Get Mystery Box with random crypto!

ሳልፆም ሊፈሰክ ነው። አይ የኔ ነገር እርግጥ አልበላሁም ስጋም ሆነ ቅቤ አልፆም አለኝ እን | መንፈሳዊ ኪነ ጥበብ ብቻ

ሳልፆም ሊፈሰክ ነው።
አይ የኔ ነገር

እርግጥ አልበላሁም ስጋም ሆነ ቅቤ
አልፆም አለኝ እንጂ አመፀኛ ልቤ
ካምናና ካቻምና የዘንድሮ ብሶ
መላ ማንነቴ በሀጢያት ተለውሶ
ስዋሽ ስቀጥፍ
ህግን ስተላለፍ
ስሰድብ ሳደማ
የሰው ስጋ ሳማ
ባይኔ ሳመነዝር
የሰው ሰው ሳማትር
ገላዬን ሳራቁት
አዳምን/ሔዋንን ሳሳስት
ስረሳ ስቃይህን
መስቀል ህማምህን
ያን ሁሉ ግርፋት
ነብሴ ሳያስጨንቃት
አይ እኔ
በሀሰት ስመሰክር
በሀጢያት ስዳክር
ለማይሞላ ኑሮ
ሳልሻል ዘንድሮ
ፆሙ ተጋመሰ
ጊዜው ተጋመሰ
ጌታ ሆይ
አቤቱ አስበኝ
ለንሰሀ አብቃኝ
እስቲ የቀረውን ለበረከት በለው
አመፀኛ ልቤ ፆምህን ይፁመው
"ከደጀ ሰላሙ ከካህኑ እግር ስር
ንስሀዬን ልውሰድ ስለመስቀል ፍቅር"

የንሰሀ ህይወት ይስጠን!፦
@kinexebebe