንሥቶ
ከብሔረ ሕያዋን ኤልያስን አምጥቶ
በአምላክነቱ ፍጹም አንጸባርቆ
በሕያው መለኮቱ በብርሃን ደምቆ
አብም ተገለጠ በብሩህ ደመና
የምወደው ልጄ ክርስቶስ ነውና።
እርሱን ብቻ ሰሙት እስከ ዘለዓለም
ሕይወት በእርሱ ነው ያለርሱ አትድኑም።
ብሎ ስለልጁ በግለጽ መሰከረ
አምላክነቱንም በተግባር ነገረ።
https://t.me/kinexebebe