Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹ዘወልድ ምክረ-ሕግ🇪🇹‼️

የቴሌግራም ቻናል አርማ khalidkebede — 🇪🇹ዘወልድ ምክረ-ሕግ🇪🇹‼️
የቴሌግራም ቻናል አርማ khalidkebede — 🇪🇹ዘወልድ ምክረ-ሕግ🇪🇹‼️
የሰርጥ አድራሻ: @khalidkebede
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.22K
የሰርጥ መግለጫ

ቻናሉ ሕጎችንና የፍ/ቤት ዉሳኔዎችን ያጋራል። አጫጭር የሕግ ማብራሪያዎችንና የምክር አገልግሎቶችን ይሰጣል።
ጠበቃ ካሊድ ከበደ እና ጠበቃ አማረ እሸቱ
በማንኛዉም የፌዴራል እና የክልል ፍ/ቤት ጠባቃና የሕግ አማካሪ
ስልክ- 0935439820
ኢሜይል- khalidbinkebe@gmail.com

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-02 18:02:04 ጉባዔው በ26 የሕገ መንግሥት ትርጉም ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።
--------------------------------------------------------------------------------
የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ረቡእ ሚያዝያ 05 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ 26 ጉዳዮች ላይ በመወያየት 25ቱ የሕገ መንግሥት ትርጉም አያስፈልጋቸውም በማለት እንዲዘጉ የወሰነ ሲሆን፤ በአንድ ጉዳይ ላይ በሰፊው በመወያየት ጉዳዩ ተጨማሪ ጥናት እንዲደረግበት በይደር እንዲያልፍ ወስኗል።
ሰፊ ውይይት የተደረገበትና ተጨማሪ ጥናት እንዲደረግበት የተወሰነው ጉዳይ የንብረት ክርክር ጉዳይ ሲሆን ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት የስምንት ሰዎች ይዞታ የተመዘገበ ሆኖ እያለ ፍ/ቤቱ ከስምንቱ አመልካች አንዱ ሆነው የቀረቡትን የተከሳሽ ሚስትንና ተከሳሽ ሆነው የቀረቡትን ባል በማከራከር የከሣሽ እና ተከሣሽ የጋራ ሀብት ነው በማለት ይወስናል፡፡ የተቀሩት ሰባቱ ባለይዞታዎችም ውሳኔውን በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 358 በመቃወም ጣልቃ ገብ አመልካች ሆነው ወደ ክርክሩ ቢገቡም ፍ/ቤቱ በክርክሩ ሂደት ወቅት ግማሾቹ በምስክርነት የቀረቡ ሌሎቹ ደግሞ ችሎት እየገቡ ሲከታተሉ የነበሩ በመሆኑ መብታቸውን ለማስከበር ጣልቃ በመግባት መከራከር እየቻሉ የክርክሩን ውጤት ጠብቀው መብታቸውን የሚነካ ውሣኔ ሲሰጥ በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 358 መሠረት ያቀረቡት ተቃውሞ ተቀባይነት የለውም በማለት ብይን ይሰጣል፡፡ የይግባኝ አቤቱታቸውን ለፌ/ከ/ፍ/ቤት ቢያቀርቡም ፍ/ቤቱ አስቀርቦ በማከራከር የስር ፍ/ቤት ውሣኔን አፅንቷል፡፡ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም አያስቀርብም በማለት ጉዳዩን በመዝጋቱ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መ.ቁ. 201187 እና 187023 የሰጣቸው ውሣኔዎች በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 40/1፣ 2፣ 7 እና 81 ስር የተደነገጉትን የንብረት መብቶች እና በአንቀጽ 9/1/ የተደነገገውን የሕገ መንግሥት የበላይነት ድንጋጌን ስለሚቃረን የሕገ መንግሥት ትርጉም ይሰጠን በማለት ጠይቀዋል፡፡
ጉባዔውም በጉዳዩ ላይ በስፋት የተከራከረ ሲሆን በአንድ በኩል ከላይ ፀንተው ያሉት ሁለቱ ውሣኔዎች ለሕገ መንግሥት ትርጉም አቤቱታ የቀረቡ ቢሆንም ሁለቱም የፍ/ቤቶቹ ውሣኔዎች ማስረጃን በመመዘን እና ሕግን በመተርጎም የተወሰኑ በመሆናቸው የአመልካቾችን የትኛውንም ሕገ መንግሥታዊ መብት የሚፃረሩ አይደሉም የሚል ሀሳብ ቀርቧል፡፡
በሌላ በኩል የፍ/ስ/ስ/ህጉ ቁ. 358 ድንጋጌ ይዘት ሲመረመር በዋና ክርክር ወቅት ተካፋይ መሆን ሲገባው በክርክሩ ተካፋይ ያልሆነና ወይም በክርክሩ መብት ያለው እና ተካፋይ ባልሆነበት ክርክር የተሰጠው ፍርድ መብቱ የተነካበት ሰው ፍርዱ ከመፈጸሙ በፊት የመቃወም አቤቱታ አቅርቦ መከራከር እንደሚችል በግልጽ ስለሚገነግግ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መዝገብ ቁጥር 56795 ላይ አንድ ክርክር መጀመሩን ያወቀ ወገን የክርክሩን ውጤት ጠብቆ መብቱን የሚነካበት ሆኖ ባገኘው ጊዜ ከውሳኔው በኋላ የሚያቀርበው አቤቱታ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 358 መሰረት ተቀባይነት የለውም ብሎ የሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም ህግን ከመተርጎም ስልጣኑ ያለፈና የአመልካቾችን ንብረት የማፍራት መብት የሚጻረረር በመሆኑ ውሳኔው የሕገ መንግስቱን አንቀጽ 37፣ 40 እና 79(1) ድንጋጌ ስለሚቃረን የሕገ መንግሥት ትርጉም ያስፈልገዋል የሚል ሀሳብ ቀርቧል፡፡ ጉባዔውም በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ጥናት እንዲደረግበትና ለቀጣይ ውይይት እንዲቀርብ ወስኗል፡፡
178 viewsKhalid Kebede, 15:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 23:39:26 የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 205827 ህዳር 27ቀን 2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት የአብክመ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 23(2) ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ አላማውን በማያሳካ መንገድ ተርጉሞታል በማለት አስገዳጅ ውሳኔ ሰጠ ።

ጉዳዩ የተነሳው ያረጋል ተገኘ የተባለ ተከሳሽ መስከረም 11/2012 ዓ/ም በአንከሻ ጓጉሳ ወረዳ 1 ቱርክ ሽጉጥ ከመሰል 31 ጥይቶች ጋር ይዞ በመገኘቱ ዐቃቤ ህግ የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 4(1) እና 22(2) ላይ የተመለከተውን ተላልፎ ጦር መሳሪያ ይዞ ተገኝቷል በሚል ክስ መስርቶበት የአንከሻ ጓጉሳ ወረዳ ፍ/ቤት ተከሳሸን ባመነው መሰረት ጥፍተኛ በማለት 2ወር ቀላል እስራትና 600ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ስለወሰነና ውሳኔ የአዊ/ብ/ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ስላጸናው በተከሳሽ ይግባኝ ጠያቂነት የአብክመ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 23(2) ላይ የተመለከተውን የጊዜ ገደብ በመጥቀስ ተቆጣጣሪ ተቋሙ የጊዜ ገደብ አውጥቶ ምዝገባ ባልጀመረበት ሁኔታ ተከሳሽን ጥፋተኛ ብሎ መቅጣት ህጋዊ መሰረት የለውም በማለት የስር ፍ/ቤቶችን ውሳኔ በመሻሩ የአብክመ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ለፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ይግባኝ በማቅረቡ ነው ።
ይግባኝ የቀረበለት የፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም ፦
1ኛ የአዋጁ አንቀጽ 23(2) ጊዜ ሰሌዳ ያስቀመጠ ቢሆንም ቅሉ በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ ሆኖ ማነኛውም ግለሰብ ጦር መሳሪያ ይዞ ቢገኝ ከተጠያቂነት እንደሚድን አያስቀምጥም ።
2ኛ የአዋጁ መሰረታዊ አላማ የጦር መሳሪያን ወደ ህጋዊ ስርዓት አስገብቶ መቆጣጠር እንጅ በዚህ አንድ አመት ጊዜ ውስጥ ማንኛውም ግለሰብ የጦር መሳሪያ ይዞ ለመገኘት ፈቃድ የሚሰጥ አይደለም ፤ የጊዜ ገደቡ የሚያገለግለው ጦር መሳሪያው በምዝገባ ሂደት ላይ እያለ ችግር እንዳያጋጥም እንጅ የአንድ አመት የመያዝ ፈቃድ የሚሰጥ ተደርጎ መተርጎም የለበትም ፤
ስለሆነም የጊዜ ገደብ መቀመጡ እስከ አንድ አመት ያለማንም ጠያቂነት የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመፍቀድ ታስቦ የተደነገገ አድርጎ መተርጎም የህዝብን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የወጣውን አዋጅ አላማ የሚያሳካ ካልመሆኑም በተጨማሪ ተከሳሹ በሰጠው የእምነት ቃል መሰረት ጦር መሳሪያውን የያዘው ነባሩ አዋጅ በስራ ላይ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ መሆኑ ያልተካደ በሆነበት ሁኔታ ተከሳሽን ከተጠያቂነት ነጻ ማድረግ የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 23(2) ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ አላማ ባልተገባ መንገድ በመተርጎም መሰረታዊ የህግ ስህተት መፈጸም ነው በማለት የወረዳውንና የከፍተኛውን ፍ/ቤቶች ውሳኔ አጽንቶ የአብክመ ጠ/ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ ሽሮታል ።
Please share it ( እባክዎ ያጋሩት)
በ ተስፍሽ ዐቢሲኒያ
635 viewsKhalid Kebede, 20:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 21:34:07
1.8K viewsKhalid Kebede, 18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 21:33:56 ሁለት ነገር!
1. ከብዙ ጥረት በኋላ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ት/ቤት የከፈተ በመሆኑ እንኳን ደስ ያለን!

2. የሕግ ዲግሪ በኤክስቴንሽን መማር ለምትፈልጉ ሁሉ እነሆ እድሉ ተመቻችቷል፤ ጊዜው ሳያልፍ ይመዝገቡ! ዝርዘሩን ከስር ከተለጠፈው ማስታዎቂያ ማግኘት ይችላሉ!
1.7K viewsKhalid Kebede, 18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 20:37:54 በሀሰተኛ ሰነድ መገልገል ወንጀል የተከሰሰው ተከሳሽ ላይ በፅኑ እስራት እና የገንዘብ ቅጣት ተወሰነ ተከሳሽ ሞገስ ሙላት ለራሱ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ የላይ አርማጭሆ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ በቁጥር የሰ/ሃ/459/09 በቀን 15/02/2009 ለትክል ድንጋይ መሪ ማዘጋጃ ቤት ሲቪል መኃንዲስ ባወጣው ማስታወቂያ ተወዳዳሪዎች ለትምህርት ደረጃው መነሻ የብቃት ማረጋገጫ COC ማቅረብ እንዳለባቸው ማስታወቂያው ስለሚገልፅ ተከሳሽም በዚህ ማስታወቂያ ከሳንጃ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ደረጃ lV በኢንሳይት ቢውልዲንግ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት የተሰጠ ማስረጃ በመያዝ ለዚህም የትምህርት ዝግጅት የብቃት ማረጋገጫ እንዳለፈ በማስመሰል በፌዴራል ትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሙያ ብቃት ምዘናና ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ በመለያ ቁጥር CONBBC 2014 _ 2017 _03_ 154548 በሐሰት በማዘጋጀት በወጣው ማስታወቂያ ተመዝግቦ በማለፍ እና ስራ ላይ ሆኖ እየተገለገለ ብር 59,930.00 የማይገባውን ክፍያ /ጥቅም በማግኘቱ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፓሊስ መምርያ የሙስና ወንጀል ምርመራ ዋና ክፍል በተከሳሹ ላይ ምርመራ አጣርቶ ለማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፍትሕ መምርያ የሙስና ጉዳይ ወንጀል የስራ ሒደት በመላክ የዞን ዐቃቤ ሕግ መዝገቡን ምርምሮ በሰውና እና በሰነድ ማስረጃ ወንጀሉ ሰለመፈፀሙ አረጋግጦ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 23/3/ የተመለከተውን በመጥቀስ ክስ መስርቶ ለማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ክስ በማቅረብ ጉዳዮ በክርክር ቆይቶ በ28.8.2014 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ3 አመት ፅኑ እስራት እና በብር 60,000 እንዲቀጣ ተወስኗል በማለት መረጃውን ያደረሰን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፍትሕ መምሪያ ነው።
972 viewsKhalid Kebede, 17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 23:04:47 የአብክመ የተሻሻለው የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 253/2010
1.0K viewsKhalid Kebede, edited  20:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 23:01:01 የአብክመ ማህበራዊ ፍ/ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 246/2009
990 viewsKhalid Kebede, edited  20:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 22:00:15 የጦር መሣሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 - መንግሥት በፉጨት የጠራውን በጅራፍ የገረፈበት ሕግ

“The execution of the laws is more important than the making of them” Thomas Jefferson

“የሕጎች አተገባበር ሕጎቹን ከመደንገግ በላይ አጅግ አስፈላጊ ነው”

“ይህ ጽሑፍ በሕግ ትምህርት ዘርፍ በተለይም በውል ሕግ ዙሪያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉት ዛሬም በሕግ ሥርዓቱ መሻሻል ላይ አሻራቸውን እያኖሩ ላሉት ለፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ ትንሽ ምስጋና ትሁንልኝ”

ዛሬም ያልተላቀቅነው እርግማን ነው፡፡ ትውልድ ቢቀያየርም፤ መሪ ቢለዋወጥም፤ ዓለም ብትሰለጥንም፤ ዕውቀት ቢገባንም፤---ትላንት ታሪካችን ነበር፡፡ “የኢትዮጵያ ታሪክ” ብለው በልጅ አዕምሮ ያስተማሩንም ይህንኑ ነው….‘የእርስ በእርስ ጦርነት’፡፡ዛሬም ይህ ትውልድም ይህን እርግማን ዕውቀት አድርጎት እርስ በእርሱ እየተገዳደለ የራሱን ታሪክን በመጻፍ ላይ ነው፡፡ የኢፌዲሪ መንግሥትም “የሕግ ማስከበር ዘመቻ” ብሎ ለጠራው ለዚህ ጦርነት “ወንዱን ትጥቅ ሴቷን ስንቅ” ይዛችሁ ውጡ ብሎ አስቸኳይ አዋጅ በነጋሪት ጎስሞ ከድሉ መልስ በጦርነቱ ጊዜ ለተጠቀምብክበት ትጥቅ ፍቃድ የለህም ብሎ ታህሳስ 30 ቀን 2012ዓ.ም ባወጣው የጦር መሣሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 በሕግ ጅራፍ ህዝቡን ዛሬም እየገረፈ ነው ብልህ---ምላሽህ እንደ ገብረሕይወት ባይከዳኝ “ጃንሆይ ይህን ህዝብ ግን እንደራስዎ ህዝብ ያዩታል?” የሚለው ጥያቄ አይሆንም ወዳጄ? ተከተለኝማ ነገሩን ልዝለቅህ…



1. መነሻ ምክንያት

አንድ

የፌደራል ዐቃቤ ሕግ በተከሳሽ ላይ በጥቅምት 2 ቀን 2013 ዓ.ም የጦር መሣሪያ ፍቃድ ሳይኖረው 16 ጥይትና 01 ካርታ ይዞ በመገኘቱ የጦር መሣሪያ አስተዳደር ቁጥጥር አዎጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 4/1/ እና 22/3/ ተላልፎል የሚል በማቅረቡ ነው፡፡ ተከሳሹ የተከሰሱባቸው መሣሪያዎች አስቀድመው ከያዙትና ፍቃድ ካላቸው መሣሪያዎች በተጨማሪ ነው፡፡

ሁለት

መንግሥት በህልውናው ዘመቻ ጊዜ ያወጣሁን ልዩ መመሪያ ተከትሎ የያዘውን ሽጉጥና 1 ጥይት አስመዝገቦ በዘመቻው ከተሳተፈ በኃላ ዘመቻው ሲጠናቀቅ ግለሰቡን ተከሳሽ በማድረግ ከሳሽ በየካቲት 7 ቀን 2014ዓ.ም የጦር መሣሪያ ፍቃድ ሳይኖረው 1 ጥይትና አንድ ሽጉጥ ይዞ በመገኘቱ የጦር መሣሪያ አስተዳደር ቁጥጥር አዎጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 4/1/ እና 22/3/ ተላልፎል የሚል ክስ በፌደራል ዐቃቤ-ሕግ የቀረበባቸው መሆኑ ነው፡፡

2. የጦር መሣሪያ አስተዳደር ቁጥጥር አዎጅ ቁጥር 1177/2012 የአተገባበር አድማስ

ይህ የጦር መሣሪያ አስተዳደር ቁጥጥር አዎጅ በአንቀጽ ቁጥር 29 ላይ ከታህሳስ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ተፈጻሚ እንደሚሆንና የደነገገ ቢሆንም በመሸጋገሪያው ድንጋጌ በሆነው አንቀጽ ቁጥር 23(1) ላይ ይህ አዋጅ ከመጽናቱ በፊት መሣሪያ የያዙና ለያዙት የጦር መሣሪያ ፍቃድ የመያዝና የመጠቀም ፍቃድ ያላቸው ሰዎች በሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ተቆጣጣሪው ተቋም በሚያወጣው የጊዜ ሰሌዳ ቀርበው ፍቃድ የመጠየቅና በአዎጁ የተመለከቱትን መስፈርቶችን አሟልተው ከተቆጣጣሪው ተቋም ፍቃድ መውሰድ እንዳለባቸው ተደንግጓል፡፡
እንደዚሁም ይህ አዋጅ ከመጽናቱ በፊት ፍቃድ ሳይሰጣቸው ግን ደግሞ የጦር መሣሪያ የያዙ ሰዎች ደግሞ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተቆጣጣሪው ተቋም በሚያወጣው የጊዜ ሰሌዳ ቀርበው ፍቃድ የመጠየቅና በአዎጁ የተመለከቱትን መስፈርቶችን አሟልተው ከተቆጣጣሪው ተቋም ፍቃድ መውሰድ እንዳለባቸው በአንቀጽ ቁጥር 23(2) ላይ ተደንግጓል፡፡
በመሆኑም አስቀድሞ በነበረው የሕግ አሰራር የጸና ፍቃድ ያላቸው ግለሰቦች በአንቀጽ 23(1) መሰረት ቀርበው አዲስ ፍቃድ ለማውጣት የሁለት ዓመታት ማለትም እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2014ዓ.ም ጊዜ ድረስ አላቸው፡፡
እንደዚሁም አስቀድሞ በነበረው አሰራር ፍቃድ ሳይኖራቸው የጦር መሣሪያ የያዙ ሰዎች ደግሞ የአንድ ዓመት ማለትም እስከ ታኀሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ፍቃድ የማውጣት መብት በሕጉ ተሰጥቷቸዋል፡፡
በተለይም የጦር መሣሪያ የያዙ ግለሰቦች ከላይ የተመለከተውን ግዴታቸውን እንዲወጡ አዲስ ፍቃድ እንዲያወጡ የጊዜ ሰሌዳ የማስቀመጥ ግዴታ በተቆጣጣሪው ተቋም ላይ ተጥሏል። ዳሩ ግን ተቋጣጣሪ ተቋሙ የጊዜ ሰሌዳ አላወጣም። በዚህም ተቋሙ ይህን መንግሥታዊ ግዴታውን አልተወጣም። ስለዚህ የማስመዝገቢያ ጊዜ ባላለፈበት፣ መመሪያና የጊዜ ሠሌዳ ባልወጠዓበት ሁኔታ ግለሰቦችን ተፈጻሚ ሊደረግ የማይገባባቸውን የጦር መሣሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ 1177/2012ን መሠረት በማድረግ ምንም ዓይነት ክስ ሊቀርብ አይገባም።
ነገር ግን ዛሬም እራሱ መንግሥት ላልተወጣው ግዴታ ግለሰቦችን እየቀጣ ነው፡፡ ፍ/ቤቶችም እንደ ሦስተኛ የመንግሥት አካልነታቸውና ሌሎች የመንግሥት አካል የሆኑትን ሕግ አውጪና ሕግ አስፈጻሚ በcheck & balance ስልጣናቸው መቆጣጠርና ይህ አለመተግበሩን በመከታተል ግለሰቦችን ነጻ ሊያደርግ ሲገባው ሕጉን እንደ ወረደ በመተግበር የአስፈጻሚው አካል ጅራፍ የሚጮህበት ሜዳ መሆናቸው ሊቀር ይገባል፡፡
3. ልዩ ሁኔታ

የጸና ፍቃድ የሌላቸው የጦር መሣሪያዎችን ሁሉ በአዲስ ምዝገባ ህጋዊ ለማድረግ መመሪያ የወጣ ስለመሆኑ

ሀገራችን የነበረችበትን ህልውና የማስከበር የጦርነት ዘመቻን ተከትሎ መንግሥት ማንኛውም ሰው የጸና ፍቃድ ባይኖረውም የጦር መሣሪያ የያዘ በሙሉ ይህን የጦር መሣሪያ እንዲያስመዘግብና አስቀድሞ ያለፍቃድ በመያዙም የወንጀል ተግባር ተደርጎ እንደማይቆጠር የሚገልጽ መምሪያ ወጥቶ ተግባራዊ ሲደደረግ ነበር፡፡
በተጨማሪም ማንኛውም የወንጀል ሕግን አስመልክቶ የሚወጣ ሕግና መመሪያ ለተከሳሹ ጥቅም የሚሰጥ ከሆነ ወደኃላ በመሄድ ተፈጻሚ ሊሆን የሚገባው ስለመሆኑ የሚደነግግው የወንጀል ሕጉ አንቀጽ ቁጥር 5(3) እና ኢትዮጵያ ያጸደቀችሁ ዓለምአቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብት የቃልኪዳን ሰነድ አንቀጽ ቁጥር 9(4) አንዱና ዋናው የሕጉ መርህ ነው፡፡
በመሆኑም ይህ ልዩ የመንግሥት የዘመቻ ጥሪና መመሪያ ያለፍቃድ የጦር መሣሪያ መያዝን አስመልክቶ በጦር መሣሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ 1177/2012 መሰረት ክስ የቀረበባቸውን እና ጉዳያቸው በፖሊስ በምርመራ ላይ ያሉ ጉዳዮችን ሁሉ ወንጀልነታቸውን ያስቀረ በመሆኑ ይህ ልዩ መመሪያ በስራ ላይ በነበረ ጊዜና ከዚያ በፊት በነበሩ ጉዳዮች ላይ አዎጅ ቁጥር 1177/2012 ተፈጻሚነት የለውም፡፡
4. ትግበራ

ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆኑኝን ምክንያቶች በግል የገጠሙኝ ጉዳዮች ሲሆኑ በትግበራ ላይ ያለውን ሂደት ለመጠቆም የሚረዱ ከመሆኑ ባሻገር አጠቃላይ ስለአተገባሩ መደምደሚያ ላይ ልንደርስባቸው የሚገቡ አይደሉም፡፡ በመሆኑም እናንተም የገጠማችሀን ጨምራችሁበት በዕውቀት ብርህን ይበልጥ እንድንቀራረብና ወጥ እና ታማኝ የሆነ የፍትሕ ሥርዓት ለመገንባት በሚደረገው ርብርብ የበኩላችንን እንድናዋጣ አደራ እላለሁ፡፡

አመሰግናለሁ! Dagim Assefa source Abyssinia Law blog , Apr 20 2022
2.7K viewsKhalid Kebede, 19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ