Get Mystery Box with random crypto!

' ኤሴቅ ' ክፍል ~፪፻፴~ ( 230) በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888 ወገሜት ቅቤው የወጣ | ቅን ልቦች

" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፴~ ( 230)
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
ወገሜት ቅቤው የወጣ ወተት አጓቱ በእሳት ተሙቆ የሚጠጣ ነው። ወተቱ ወደ አይብነት ተቀይሮ ውሃው ለሰውነት ተስማሚ በመሆኑ አመሻሽ ላይ ተሙቆ ይጠጣል። እነ ሔዋን ግን በጭራሽ አይሆንም ምንም ነገር አንጨምርም ብለው አሻፈረኝ አሉ። ቀዳማዊም "በቃ ተዋቸው ሁላችንም በሚገባ ጠግበናል። በዛ ላይ እርጎ ጠጥተናል"ብሎ የነ ሔዋንን ድምፅ አስተጋባ "ወገሜቱ እኮ ጥሩ ነው። ስለደከማችሁም ለእንቅልፍ ጥሩ መቅኔ ይሆናል። "አለ ሙሉቀን ቅር እያለው። "አይ ወንድሜ እባክህ አትቸገር!"አለ ቀዳማዊ "አይይ የአንተ ነገር ደግሞ የምን መቸገር አመጣህ! ለማንኛውም ጥሩ ይሁን እሺ እንግዲህ አይሆንም ካላችሁ በግድ አልግታችሁ ነገር"አለና ወደ ዳሳሽ ዘወር ብሎ "ውሃው ለብ ብሏል አይደል?"አዎ ሞቅ ብሏል ለሰስ ብሏል"አለች ዳሳሽ "በይ ይዘሽው ነይ!" ለሰስ ያለውን ውሃ በቆርቆሮው ይዛ መጣች ከጎኑ ትንሽ ቀዝቃዛ ውሃ በባልዲ አስጠጋችና ሰፋ ያለ የእግር መታጠቢያ ገበታ አቅርበው የሙሉሰውንና የሱራፌልን እግር ያዙ። ሱራፌልና ሙሉሰው "በጭራሽ አይሆንም ብለው አሻፈረኝ አሉ" "ነገር ግን ሙሉቀንና ዳሳሽም ኮስተር ብለው "አይሆንም። ለእኛ የምታስቡ ከሆነ በረከቱን አትንፈጉን እንግዳን እግሩን ማጠብ በረከት ነው"በማለት ሞገቷቸው። ሙሉሰውና ሱራፌል ወደ ቀዳማዊ አንድ ላይ ዞረው በአይናቸው እንዲያስቆምላቸው ቢጠይቁትም "ይሄ እንኳ ግዴታ ነው"በማለት ለነ ሙሉቀን ወግኖ ቆመ። የግድ ሲሆንባቸው እግራቸውን ሰጥተው ታጠቡ። አጥበው ሲጨርሱ የእግር አውራ ጣታቸውን ስመው ምርቃት ተቀበሉ። በተመሳሳይ ሔዋንና ፊደላዊትም ታጠቡ። በመጨረሻ ሐምራዊን ዳሳሽ ቀስስ አድርጋ እግሮቿን አጣጥባ እንዳይደነዝዛት በደንብ ማሳጅ አድርጋ ጨረሰች። ቀዳማዊ ግን አይሆንም በማለት ዳግማዊ እንዲያጥበው አደረገ። በየ ማረፊያቸው አረፍ ብለው ይጨዋወቱ ጀመር።"ፍፁም ትሑቶች ናቸው። እነዚህ የክርስቶስ አምሳያዎች ናቸው። እነሱ ቃሉን ሳያውቁት ያደርጉታል ይኖሩታል። እኛ ግን ምን እንደሚደረግ እናውቃለን ነገር ግን ምንም ነገር አናደርግም። ስለዚህ ትክክለኛ ሐይማኖተኞች እነሱ እንጅ እኛ አይደለንም"ሲል ሱራፌል ደመደመ።ፊደላዊትም በሀሳቡ ሙሉ በሙሉ እየተስማማች "ነገር ግን ጥሩ የሚሆኑት አዲስ እንግዳ ለሆነባቸው ሰው ነው። ሲበዛ ደግ እንደሆኑት ሁሉ ጨካኝም ናቸው። በርግጥ እነ ሙሉቀን ችክክለኛዎቹ የዋሆች ናቸው"ብለዋ እነ ሙሉቀን ወደ እነሱ ሲሄድ ንግግራቸውን አቁመው ሌላ ወሬ ያዙ።
ጠዋት ላይ ሁላቸውም አንድ ላይ ቀርበው በሞሰብ ቁርሳቸውን በልተው ልብሳቸውን ቀያይረው ወደ ራስ አምባ ለመሄድ ተነሱ። ሐምራዊ ዘግየት ብላ ስለነበር ከእንቅልፏ የነባችው ለብቻዋ ቁርስ ልትበላ ስትል ቀዳማዊ አብሯት ቀረበና እያጎረሰ በደንብ አበላት። "ቀዳማ እንደው ምን ቢሰራላት ጥሩ ነው። ምንም እኮ አልጠየቅናትም ትውደደው ትጥላው?"አለ ሙሉቀን ሐምራዊን በስስት እየተመለከተ። "ምንም ሙሌዋ ችግር የለውም።ቢኖር አሳውቅህ ነበር። ሐምራ ብዙ ይሄ ቢሆን ያ ቢሆን ብላ አታማርጥም እንዲሁ ያገኘችውን ትመገባለች። ከሚገርምህ እኔ ታዲያ አንዳንድ ጊዜ አንቺ ልጅ ያረገዝሺው ልጅ ነው? ወይስ ቦርጭ ነው? ብዬ እቀልዳት ነበር"አለ ቀዳማዊ። "ግን የምር ሐምራ ማርም ከፈለግሽ ንፁህ ማር አለ እሺ?"አለ ሙሉቀን ሐምራዊን በስስት እየተመለከተ" "እሺ ሙሉቀን እንደ እንግዳ ዝም አልልም ችግር የለውም የምፈልገውን እናገራለሁ"አለችና ሐምራዊ የእለቱን ልብሷን ለመልበስ ወደ ጓዳ ገባች።
****
"ስም ተመቃብር በላይ እንደ ሰው ቆሞ ሲሄድ እንዲህ ነውይ! አይ ደጃዝማች ታረቀኝ ምናለ ልጅህን ለአፍታ ቀና ብለህ ብታየው"እያሉ የመንደሩ ሰው የቀዳማዊን ደረጃ በመመልከት ይናገራሉ። "ሁላቸውም ግልብጥ ብለው አይደል እንዴ የመጡት። የሚስቱ እናትና አባት ራሱ መጥተውየለ እንዴ!"አለ ሌላኛው። "ወትሮስ ሊቀሩ ኖሯል። ሀተጋቡ በኋላ እኮ የእሷ ቤተሰብ የእሱ ቤተሰብ ሚባል ነገር የለም"አለ አንደኛው የመንደሩ ነዋሪ "እሱማ ልክ ነህ" "ስለዚህ በይህ የስራ ምርቃት ጊዜ ያልመጡ በያውም የቀዳማዊን አካባቢ ማየትና የማን ዘር ነው የሚለውን ማየት ይፈልጋሉ። የኸተማ ሰው እኮ እንደራሱ ሀፍታምና የደህና ሰው ልጅ ታልሆነ ሊያፋቱ ሁሉ ይችላሉ!!!" ያን እንኳ ስለ ቀዳማዊ በደንብ ያውቁ ይሆናል። ልጆቹ ተከጃጅለው ነው የሚሆን ብቻ እስቲ ቀድመን እንሂድና ቦታ እንያዝ። ለጉድ ነው ድግሱኮ"ተባብለው ወደራስ አምባ እየተጠራሩ ሄዱ።
*
"ያ መንገድ ዳር ያለው ወደ ገበያው ስንሄድ" "እሺ " "እሱ ጋር በቆርቆሮ ተከብቦ ሲሰራ የነበረው ሕንፃ የቀዳማዊ ነው አሉ።እሱን ለማስመረቅ ነው ሁላቸውም ግልብጥ ብለው የመጡት"አለች አድና ለማለፊያ እያስረዳች። "ያነ ሁሉ የእሱ የው?"አለች ማለፊያ በመደነቅ "አዎ እህቴ እኔም የሆኑ የቀን ሰራተኛ ሲሰሩ የነበሩ የባሌ ዘመዶች ሲናገሩ ነው የሰማሁት"አለች አድና። ማለፊ ዝም አለች። "ሚስቱ በጣም ነው የምታምረው ደግሞ እርጉዝ ናት!"አለችና አድና ንግግሯን ቀጠለች። ወይዘሮ አትጠገብ ጉልበቷ ከድቷት አቅም አንሷት አልጋ ላይ ሆና የሚያወሩትን ትሰማለች። ምንም እንኳ የአልጋ ቁራኛ ባትባልም ነገር ግን በእድሜ መግፋት የመጣ ችግር ገጥሟታል። ጉልበቷን ይይዛታል። የቀዳማዊ ሚስት ነፍሰጡር መሆኗን ሲያወሩ ስትሰማ እንባዋን መቆጣጠር ተሳናት። አለቀሰች "እንግዲህ ይቺ አሮጊት ደግሞ ጀመራት። ልታላዝንብን ነው"አለች ማለፊያ እናቷን ዞር ብላ በንቀት እየተመለከተች። "አሁን ይሄ ምኑ ነው የሚያስለቅስሽ?"አለች አድናም የማለፊያ ሀሳብ ላይ የራሷን ሀሳብ እየጨመረች። ወይዘሮ አትጠገብ ትንፋሿን ዋጥ አደረገችና ጋቢያዋን ለብሳ ታለቅስ ያዘች።
****
"የተከበሩ የሀመረ ኖህ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ና ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የተከበራችሁ የሐመረ ኖኅ ከተማ ከንቲባ እንዲሁም የራስ አምባ ቀበሌ አስተዳዳሪና ስራ አስፈፃሚዎች እንዲሁም ኢንጂነር ቀዳማዊ ታረቀኝ እንኳን ደህና መጣችሁ"መድረክ አጋፋሪው ተናገረ። ታዳሚው አጨበጨበ። "እንግዲህ ላለፉት ሁለት አመታት ገደማ በጥንቃቄና በትልቅ ሀላፊነት ሲሰራ የነበረው ፕሮጀክት ዛሬ በይፋ ይመረቃል። ነገር ግን እስኪ ከማስመረቃችን በፊት ስለ ፕሮጀክቱ ስራ ጠቅለል አድርጎ እንዲነግረን ይህንን ፕሮጀክት በበላይነት እያስተባበረ ሲያሰራ የነበረውን አቶ አቤልን ወደ መድረክ ልጋብዝ" አለና መልካሙን (አቤልን)ወደ መድረክ ጋብዞት ወረደ። " እሺ በብዙ እንግዶችና አዋቂዎች ፊት ሆኜ ስናገር ይህ የመጀመሪያዬ ነው"በማለት ሳቅ ብሎ ታዳሚውንም በሳቅ ፈገግ አሰኛቸው። "ያው ይሄን ለመስራት ስናቅድ ሀሳቡን በማበረታታትና አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም ከቦታ አመራረጥም ጋር አብረውን ሆነው ለደገፉን የሐመረ ኖህ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቢሻው ሳህሌን በእናንተ ና በእኔ ስም ላመሰግናቸው እፈልጋለሁ። በመቀጠል........

@amba88
@ken_leboch