Get Mystery Box with random crypto!

' ኤሴቅ ' ክፍል ~፪፻፳፭~ ( 225) በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888 #ከትውስታ መልስ አሁ | ቅን ልቦች

" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፳፭~ ( 225)
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
#ከትውስታ መልስ አሁን
ኤሊያና እየሮጠች ሄዳ አባቷ ላይ ወጣችበት። "አቤት የኔ ወፍ ምን ፈልገሽ ነው?" "ምንም አልፈለኩም ተመልከት አባቴ ሁሉንም ትምህርት ደፍኜዋለሁ። መምህሯ ራሱ በጣም ጎበዝ ተማሪ ነሽ በርቺ እንቺ ሳይንቲስት ነው የምትሆኚው"አለችኝ እኔ ግን እንደ ቀዳማዊ ነው የምሆነው"አልኳት። ሙሉሰው ከሀዘን ወዲያው ባይወጣም በኤሊያና አነጋገር ፈገግ ብሎ "አንቺማ ከቀዳማዊም ትበልጫለሽ እንጅ የኔ ጀግና" "እንዴ አባዬ ተሳሳትክ ከቀዳማዊ በላይ እኮ ጎበዝ አይኮንም።እሱ ሁሉንም ይበልጣል እንጅ ማንም አይበልጠውም"አለች። አሁን ሙሉ በሙሉ ሳቀና "እሺ የኔ ቆንጆ በቃ እንደ ወንድምሽ ጎበዝ ሁኝ!" "አዎ እንደሱ ነው የሚባለው። ዋንጫ አመጣለሁ ወርቅ እሸለማለሁ።አሜሪካ ሄጄም አንደኛ እሆናለሁ" "አምንብሻለሁ የኔ ጣፋጭ" አለና ጉንጯን እያዟዟረ ሳማት። በኤሊያና ሁኔታ የነበረበትን የማህደሬ ትውስታ አጠፋው። ሁሌም የሆነ ጥሩ ነገር ባልተሰማው ጊዜ ኤሊያና ወይም ሔመን መጥተው ፈገግ ያደርጉታል። ይህ ነገር በጣም ይገርመዋል። ለኣ ሀዘናቸውን የሚረሱበት የሌላቸው ሰዎችም አሉ"ይልና ፈጣሪውን ያመሰግናል። እንደቤተሰብ ደስተኛ መሆኑ እፎይ ያስብለዋል። ደግሞ አሁን ከልጆቹ ራሱ አስበልጦ የሚወደውን ልጅ በመዳሩ ኩራትም ደስታም ተሰምቶታል።
****
"ሰርግ ቢሉሽ ሰርግ መሰለሽ እናቴ አገር ምድሩ አልቀረ። የእንግዳው አበዛዝ እንዳለ የተጠራው በሙሉ ሀፍታም ነው። የምግቡ አበዛዝ ትንሽ ከዛም ከዛም ስታነሽ ገና ሶስት አይነት እንዳነሳሽ ሳህንሽ ይሞላል። ኧረ ምኑ ቅጡ እታተዬ አለም ነበር አልኩሽ። ዘፋኞችም አሉ። የሚቀርጡም አሉ ይሄ ፎቶ ማንሻቸውን ይዘው በየቦታው ቆመው ቦግ ቦግ ቦግ ያደርጉታል። ብቻ ሰርጉ የአንድ ሰው አይመስልም የሶስት አራት ሰው ነው የሚመስለው"አለ ሙሉቀን የሰርጉን ሁኔታ ለመግለፅ ቃላት እያጠረው "እሰይ እሰይ እልል ነው። ወትሮስ እሱ የሁሉ ጌታ ሁሉንም ይመለከት የለ" " እነዛ ያስተማሩትን ሰዎች ብታያቸው አናቴ እንዴት የተባረኩና የተቀደሱ ሰዎች እንደሆነ። እኛን ራሱ እንዴት ሲያጣውቱን ና ሲንከባከቡን እንደነበሩ ብታይ" "እኔ ከተሜ ለያውም የአዲስአበባ ሰው እንደዛ ደግና ሩህሩህ ይሆናል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር። እንዴት ያሉ ደግ ሰዎች እንደሆኑ። አይፀየፉ ሁሉንም እኩል ነው የሚያዩት። እዚህ ተኛ ራስ አምባ ገበያ ስንሄድ ያሉት ሰዎች እንዴት እንዴት ነው የሚሆኑት ይቺም ከተማ ሆና። እና ሰዎቹ የጠባይ ሀብታም ና አዛኞች ናቸው"ብላ ዳሳሽም የሙሉቀን ሀሳብ ላይ ሀሳቧን ጨመረች። የሙሉቀን እናት በጣም ተደሰተች። "የኔ ከርታታ ልጅ እንኳን አባት የለኝሞ ብሎ እንዳይሰማው ተንከባከቡት። "የተጠሩት ሰዎች ራሱ አቤት ሰርግ ብለው እጃቸውን በግርምት አፋቸው ላይ ከድነው ነው የሄዱት። እኛ የማናውቀው መጠጥ ሁሉ አለ። ውስኪ ነው ጉደር ነው ያሉት?" ውስኪ ነው እንጅ"አለች ዳሳሽ "አዎ ውስኪ ብቻ እናቴ ምን አለፋሽ ድብልቅልቅ ያለ ሰርግ ነበር። ሙሽራይቱም ሸጋ ናት የተወለወለይ ቅቤ ቅል ነው ምመስለ። አይ ባህሪ አዬ ጠባይ ከቀዳማዊ ጋር ሆነው ነበር በመኪናቸው ወደ አየር መነሻው የሸኙን ብቻ የወንድሜን አለም አየሁት። አሁን በጣም ደስ ብሎኛል"ብሎ ሔዋን የሰጠቻቸውን እቃ ከሻንጣው እያወጣ ለእናትህ ስጥ የተባለውን እየመረጠ ከሰጣት በኋላ "ይሄን የላከችልሽ የቀዳማዊ እናት ናት"አለ ሙሉቀን "ኧረ ትባረክ ምነው ይሄን ሁሉ ልብስ መቼ ልለብሰው ነው የቀዳማዊን ራሱ ለብሼ መቼ አዳረስኩት?" "እንግዲህ ወደ በተስኪያን ስትሄጅ አንደኛውን ትለብሽና ሌላኛውን በፌስታል ሀይዘሽ ልክ ቤተስኪያን ስመሽ ስትጨርሽ ደግሞ ቀይረሽ ትመጫለሽ"አለና ሳቀ። ዳሳሽም ሳቀች። ሁላቸውም አንድ ላይ ተሳሳቁ።
*
"ጋሼ ለጫጉላ ሽርሽር ለአንድ ሳምንት ወይ ሁለት ሳምንት ወደ አርባምንጭ ሄደናል"አለ ቀዳማዊ "ጥሩ ነው። በሉ በደንብ ተዝናኑ ልጄ። ታዲያ ተጠንቅቃችሁ"አለ ሙሉሰው እንደማንኛውም ወላጅ ልጆቹ እንዲጠነቀቁ በማሳሰብ "እሺ ጋሼ እንጠብቃለን። ለእትዬም ንገረልኝ ስልኳን አላየችውም መሰል ስደውላት አታነሳም" "አይ ልጄ የእሷን ነገር ታውቀው የለ ለይስሙላ እኮ ነው ስልክ የምትይዘው። ልትደውል ስትፈልግ ብቻ ነው ስልክ እንዳላት ትዝ የሚላት"አለ ሙሉሰው።
ሐምራዊም ለእናትና ለአባቷ አሳወቀቻቸው። ደስ አላቸው እንደውም አባቷ ቀዳማዊን እንድታገናኘው ጠየቃትና አገናኘቻቸው። "ልጄ እንግዲህ ልጃችንን አደራ ሰጥተንሀል። እኛ ሀሳባችንን በአንተ ጥለናል። ከእንግዲህ ከአንተ በላይ ለእሷ እናስብላታለን ማለት አንችልም። ከአንተ በላይ ለእሷ የሚያስብ ማንም የለም። ስለዚህ እርስ በእርስ ተጠባበቁ ተንከባከቡ"አለ ሱራፌል። ቀዳማዊ በእሺታና በአክብሮት ሲያወራው ቆይቶ በመጨረሻ ስልኩን መልሶ ለሐምራዊ ሰጣት።
"አባዬ ግን በጣም ነው የሚወድህ። ከእኔ እንደውም ወደ አንተ ሳያመዝን ይቀራል። እኔም ቅልል ይሉኛል ሳወራቸው። ኮከባችን ተገጣጥሞ ይሆናል። አንዳንድ ጊዜ ሰውን ምንም ሳያደርገን እንዲሁ አይተን ልንወድ እንችላለን ልንጠላ እንችላለን። እና አባትሽም እንዲሁ ስለወደዱኝ ይሆናል" "እሪ ቀዳማ ግን እኔ ስለምወድህና የእኔ ባል ስለሆንክ ቢሆንስ የወደደህ?"አለች ሐምራዊ "እኔ በእሱ ግብረመልስ እወደዳለሁ ብዬ አላስብም። የራሱ መውደጃ ምክንያት ይኖረዋል ብዬ እንጅ የማስበው አንቺ ስለወደድሽኝ ብቻ ይወደኛል ብዬ አላስብም። ምን አልባት አንቺ ባልሽው መንገድ ወዶኝ ቢሆን እንኳ እኔ በዛ መንገድ እንደወደደኝ ማሰብ የለብኝም። እኔ አሁን የሚሰማኝ አንቺ ጋር እንኳ ብንጣላ ከእኔ ጋር የማይጣላ አድርጌ ነው ያሰብኩት" "አቤት አቤት ይሁንልህ አለችና ከንፈሩን ሳም አደረገችው።
*
መልካሙ (አቤል)"ቶሎ ቶሎ መስራት ይኖርብናል በዚህ አመት መጨረሻ ማለቅ አለበት"አለ ሁሉንም ሰራተኞች ከአናፂዎች እስከ ቀን ሰራተኞች ሰብስቦ። " አንዳንድ ጊዜም ከስራ መውጫችን ስአት ዘግየት ከስራ መግቢያችን ስአት ቀደም ብለን ሰርተን ብንጨርስ ለእኛም ደስ እንሰኛለን። ስራው አይጓተትም ማለት ነው። ይሄ የመጨረሻ ስብሰባችን ነው ከዚህ ቀኋላ ሁላችንም ሳንለግም በቅንነት እንሰራለን። ለራሳችሁ ስትሉ ለእናንተው ስትሉ ትሰራላችሁ "አለና ኮስተር ብሎ ተናግሮ ወደ ስራ ተሰማሩ።
**
"ቤርሲ ይሄ ነገር መብቃት አለበት። ደሐብ ከዚህ በላይ መሰቃየት የለባትም አንቺ እንደ ጓደኛ ማድረግ ካለብሽ በላይ አድርጊ። እያት በአንድ ጊዜ ነው ጥውልግ ያለቺው። በጣም ታሳዝናለች። ታሮስም እሷ በተጎዳችው ለሰክ ነው እየተጎዳ ያለው። ተስፋው እሷ ነች። እርግጠኛ ነኝ ታሮስ በጣም እንደሚንከባከባት"አለ ኪሩቤል "አዬ ኪሩ እንደሚንከባከባት ለእኔ ነው የምትነግረኝ እንኳን እኔ እሷም በደንብ ታውቃለች ግን አንዴ ልብህ ሲጎዳ ለሌላ ዝግ ይሆን የል ለዛ ነው......ትንሽ ትረጋጋና አናግራታለሁ"አለችና ቤርሳቤህ በዝምታ አቀረቀረች።

@amba88
@ken_leboch