Get Mystery Box with random crypto!

' ኤሴቅ ' ክፍል ~፪፻፳፬~ ( 224) በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888 'ምንም አትሆኝም ሌላ | ቅን ልቦች

" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፳፬~ ( 224)
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
"ምንም አትሆኝም ሌላ ሕይወት ሌላ ባል ይኖርሽ ነበር። መቼም የማታቂውን ሰው ስትፈልጊ አትኖሪም!" አለ ቀዳማዊ "እሱስ ልክ ነህ። ግን የምር የሚደንቅ ነው። በዚህ ልክ አንተን ኬር ያደርግህ እንደነበር ስትነግረኝ በጣም ነው የገረመኝ" "አዎ ግን እስካሁን ቅር የሚለኝ በአንድ ነገር ብቻ ነው። አንድ እስካሁን ላገኘው ያልቻልኩት ባለውለታዬ አለ"አለ ቀዳማዊ "ማነው እሱ አባትዬ?" "የቀድሞ መምህሬ ነው። ለእኔ ሲል በእኔ ምክንያት ከስራው ተባሯል። እኔ ከእናቴ ጋር ተጣልቼ እያለ እሱ ጋር ሆኜ ለተወሰነ ጊዜ እየተማርኩ እያለ እናቴ ከሊቀመንበራችን ጋር በመመሳጠር እንዲከሰስ አደረጉት ከዛም የሰው ልጅ በማባለግ ተብሎ ከስራው ተባረረ። ባለቤቱ ራሱ እንዴት አይነት መልካም ሴት ነበረች መሰለሽ። ደረጄ ነው የሚባለው እንደው እናትዬ እሱን ካገኘሁት ደስታዬ እጥፍ ይሆናል። አግኝቼው እንደዚህ ትልቅ ሆኜ ያለሁበትን ደረጃም አይቶ ምን ያህል ደስ እንደሚለው ባይ ደስ ይለኛል" "በቃ ታገኘዋለህ የኔ ፍቅር። የምታገኝበትን መንገድ እናመቻቻለን። ያው መቼም በአሁኑ ጊዜ ከተማ ገብተው ይሆናል። ስለዚህ በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች እንፈልገዋለን ለምሳሌ በሬዲዮም ሆነ በቴለቪዥን ብናስነግር መፍትሔ ይኖረዋል!"አለች ሐምራዊ። "እንዴት እስካሁን ይሄን አላሰብኩትም በቃ ይሄን መንገድ ነው እንጅ የምንጠቀመው"አለ ቀዳማዊ ከልቡ ደስ ብሎት። "እሺ በሚገባ እንጠቀመዋለን እንጅ የኔ ፍቅር"አለችና ቀበቶዋን አወለቀች። የቤታቸው ጊቢ ደርሰዋል። ቤታቸው ቅንጡ የሚባልና ሰፊ መሬት ላይ የተንጣለለ ግሩም ቤት!
ቤት ተቀምጠው እየተጨዋወቱ ሳለ ሙሉቀን ደውሎ በሰላም እንደገቡና ወደ ራስ አምባ ቀይ አፈር እየሄዱ እንደሆነ ነገራቸው። "ፍቅሬ አሁን በቀጣይ ምንድን ነው የምናደርገው?" "ጫጉላችንን አርባምንጭ ወይም ሐዋሳ እናሳልፍና በሁለተኛው ደግሞ ደስ ያለሽ ቦታ እንዝናናለን!!! ወይም ደግሞ በአንቺ ምርጫ እኔ ብቻ አንቺ አጠገቤ እስካለሽ ድረስ የትም ቦታ ሄጄ መዝናናት እችላለሁ"አለ ቀዳማዊ እያቀፋት።"አይ እኔም የተለዬ ሀሳብ የለኝም ፍቅሬ እንዳልከው መጀመሪያ አርባምንጭና ሐዋሳ እናሳልፍ"ብላ ሐምራዊም በአንድ ሀሳብ ተስማሙ።
*
"እንዴት አንጀት የሚበላ ልጅ ነው ሙሉዬ? እኔማ አሳዘነኝ ቀዳማዊን አይቶ አይጠግበውም። ጓደኛው ሳይሆን እኮ ወንድሙ ነው የሚመስለው። በል እስኪ ለቀዳማዊ ደውልልለትና በሰላም መግባታቸውን ጠይቀው"አለች ሔዋን። ሙሉሰው በሀሳብ ሄዶ ስለነበር በሔዋን ጣት ሲገካ ወደ ራሱ ተመለሰና "ምን አልሽኝ ሔዋኔ?" "እስኪ እነ ሙሉቀን በሰላም እንደገቡ ቀዳማዊን ደውለህ ጠይቀው ነው ያልኩህ" "እሺ እሺ "አለና ስልኩን አውጥቶ ደወለለት "አቤት ጋሼ"ቀዳማዊ ከወዲያኛው የስልክ ጫፍ ፈጣን ምላሽ "ልጄ ወንድምህ ደወለልህ? በሰላም ገብተዋል?" "አዎ ጋሼ አሁን ከደቂቃዎች በፊት ደውሎልኝ ነበር በሰላም ገብተዋል"አለ ቀዳማዊ "ጥሩ እንኳን በሰላም ገቡ። እናንተስ እንዴት ናችሁ ቤታችሁን ተላመዳችሁት?" "አዎ ጋሼ በደንብ ተላመደናል" "ጥሩ በሉ የወንድምህን ዜና ለመጠየቅ ነው የደወልነው። እናትህም ሰላም እያለችህ ነው መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ" "አሜን አሜን ለእናንተም መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ ጋሼ። እትዬን ሰላም በልልኝ" "እሺ እልልሀለሁ"
ሙሉሰው ከቀዳማዊ ጋር አውርቶ ከእንደገና በሀሳብ ንውዝ አለ። "ሙሉዬ የሆንከው ነገር አለ? ፍዝዝ ትክዝ እኮ አልክብኝ"አለች ሔዋን አጠገቡ እየተቀመጠች። "ቀዳማዊን በመዳራችን በጣም ነው ደስ ያለኝ። ግን መጀመሪያ እድራታለሁ ወግ ማዕረጓን አያለሁ ብዬ የነበረው የእህቴን ነበር"ብሎ የእንባ ዘለላዎቹን በጉንጮቹ ቦይ አፈሰሳቸው። "ያው ምን ታደርገዋለህ ፈጣሪ አልፈቀደልንም። የፈቀደልንን አድርገናል"አለች ሔዋን እሷም አይኖ እምባ ሞልቶ። ሙሉሰው በትውስታ ተመለሰ።
#ትውስታ "ኮሚሺነር መላኩ በጣም ተናዶ ጠረንጴዛውን በቡጢ እየነረተ እያንዳንዱን ታራሚ እየጮኸ ጠየቃቸው። እርስ በእርስ የት እንደነበሩ። ሰላማዊትን ለመጨረሻ ጊዜ ከማን ጋር እንደነበረች። ሁሏንም ነገር አንድ በአንድ በጥንቃቄ በመጠየቅ ሁላቸውንም አንድ በአንድ። የብዙዎቹ ታራሚዎች መልስ ለመጨረሻ ጊዜ ሰላማዊትን ያይዋት ከ ስርጉቴ ጋር እንደሆነ መሰከሩ። የሁሉም ጣት እና ነገሮች ሁሉ ወደ ስርጉት ሲወስድ ኮሚሺነር መላኩ ጊዜ ሳያጠፋ ስርጉትን ለብቻዋ የምርመራ ክፍል ይዟት ገባ። ለትንሽ ጊዜ ካናዘዘችው በኋላ እውነቱን ተናገረች። ዳዊት ብር እንደከፈላት ውጪ ላይ ካለ የእሱ ሰው ጋር እየተገናኙ እያንዳንዱን ነገር ሲያደርጉ እንደነበር ቀን በቀን ስታደርገው የነበረውን የቀን እንቅስቃሴዋን ሳይቀር አንድ በአንድ ተናዘዘች። "ከእኛ በተጨማሪ አቤልንም በተመሳሳይ ያስገደለው ራሱ ዳዊት ነው" አለች ስርጉት። ኮሚሺነር መላኩ ስርጉትን ባለችበት ትቷት ቀጥታ ወደ ወንዶች እስር ቤት ዳዊት ጋር አመራ
"ኮሚሺነር ዞረህ ዞረህ እኔ ጋር መጣህ ደግሞ ?" አለ ዳዊት ያስጠራው እንግዳ ኮሚሺነር መላኩ መሆኑን ሲመለከት። "አዎ ዞሬ ዞሬ መጣሁ። በርግጥ በመዞር ደከምኩ እንጅ መድረሻዬ መነሻዬ ነበር። መነሻዬ ላይ በትክክል መንገዴን አላሰብኩም ነበር መሰል የተነሳሁበት ቦታ ደረስኩ"አለ ኮሚሺነር ዳዊን ትክ ብሎ እየተመለከተ። "እና አሁን እኔ ምን ልርዳህ"አለ ዳዊት እግሩን እግሩ ላይ አነባብሮ። "የወንጀል ድርጊትህን ደርሰንበታል። ወይዘሮ ሰላማዊትንና አቶ አቤልን አንተ እንዳስገደልካቸው ደርሰንበታል"አለ ኮሚሺነር መላኩ። "ምኑን ነው የምትደርሱበት? ይሄ እኮ በጣም ተራ ነገር ነው። ትልቅ ነገር እኮ አይደለም ያገኛችሁት። እንደውም ይሄን ያህል ጊዜ እንደምትቆዩ ባውቅ ቀድሜ እኔ እንዳደረኩት እነግራችሁ ነበር። ግን እስኪ ትንሽ ጭንቅላታቸውን ይጠቀሙበት ፖሊስነታቸውን በሚገባ ይወጡ"ብዬ እንጂ ቀድሜ እነግራችኋለሁ እንኳን እንደዚህ አይነት ተራ ወንጀል ቀርቶ በበርካታ እንቆቅልሽ የታጀበ የወንጀል ድርጊት እንኳ ይደረስበታል"አለ ፈገግ እያለ። "እና አመንክ ማለት ነው?"አለ ኮሚሺነር መላኩ። "እንዴት አላምን!"ሰው የሰራውን ስራ ካላመነ ምኑን ሰው ሆነ ታዲያ?" " ጥሩ የአቃቤ ህግ ቢሮ እንሄዳለን የእምነት ክህደት ቃልህን ትሰጣለህ"ብሎ አብረው ተነሱ። ዳዊት ሳይጨምር ሳይቀንስ ለአቃቤ ህጉ ለኮሚሽኑ የነገረውን መልሶ ነገረው። አቃቤ ህጉ ተገርሞ ቃሉን እንዳለ አንድ በአንድ።አቃቤ ህግ የዳዊትን ቃል በደንብ ከመዘገበ በኋላ በድጋሚ የወንጀል ከስ መሠረተ።
"እንግዲህ አቶ ሙሉሰው ለሁሉም ነገር ፅናቱን ይስጥህ የእህትህን ገዳይ ይዘን ለፍርድ ማቅረብ አልቻልንም ነገር ግን የእህትህን ገዳዮች ገዳይን አጎኝተነዋል። የነ አቤልና ሰላማዊት ገዳይ ወንድምህ ዳዊት ነው። ይሄንን እውነት እሱሙ አረጋግጦልናል። ክሱን አልተቃወመም በደስታ ነው የተቀበለው። እንግዲህ በድጋሚ ፈጣሪ ያፅናህ "ብሎት ሙሉሰውን ተሰናብቶት ወደ ቢሮው ገባ። ሙሉሰው ራሱን ይዞ ሲያስብ ከቆየ በኋላ መኪናው ውስጥ ገብቶ ወደ ቤት ተመለሰ።"ዳዊት ስለተበቀላቸው ደስ ብሎኛል "አለች ሔዋን። ሙሉሰው ምንም አይነት መልስ አልመለሰላትም። ቀጥታ ወደ መኝታ ከፍል ገብቶ ነበር የተኛው

@amba88
@ken_leboch