Get Mystery Box with random crypto!

ሚዛናዊ ሕይወት

የቴሌግራም ቻናል አርማ mizanawihewot — ሚዛናዊ ሕይወት
የቴሌግራም ቻናል አርማ mizanawihewot — ሚዛናዊ ሕይወት
የሰርጥ አድራሻ: @mizanawihewot
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 200
የሰርጥ መግለጫ

እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ፣ ያዝናናሉ ብየ/ለን ያሰብኩት/ናቸውን ማንኛውም አይነት ፅሁፎች ከተለያዩ channelና ካነበብናቸው እያሰባሰብኩ/ን አቀርባለው/ን። የአንድ አስተሳሰብ እስረኛ አትሁን። የሰው ልጅ ብስለት የሚለካው አንድ አስተሳሰብ ላይ ሙጥኝ በማለት ሳይሆን የተለያዩ አስተሳሰቦችን በብቃት ማስተናገድ የሚችል አእምሮ በመገንባት እንደሆነ እወቅ።
Creator @ela_T

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-10 14:19:29 አንዳንድ ቀልድ የሚያበዛ ሰው ቁምነገር አያቅም ማለት አይደለም! ቁምነገሩን በቀልድ ስለሚያዋዛው እኛ ንግግሩ ፍጹም ልቦለዳዊ ፈገግታን ጫሪ ብቻ ይመስለናል እንጂ!!!
#ሚዛናዊ_ሕይወት_ለተሻለ_ነገ
17 views11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 07:58:45 " ምርጥ የአፍሪካዊያን አባባሎች"(ከእውቀት ማዕድ ቃረምኩት)

1፦……"በችግርጊዜ ብልህ ሰው ድልድይ ሲገነባ፤ ሞኝ ደግሞ ግድብ ይገድባል!!"(ናይጄሪያዊያን)
*
2፦……"ሀብት ሲጠቀሙበት እያለቀ ይሄዳል፤ ትምህርት ግን እየተጠቀሙበት በሄዱ ቁጥር እየጨመረ ይሄዳል!!"(ታንዛኒያውያን)
*
3፦……"እውነቱን ላለማየት ዓይናችንን የምንጨፍን ከሆነ ልንማር የምንችለው ከአደጋ ይሆናል!!"(ኬንያዊያን)
*
4፦………"ከማሸነፍ ይልቅ በመሸነፍ ወቅት ብዙ ትምህርት ይገኛል!!"(ጋቦናዊያን)
*
5፦……" ሞኝ ጨዋታውን በሚለምድበት ጊዜ ተጨዋቹ ይበተናል!!"(አሻንቲዎች/ጋና)
*
6፦……" ምክር ልክ እንደ-እንግዳ ነው። የሚቀበለው ካገኘ ያድራል፤ የሚቀበለው ካጣ ግን የዚያኑ ቀን ተመልሶ ይሄዳል!!"(ኮንጎዎች)
*
7፦……" አዋቂዎች በበዙበት ቦታ የአዳማጭ ዕጥረት አለ!!"(የስህዋሊ አባባል)
*
8፦……" በአንበጣዎች መካከል የሚደረግ ፀብ ለከብቶች መዝናኛ ነው!!"(ቦትስዋናዊያን)
*
9፦……" ትልቅ ወንበር ብቻውን ንጉሥ ሊያደርግ አይችልም!!"(ሱዳናዊያን)
*
10፦……" በረሮ ዶሮዎችን የመምራት ሃሣብ ካለው፤ ቀበሮን ጠባቂው አድርጎ መቅጠር ይኖርበታል!!"(ሴራሊዮናዊያን)
*
11፦……" ቤተሰብ ልክ እንደ-ደን ነው። ከሩቅ ሲያዩት ጥቅጥቅ ያለ ሲሆን፤ ሲገቡበት ግን እያንዳንዱ የየራሱ ቦታ አለው!!"(ዛየራዊያን)
*
12፦……" የገንዘብ ስልት ከጦር ስልት ይበልጣል!!"(ካሜሮናዊያን)
*
13፦……" ገንዘብ ማውራት ባይችልም፤ ውሸትን እውነት የማድረግ አቅም ግን አለው!!"(ደቡብ አፍሪካዊያን)
*
14፦……" ከገንዘብ ውስጥ ስንወጣ አዋቂ እየሆንን እንሄዳለን!!"(አይቮሪኮስታዊያን)
*
15፦……" እስኪያወራ ድረስ እያንዳንዱ ሰው ውብ እና ቆንጆ ነው!!"(ዙምባቤዎች)
*
16፦……" ያለሰዓቱ የሚጮኽ ዶሮ መንጋቱን ሳይሆን መታረዱን ያውጃል!!"(ኢትዮጵያዊያን)
*
የትኛው ተራ-ቁጥር ላይ ያለውን አባባል ወደዳችሁት::
#ምርጥ_ከቁርስ_በፍት_እችን_ቅመሱዋት_እስቲ
#ሚዛናዊ_ሕይወት_ለተሻለ_ነገ
@mizanawihewot
21 viewsedited  04:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 22:02:13 ስለ ምስራቅ አፍሪካ ሀገራት 25 ዋና ዋና እውነታዎች

1. ኢትዮጵያ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ያላት (114,963,588 ሰዎች) አላት።

2. ሶማሊያ ከአካባቢው ትልቁ የባህር ዳርቻ አላት።

3. ኬንያ በክልሉ ከፍተኛ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) አላት።

4. ደቡብ ሱዳን በቀጣናው ቀዳሚ የነዳጅ ዘይት አምራች ሀገር ነች።

5. ጅቡቲ ከአካባቢው በጣም ትንሽ የህዝብ ቁጥር አላት።

6. ታንዛኒያ ከአፍሪካ ከፍተኛው ነጥብ ኤምቲ ኪሊማንጃሮ አላት።

7. ኢትዮጵያ በቀጣናው ጠንካራ ወታደራዊ ኃይል አላት።

8. ኢትዮጵያ በአፍሪካ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አላት።

9.ኬንያ በአለም ትልቁ የበረሃ ሀይቅ የቱርካና ሀይቅ አላት።

10. ዩጋንዳ ለኬንያ፣ ታንዛኒያ እና አቅራቢያ ለዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ሪፐብሊክ ክልሎች የኤሌክትሪክ ኃይል ያቀርባል።

11. ሩዋንዳ ከአፍሪካ ፅዱ ከተማ አላት።

12. ብሩንዲ በአንድ ወቅት ነገሥታት ነበሯት።

13. ኢትዮጵያ የንጉሥ ቤተመንግስት እና የአፄ ቤተ መንግስት ታሪካዊ ቦታዎች ያሏት ናት።

14. የኤርትራው ስም ዋና ከተማ ''አስመራ'' ማለት ''አንድ አደረጉአቸው'' ማለት ነው።

15. ኢትዮጵያ በምድር ላይ ትልቁን የአንበሳ ዝርያ ያላት ባርባሪ አንበሳ አንገቷ ላይ ጠቆር ያለ ፀጉር አላት

16. ሱዳን ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኢትዮጵያ ከ3500 ዓመታት በፊት የጀመረ ረጅም ታሪክ አላቸው።

17. ሱዳን በሰሜናዊ ግዛቷ ላይ አንዳንድ ጥንታዊ ፒራሚዶች አሏት።

18. ከአፍሪካ ትልቁ የንፁህ ውሃ ሀይቅ የሆነው ቪክቶሪያ ሀይቅ አለው።

19. እና ለታላቁ ፍልሰታ እና 8ኛው የአለም 8ኛ ድንቅ ቤት ሰርንጌቲ እና ማሳይ ማራ አላቸው።

20.ኬንያ የሞምባሳ ወደብ በ1896 ከተቋቋመ በክልሉ የመጀመሪያው ወደብ ነበር።

21. ሶማሊያ ፓይለት በማፍራት ከአፍሪካ የመጀመሪያዋ ሀገር ነበረች።

22. በኡጋንዳ ለአንድ ቀን ለማቆየት ከአንድ ዶላር ያነሰ በቂ ነው.

23. ኢትዮጵያ ቅኝ ግዛትን እንዲቃወሙ ያደረጋቸው ጠንካራው ንጉሠ ነገሥት እና ነገሥታት ነበሯት።

24. ታንዛኒያ ፣ በቲዝ የሚገኘው ታንጋኒካ ሐይቅ በአፍሪካ ውስጥ ጥልቅ የሆነው ሀይቅ ነው።

25. በመጨረሻም የአለማችን ረጅሙ ወንዝ አባይ ነው 30 ሚሊዮን አመት ያስቆጠረው...
#ሚዛናዊ_ሕይወት_ለተሻለ_ነገ
@mizanawihewot
20 views19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 22:01:53
18 views19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 21:40:08 "ቢልጌትስ በሐብት የሚበልጠኝ አንድ ጥቁር ብቻ ነው" አለ

የአለማችን ቀዳሚ ባለጠጋ በአንድ ኢንተርቪው እንዲህ ተጠየቀ ከአንተ የሚበልጥ ባለጠጋ ማን ነው ? ከአንተ የሚበልጥህ ባለጠጋ አለ ?

‹‹አዎ የሚበልጠኝ ሰው አለ ፡፡ የሚበልጠኝ አንድ ሰው ብቻ ነው ፡፡ ከብዙ ዓመት በፊት ወደ ኒውዮርክ መሄድ ነበረብኝ ፡፡ ወደ ኒውዮርክ ለመሄድ አየር መንገድ ላይ ሳለሁ የተለያዩ ጋዜጦችን የጋዜጣ አዟሪዎች እጅ ላይ አየሁ ፡፡ ካየኋቸው ጋዜጦች መካከል አንዱን ወደድኩት ለመግዛት አስቤ ኪሴ ስገባ ዝርዝር ስላጣሁ ሳልገዛው መልሼ ተውኩት ፡፡

በድንገትም አንድ ጥቁር ጋዜጣ አዟሪ ልጅ መጣና ጋዜጣውን ሰጠኝ ፡፡ ዝርዝር የለኝም አልወስደውም አልኩት እርሱም ችግር የለውም በነጻ ውሰደው አለኝና በነጻ ሰጠኝ ፡፡

ከሦስት ወር በኋላ ተመልሼ በዚያው አየር መንገድ ማለፍ ነበረብኝና በዚያ አየር መንገድ ሳልፍ አሁንም አጋጣሚ ሆነና ያንን ጋዜጣ አዟሪ ጥቁር ልጅ አገኘሁት ፡፡ አሁንም በነፃ ጋዜጣ ሰጠኝ ፡፡ እኔም በነፃ አልቀበልህም አልኩት እርሱም ግድየለም ከትርፌ ላይ እቀንሳለሁ ውሰድ አለኝና በነጻ ሰጠኝ ፡፡

ከ19 አመትም በኋላ ባለጠጋ ከሆንኩ በኋላ ያንን ልጅ ፈልጌ ለማግኘት ወሰንኩና ፈለኩት ከአንድ ወር ተኩል ፍለጋም በኋላ አገኘሁት ፡፡ ከዚያም አወቅከኝ ብዬ ጠየኩት ፡፡ አዎ አውቅሃለሁ ዝነኛው ቢልጌት አይደለህም አለኝ ፡፡ ከብዙ አመት በፊት ሁለት ጊዜ ጋዜጣ በነጻ ሰጥተኸኛል ፡፡ ያንን ውለታህን አካክሼ መመለስ እፈልጋለሁና የፈለከውን የትኛውንም ነገር እሰጥሃለሁ ጠይቀኝ አልኩት ፡፡

ያም ጥቁር ሰው በምንም መካካሻ ልትሰጠኝ አትችልም አለኝ ። እኔም ለምን አልኩት ። እኔ የሰጠሁህ ደሃ በነበርኩ ጊዜ ከድህነቴ ነው ፡፡ አንተ ግን ልትሰጠኝ የመጣኸው ባለጠጋ በሆንክ ጊዜ ነው ፡፡ እነዚህን ሁለቱን እንዴት አካክሰህ ልትሰጠኝ ትችላለህ ፡፡

ቢልጌትም ያጥቁር ወጣት በርግጥም ከእኔ የሚበልጥ ባለጠጋ ነው ፡፡

ለመስጠት ባለጠጋ መሆንህን ወይም ባለጠጋ እስክትሆን ድረስ አትጠብቅ ፡፡ መስጠት የልብ ጉዳይ ነው እንጂ የአቅም ጉዳይ አይደለም ፡፡
#ሚዛናዊ_ሕይወት_ለተሻለ_ነገ
@mizanawihewot
19 views18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 21:34:29
ተሳታፊ፡ ፓስተር፣ ስለጸሎት መጠየቅ እችላለሁ?
ፓስተር፡- በእርግጥ መጠየቅ ትችላለህ ምንድን ነው?

ተሳታፊ፡ የአክስቴ ልጅ ሞቷል።
ፓስተር፡ እና ስለ ምን መጸለይ ትፈልጋለህ?

ተሳታፊ፡- ባለፈው ሳምንት ሞቷል። በድህረ ዓለም እግዚአብሔር እንዲምረው ጸልይለት።

ፓስተር፡ ኦ ... ፈተና አለ እንበል መቼ ነው መጸለይ ያለብህ፥ ከፈተና በፊት ወይስ በኋላ?
ተሳታፊ፡- በእርግጥ ከፈተና በፊት...

ፓስተር፡ ልክ። ልክ እንደዛ ነው ከፈተና በኋላ ስትጸልይ እግዚአብሔር ውጤቱን እንዲቀይር እንደነገርከው ነው። እግዚአብሔር ታማኝ ስለሆነ ይህ አይቻልም። ውጤቱን ማታለል አይችልም.

በተመሳሳይ እኛ ስንሞት ፈተናው አልቋል። በህይወት እያለን የውሳኔያችንን ውጤት መለወጥ እችል ነበረ። ከሞትን በኋላ እጣ ፈንታችንን መለወጥ አንችልም።

ይላል ዕብራውያን 9፡27 አንድ ጊዜ እንሞታለን ከዚያም በኋላ በፍርድ እንገናኛለን።

ያ ማለት ሁለተኛ ዕድል የለም ማለት ነው። ይቅርታ ግን እውነታው ይህ ነው።

ተሳታፊ፡ ኦህ? እንደዛ ነው? እኛ በህይወት እያለን ነው ምናስተካክለው?

ፓስተር፡ አዎ። ለዘመድህ አዝኛለሁ። ከዚህ በኋላ ሊጸልይለት አይቻልም። ለዛም ነው ሰዎች በህይወት እያሉ ወንጌልን ሊረዱት የሚገባው። ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ኢየሱስን እንደ ጌታ እና አዳኝ መቀበል ነበረባቸው።

ተሳታፊ፡ እሺ ፓስተር።

ከሞት በኋላ መዳን እንዳለ የሚያስተምሩ አብያተ ክርስቲያናት ከቅዱሳት መጻሕፍት ጋር የሚጻረር ነገር እያስተማሩ አባላቶቻቸውን እያታለሉ ነው።
ከሞት በኋላ መዳን እንደሚችሉ የሚያምኑ ሰዎች ከሞት በኋላ መዳን እንደሌለ እውነቱን ሲያውቁ በሕይወታቸው ውስጥ ትልቁን ድንጋጤ ያገኛሉ።
ሰዎችን ነፃ የሚያወጣው ይህ ብቻ ነውና እውነትን አስተምር! ( ዮሐንስ 8:32 )
#ሚዛናዊ_ሕይወት_ለተሻለ_ነገ
@mizanawihewot
19 views18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 20:11:09 በፍቅር ማሸነፍ!

ሰዎችን ሁሉ አሳምናለው ካልክ ከድካም ውጪ ምንም አታተርፍም፤ ዝቅ ማለት ካለብህ ዝቅ ትላለህ፣ ያንን ጊዜ አጎንብሰህ ማለፍ ካለብህ አጎንብሰህ ታልፋለህ።

አንዳንዴ ታሪክ የምትሰራው በማሸነፍ ብቻ አይደለም፤ ለፍቅር ስትል ዋጋ በመክፈልና በመሸነፍም ነው። ይሄን የምታደርገው ለጊዜው ተሸንፈህ ለዘላለም ለማሸነፍ ነው!
#ሚዛናዊ_ሕይወት_ለተሻለ_ነገ
@mizanawihewot
19 views17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 20:09:23 #ከትዳር_በፊት_ማወቅ_የሚገባን_ነጥቦች _በጥቂቱ
እባካችሁን ለሁሉም ሰው እንዲደርስ ሼር ያድርጉ
1.#አትቆጣ ቁጣ ትዳርን ይገላል ።

2.#_እምነት_ይኑርህ ፦ እምነት ማጣት ትዳርን ያፈርሳል ።
3.#_ድክመት_አይኑርህ ፦ ድክመት ትዳርን ያቀዘቅዛል ።

5.#_የሰው_ወሬ_አትስማ ፦ የሰው ወሬ ትዳርን ያፈርሳል ።

6.#_ቸልተኝነት_አይኑርህ ፦ ቸልተኝነት ትዳርን ይገላል።

7.#_እኔ_ብቻ_ያልኩት_ይሁን_አትበል ፦ እኔ ብቻ ያልኩት ይሁን ማለት ትዳርን ያቀዘቅዛል ።

8.#_ለሚስትህ_እንክብካቤ_ይኑርህ ፦ ለሚስትህ እንክብካቤ አለማድረግ ትዳርን ያቀዘግዛል ።

9.#_ገንዘብን_አታባክን ፦ ገንዘብ ማከን ትዳር ውስት እንከን ይፈጥራል ።

10.#_የጓደኛ_ብዛት_አይኑርህ ፦ የጓደኛ ብዛት ትዳር ውስጥ ችግር ይፈጥራል ።

11.#አትቅና ፦ መቅናት ትዳርን ይገላል ።

12.#_ራስ_ወዳድነት_አትሁን ፦ ራስ ወዳድነት ትዳርን ያፈርሳል ።

13.#_የሚስትህን_ፍላጎት_አዳምጥ ፦ የሚስትን ፍላጎት አለማዳመጥ ትዳርን ያፈርሳል።

14.#_ሱስ_አይኑርህ ፦ ሱስነት ትዳርን ይገድላል ።

15.#_የራስህን_ፍላጎት_አትከተል ፦ የራስን ፍላጎት መከተል ትዳርን ያፈርሳል ።

16.#_ከሚስትህ_ጋር_የምክክር_ሰዓት_ይኑርህ ፦ ከሚስትህ ጋር የምክክር(የንግግር)ሰዓት አለመኖር ትዳርን ይገላል ።

17.#_ከልክ_በላይ_የዋህ_አትሁን ፦ ከልክ በላይ የዋህነት ትዳርን ያቀዘቅዛል ።
#ሚዛናዊ_ሕይወት_ለተሻለ_ነገ
@mizanawihewot
17 views17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 19:33:52
ቢሆን ጥሩ ነበር፣ ካልሆነ ግን . . .

ቢሆን ጥሩ ነበር፣ ካልሆነ ግን ሌላ መንገድ አለ! ሌላ ሕይወት አለ! ሌላ አቅጣጫ አለ! ሌላ አማራጭ አለ!

• እውነት ነው፣ ተምሬ ቢሆን ኖሮ ጥሩ ነበር . . . የመማሩን እድል ካላገኘሁ ግን ሕይወትን ውብ የሚያደርጉ ሌሎች ብዙ አማራጮች አሉ፡፡
• እውነት ነው፣ ፍቅረኛ ቢኖረኝ ኖሮ ጥሩ ነበር . . . ትክክለኛ ፍቅረኛ ካላገኘሁ ግን ትክክለኛ ሕይወት የምመራበት ብዙ እድሎች አሉኝ፡፡
• እውነት ነው፣ ትዳሬ በሰላም ቀጥሎ ቢሆንና ባይፈርስ ጥሩ ነበር . . . አንዴ ከሆነና ሁኔታውን በፍጹም ማደስ ካልቻልኩ ግን የተዝረከረከውን ሕይወቴን አፋፍሼ፣ ሰብስቤና እንደገና አደራጅቼ በአዲስ መልኩ ሕይወት ይቀጥላል፡፡
• እውነት ነው፣ የምወደው ስራ ቢኖረኝ ኖሮ ጥሩ ነበር . . . ሁኔታው ያንን ለማግኘት ካልፈቀደልኝ ግን ባለኝና ካለሁበት በመነሳት የማድግበትን መንገድ የመፈለግ መነሳሳቱ አለኝ፡፡

በአጭሩ፣ ሕይወት እኔ እንደምፈልጋት ብትሆን ጥሩ ነበር፣ ካልሆነ ግን ለምን አልሆነም ብዬ ደብቶኝ አልውልም፡፡ ቀና እላለሁ! ብርቱ ሰው ለመሆን እወስናለሁ! ስብር አልልም! አልደካክምም!
#ሚዛናዊ_ሕይወት_ለተሻለ_ነገ
@mizanawihewot
18 views16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 18:51:41 የፍቅርና የአብሮነት ትስስር

ለባልና ሚስቶች . . .

ከትዳር አጋራችሁ ጋር አብራችሁ ባሳለፋችሁ መጠን ፍቅራችሁ ይጨምራል፡፡ ፍቅራችሁ በጨመረ ቁጥር ደግሞ አብሮ የማሳለፍ ፍላጎታችሁ ይጨምራል፡፡

ከተጋቡ ብዙ አመታቸው ሆኗቸው እንኳን አብረው የሚያሳልፉና የሚዋደዱ ባልና ሚስቶች ካያችሁ ከእነዚህ ከሁለቱ ልምምዶች ውጪ ሌላ ምስጢር እንደሌለው ላስታውሳችሁ፡፡ እንደ መነጋገር፣ ይቅር መባባልና የመሳሰሉት መልካም የትዳር ምስጢራት ሁሉ የእነዚህ ሁለት መሰረታዊ ልምምዶች ውጤቶች ናቸው፡፡

“ታዲያ ከየቱ እንጀምር?” ለምትሉ፡-
አብሮ ከማሳለፍ ጀምሩ፤ ፍቅር ራሱ ይከተላል፡፡ ትዳራችሁን ከመጀመራችሁ በፊት የጀመራችሁት በፍቅር ነበር፡፡ እሱ ከጠፋ መጀመሪያ የተበላሸው አብሮ የማሳለፍ ጉዳይ ነው፡፡

“አብሮ ማሳለፍ ማለት ምን ማለት ነው?” ለምትሉ ደግሞ፡-
አብሮ ማሳለፍ ማለት፣ ጠዋት ቁርስ አብሮ መመገብ፤ ቢቻል ለምሳ መገናኘትና አብሮ መብላት፤ በስራ መካከል ምክንያትም ኖረ አልኖረ መደዋወል፤ ባገኛችሁት አጋጣሚ ሁሉ ማታ አብሮ ማምሸት፤ እቤት አብሮ መቀመጥ፤ በእረፍት ጊዜ አብሮ መውጣትና መግባት፤ ወሲብ-ነክም ሆኑ ከዚያ ውጪ የሆኑ የአካል ንክኪዎችን ማዘውተር . . .፡፡

“በግላችን የምናደርጋቸው ነገሮችና የምናገኛቸው ሰዎች ጉዳይስ?” ለምትሉት፡-
አብሮነት ሲጨምርና ከዚያው ጋር ፍቅር አብሮ ሲጋጋል በግላችሁ የምታሳልፉት ጊዜያችሁ ጉዳይ በራሱ መስመሩን ይይዛል፡፡

መልካም ትዳር!

D.r eyob
#ሚዛናዊ_ሕይወት_ለተሻለ_ነገ
@mizanawihewot
16 views15:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ