Get Mystery Box with random crypto!

' ኤሴቅ ' ክፍል ~፪፻፳፯~ ( 227) በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888 'ጥሩ እንግዲህ አንተ | ቅን ልቦች

" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፳፯~ ( 227)
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
"ጥሩ እንግዲህ አንተን የመሰለ የተማረ ኃይል ሀገራችን አብቅታለችና ባንተ ትጠቀማለች ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ"ብሎ ቀጥሎ ሌሎች ጥያቄዎችን እያነሳ እያለ። ወይዘሮ ትሕትና የምታየውን ነገር ማመን ከበዳት "እውነት ያ ትንሽዬ ልጅ ቀዳማዊ ነው?"አይኖቿን ጨፈን ከደን አደረገችውና "ዮአኪን ሂድና አባትህን ጥራው"ብላ ላከችው "አባዬ እማዬ እየጠራችህ ነው!" "እሺ ትንሽ ቆይቼ እመጣለሁ የሆነች ነገር እየሰራሁ ነው"አለ ደረጄ የማንበቢያ ክፍሉ ውስጥ ሆኖ። ዮአኪን አባቱ ያለውን ሳይጨምር ሳይቀንስ ለትሕትና ተናገረ። እምር ብላ ተነሳችና ደረጄ ጋር ሄደች። "ደሬ " ብላ ገና ሳትጨርስ "እራት ደርሶ ነው ትሑቴ? እመጣለሁ ትንሽ ጠብቂኝ" "ኧረ አይደለም እ ቀ ቀ ቀዳማዊ በቴለቪዥን ቀርቧል!" ትሕትና ተንተባተበች። "ቀዳማዊ ቀዳማዊ? ቀዳማዊ የእኛ?" "አዎ" ተስፈንጥሮ ተነሳና ሳሎኑ ጋር ደረሰ። ነገር ግን የቀዳማዊ ቃለመጠይቅ አልቆ ስለነበር። የመጨረሻ የጋዜጠኛውን ንግግር ነበር የሰማው "ክቡራን እንግዶቻችን ከኢንጂነር ቀዳማዊ ጋር የነበረን ቆይታ ይሄን ይመስል ነበር። በርግጥ የዛሬ ቆይታችን አንድ የቀደመ መምህሩን ለማግኘት በጠየቀን መሠረት በዛው አንዳንድ ጥያቄዎችን ብጠይቀው ጥሩ ነው ብዬ ስላሰብኩ እንጅ ተፈላልገን በደንብ ተዘጋጅተን አይደለም የተገናኘነው።በሌላ ጊዜ በሰፊ ዝግጅት የምንገናኝ ይሆናል። መምህር ደረጄንና ወይዘሮ ትሕትናን የምታውቁ ወይም ራሳችሁ ካላችሁ ከታች በሚታየው ስልክ ለኢንጂነር ቀዳማዊ ልትደውሉለት ትችላላችሁ"በማለት ከቀዳማዊ ጋር ሰላምታ ተለዋውጠው ተሰነባበቱ።
"ወይ ቀዳማዊ! እንዲህ ትልቅ ሰው ሆነ።በእውነት ፈጣሪ ክበር ተመስገን።"አለ አቶ ደረጄ እጆቹን ወደ ላይ ዘርግቶ። "ቁምነገረኛው የኔ ጌታ። አሁን ያቺንም እንደ ትልቅ እርዳታ ቆጥሯት እኮ ነው!"አለ ደረጄ ወደ ትሕትና ዘወር ብሎ "በጣም እንጅ በጊዜው ልጅ ስለነበር ሁሉም ጭንቅላቱ ላይ ይቀመጣል። ባለፈው ሲናገር አልሰማኸውም? "አለች የአስራ ሁለተኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተናን ከሀገሪቱ ከፍተኛ ውጤት አምጥቶ በቴለቪዥን ቀርቦ ቃለ መጠይቁን እያስታወሰችው። "አዎ ልክ ነሽ ከአስር አመት አመት በፊት ነው አይደል?"አለ ደረጄ የአመቱን ርዝመት ለማስታወስ እየሞከረ "አዎ ልክ ነህ አስር አመት መስከረም አለፈው!"አለች ትሕትና "ይሄን ሁሉ አመት ውጪ ነበር ማለት ነው?"አለ ደረጄ "ይመስለኛል። ግን በቅርቡ ነው የተሞሸረው ለሰርጉ መጥቶ ይሁን አላውቅም!!" "እውነትሽን ነው አገባ?" "አዎ አንተን እያስጠራውህ እያለ ጋዜጠኛው ስለ ትዳር እየጠየቀው ነበር!" "ወይ ፈጣሪ። በእውነት ይሄን ስላሰማኸኝ በጣም ደስ ብሎኛል አምላኬ" ብሎ ደረጄ "በቃ እንደውልለት"አለ "አሁንማ መሽቷል ነገ ባይሆን እንደውልለታለን" "ኧረ ችግር የለም። አሁን በዚህ ስዐት ምሽት አይባልም እኮ"ብሎ ደረጄ የቀዳማዊ ስልክ ነው ተብሎ የተለጠፈውን ስልክ ቁጥር ስልኩ ላይ ፅፎ ደወለ
****
ሐምራዊ የቀዳማዊ ጭን ላይ በጀርባዋ ተኝታ እንቅልፍ ወስዷታል። በግንባሯ የወረዱትን ፀጉሮቿን እያስተካከለ የተከደኑ አይኖቿን እያዬ በስስት ይመለከታታል። ሐምራዊ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ነው የወሰዳት። "አንዱን ከአንዱ በሀሳብ እያላተመ ስልኩ ጠራ።ቀዳማዊ ስልኩን ለማንሳት ቢፈልግም ሐምራዊ ከኤንቅልፏ ልትነቃ ትችላለች ብሎ ስላሰበ ስልኩን ማንሳቱን ተወው። ሁለት ጊዜ ያህል ሲደወልለት ሐምራዊን አቅፎ አነሳትና መኝታ ክፍል አስገብቶ በስርዓት አስተኝቷት አለባብሷት ወደ ሳሎን መጥቶ ስልኩን አንስቶ ማን እኖደደወለለት ሲመለከት አዲስ ቁጥር ነው። "ምን አልባት መምህር ደረጄን የሚያውቅ ሰው ሊሆን ይችላል።"አለና መልሶ ደወለ። "አላልኩህም መሽቷል። ነገ እንደውልለት ስልህ አትሰማም "አለች ትሕትና "ምን ላጅርግ ብለሽ ነው አላስችል ብሎኝ አየሰደል..."በመሀል ስልኩ ጠራ "ይሄው ደወለ"አለ ደረጄ። "ሔሎ ጤና ይስጥልኝ" "አብሮ ይስጥልን"የሚል ምላሽ ሰጠው መምህር ደረጄ "ምልክት አግኝቼ ነበር"አለ ቀዳማዊ "ልጄ እኔ ደረጄ ነኝ!" "ም ም ም ምን?ቀዳማዊ አፉ ተያያዘ "አዎ መምህር ደረጄ ነኝ!! አሁን ቴሌቪዥን ላይ ስልክህን ወስጄ ነው"አለ "አ አዎ አዎ ጋሼ " ቀዳማዊ የሚለው ሁሉ ጠፋበት።"እንዴት ነህ" " እኔ በጣም ደህና ነኝ። ሁሌም ነው የማስባችሁ" "እናውቃለን ልጄ። እኛም እናስብህ ነበር። ወደ ዩኒቨርሲቲ ልትሄድ ስትል ቴሌቪዥን ላይ ነበር ያየንህ። ያው ወደ ውጪ ልትሄድ እንደምትችል ጠቆም ስላደረክ ሄደሀል ብለን አሰብን" "አዎ እዛው ነው ተምሬ የጨረስኩት ስራም እዛው ነው የጀመርኩት። ገና የዛሬ አመት ነው የመጣሁት" "ጥሩ ልጄ እንኳን ደስ አለህ! እዚህ ደረጃ እንደምትደርስ በአንተ ሙሉ እምነት ነበረን!!" "አመሰግናለሁ ጋሼ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እዚህ ደርሻለሁ! አሁን ተመስገን ነው ያለኝ ብዙ ነው" አለ ቀዳማዊ "ጥሩ ልጄ እንግዲህ በድምፅ ከተገናኘን በአካል ደግሞ ፈጣሪ ሲፈቅድ እንገናኛለን።አሁን በዚህ ምሽት የደወልኩት እስኪ ነጋ ስላላስቻለኝ ነው"አለ ደረጄ "እሺ ጋሼ ስላገኘኋችሁ ደስ ብሎኛል ነገ ራሴ እደውላለሁ። እትዬ ትሕትናንም ማግኘት እፈልጋለሁ!!" አለ ቀዳማዊ "እሺ ልጄ ታገኛታለህ ደህና እደርልኝ" "አሜን ደህና እደርልኝ ጋሼ!!!!
"አንቺን ማውራት ፈልጎ ነበር ።ግን የተኛሽ ስለሐሰለው ነገ ላውራት አለ። ስርአቱ አሁንም እንደድሮው ነው። ሲያወራኝ ድምፁ ውስጥ መቅለስለሱ ቀና ብሎ አለማየቱ ይታየኛል። እትዬ አባባሉ ላይም የድሮው ራሱ ትዝ ይለኛል።አንዳንዴ ሰዎች ቦታ ሲቀይሩ አብረው የሚቀየሩት ነገር አለ። ነገር ግን ቦታ አይደለም ሰውን የሚቀይረው።ራሱ ሰውየው ለመቀየር ካልፈለገ በቀር" አለ ደረጄ። ትሕትና ስታዳምጠው ከቆየች በኋላ "ቀዳማዊ ምይ ደርሶበት እዚህ እንደደረሰ ያውቀዋል። የስዎችን ደግነትም የሰውን ክፋትም ጠንቅቆ ያውቃል። በእርግጠኝነት እስካሁን እናቱን እና እህቶቹን እንደማያያግራቸውና ይቅር እንደማይላቸው"አለች "አዎ ልክ ነሽ በጭራሽ አያገኛቸውም ጠባሳዎቹ ናቸው። ይሄን ስኬቱን ሲያዩ እንደው የእግር እሳት ነው የሚሆንባቸ ግን እስካሁን ያልተረዳኝ ነገር ትሑቴ ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ? ያን ያህል በደል እንዴት አስችሏት ልጇ ላይ ታደርለች?ልጁ ህፃን ነው። በዛ ላይብቸኛ ወንድ ልጅ። አንድን ኤኮ እንዲህ ማድረግ ከባድ ነው። ደግሞ ጉዳዩ በወለዱት ላይ ሲሆን ያስጨኝቃል" ብለው እያወሩ እራታቸውን ይበሉ ጀመር።
ቀዳማዊ የሚይዘው የሚጨብጠው አጣ። ዜናውን ለሐምራዊ እንዳይነግራት ድብን ያለ እንቅልፍ ይዟታል።"ይሄ ሁሉ ሀሳብ የአንቺ ስለሆነ አድናቆት ይገባሻል የኔ ፍቅር"አለና ግንባሯን ሳም አደረጋት። "ተመስገን አምላኬ አሁን የምፈልጋቸውን ሰዎች አግኝቻለሁ። ልመናዬንም ሰምተህ ሰጥተኸኛልና ክብር ተመስገን ፈጣሪዬ ከዚህ በኋላ እድሜና ጤና ብቻ ስጠኝ። እሱም አንተን እያመሰገንኩ የምኖርበት ነው።"አለና አባታችን ሆይን ፀልዮ ተኛ።

@amba88
@ken_leboch